ሳይኮሎጂ እና ህይወት! (Psychology & Life!)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Psychology


Human Psychology,Inspired Life, & Mindfulness!
For any questions, contact me @rezuzu

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Psychology
Statistics
Posts filter




ውድ የሳይኮሎጂ እና ህይወት ቤተሰቦች,

ከቴሌግራም በተጨማሪ Tik Tok ላይም አዲስ ገፅ መከፈቱን በደስታ እንገልፃለን!


https://vm.tiktok.com/ZMNDSPpdU/?k=1


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📖 የዓለማችን የመጨረሻው ቴክኖሎጂ!


ሰናይ ቀን!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🗓ቀን- 38

📖 ራስን ማወቅ!


ሰላማችሁ ይብዛላችሁ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu






Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🗓ቀን- 35

📖መቻቻል ወይስ መቀበል?


ሰላማችሁ ይብዛላችሁ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


ግኑኝነቶች ለምን ከፍቅር ወደ ጥላቻ ይሄዳሉ!?

🗓ቀን- 34

📖 ጥልቅ እይታዎች!

https://youtu.be/JWirS0eyhkQ

@inspiredjourney
@rezuzu


የሳይኮሎጂ እና ህይወት ቤተሰብ ስለሆኑ እና ለተሻለ ማንነት ስለሚያነቡ እናመሰግናለን!🙏🏾

ሰላማችሁ ይብዛ🙏🏾🙏🏾🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


🗓ቀን- 33

📖 ፎቢያ /Phobia/


ፎቢያ የሚለው ቃል መሰረቱ ከግሪክ ቃል ፎቦስ( Phòbos) ሲሆን ፤ትርጓሜውም ፍራቻ እንደማለት ነው::

ፎቢያ ከመጠን ያለፈና ምክንያታዊ ያልሆነ ፍራቻ ሲሆን፤ በዋነኝነት በሶስት ዋና ዋና አይነቶች ይከፈላል::

የመጀመያው አይነት ሶሻል ፎቢያ(Social Phobias) ሲባል ፤ይህም በውስጡ ሰው ፊት ቆሞ ማውራት መፍራትን፣ ከሰዎች ጋር ተቀላቅሎ የመጫውት ፍራቻ እና ሌሎች ከማህበረሰብ መስተጋብር ጋር የተያያዙ ፍራቻዎችን በውስጡ ያጠቃልላል::

ሁለተኛው አይነት ደግሞ አጎራ ፎቢያ (Agoraphobia) የሚባለው ሲሆን ፤ከቤት ውጭ መውጣትን መፍራት፣ ውጭ ብወጣ በሽታ ይዘኝ ይሆን ብሎ ያላግባብ መስጋት፣ በተወሰነ ቦታ ላይ ተገድቦ መኖርን እና የመሳሰሉትን ያካትታል::

ሶስተኛው አይነት ደግሞ፤ ስፔስፊክ ፎቢያ (Specific Phobias) ይሰኛል:: ይህ ደግሞ የተመረጡ እቃዎችን፣ እንስሳትን ፣የተፈጥሮ አከባቢዎችን ወይም ሁኔታዎችን ያለ ልክ መፍራትን ይጨምራል::

በአለማችን እጅግ ብዙ ሰዎች ካሉባቸው ፎቢያዎች መካከል፤
👉🏿 አክሮ ፎቢያ (Acrophobia)- ከፍታን መፍራት ፣
👉🏿ኦፊድዮ ፎቢያ (Ophidiophobia )- የእባብ ፍራቻ፣
👉🏿ትራይፓኖ ፎቢያ ( Trypanophobia )- የ መርፌ ፍራቻ፣ 👉🏿አራክነ ፎቢያ ( Arachnophobia) - የ ጊንጥ(Spider) ፍራቻ ጥቂቶቹ ናቸው::

ሰላም ይብዛላችሁ!🙏🏾
@inspiredjourney
@rezuzu


🗓ቀን- 32

📖 ዳወን ሲንድሮም/ Down syndrome/

ዳወን ሲንድሮም የሚከሰተው አንድ ልጅ ሲወለድ ሊኖረው ከሚገባ 46 ክሮሞዞም በተጨማሪ አንድ ክሮሞዞም ኖሮት 47 ክሮሞዞም ያለው ሆኖ ሲወለድ ነው።

ይህ ተጨማሪ ክሮሞዞም መኖሩ በሚወለደው ልጅ የአእምሮ እና የመልክ/አካላዊ ገፅታ እድገት ላይ ተፅእኖ እንዲኖር ያደርጋል።

የሚከሰትበት ምክንያት ይህ ነው ተብሎ ማስቀመጥ ባይቻልም ፤ ከዘር ጋር በተያያዘ ማለትም በቤተሰብ ውስጥ ዳወን ሲንድሮም ያለው ሰው መኖር እና የወላጆች የእድሜ ሁኔታ መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቀሳል። ነገር ግን፤ በሃያዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወላጆችም ችግሩ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ጥናቶች ያመለክታሉ ።

አንድ ልጅ ዳወን ሲንድሮም ያለው ወይም የሌለው መሆኑ በእርግዝና ወቅት በሚደረግ አምኒዬስንተሲስ የተባለ ምርመራ ማወቅ ሲቻል 3 አይነት የዳወን ሲንድሮም አይነቶችም አሉ። ( Trisomy 21,Mosaic, Translocation)

ዳወን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ የሆነ ትምህርት የመቀበል፣ አካባቢን የመረዳት፣ የማስታወስ፣የንግግር፣ እጅና እግርን አቀላጥፎ የመጠቀም እና እራስን የመርዳት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል።

የተቀናጀ ባህሪ እና ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ እና ደስተኛ ሂወት እንዲመሩም ያግዛቸዋል።

በየአመቱም March 21 - የዳውን ሲንድሮም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ተብሎ ይከበራል።


ሰላማችሁ ይብዛ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


🗓ቀን- 31

📖 ፍረጃ!


በአንድ ወቅት አንዲት የ 7 ዐመት ልጅ ከወላጅ አባቷ ጋር በመንገድ ላይ እየሄዱ አፕል /ፖም/ የሚሸጥ ሰው ታይና እባቷን እዲገዛላት ትጠይቀዋለች::

አባቷ ብዙ ገንዘብ ባይዝም ፤ባለችው ሳንቲም ለእሱ እና ለልጁ ሁለት ፍሬ አፕል ገዛ::

ታድያ ሁለቱም አፕል ህፃኗ እጅ ላይ ነበርና አንዱን እንድትሰጠው ሲጠይቃት ሁለቱንም አፕሎች በየተራ ገመጠቻቸው!...አባትየው በልጁ ድርጊት በጣም አዘነ፤ ፊቱ ላይ የነበረውም ፈገግታ ሁሉ ጠፋ:: ለኔ ብቻ የምትል ራስ ወዳድ ልጅ መሆኗም አስከፋው::

ብዙም ሳይቆይ ግን ፤ልጁ "አባዬ እየጠራሁ እኮ አትሰማም.... ይሄኛውን እንካ፤ ከሁለቱ በጣም የሚጣፍጠው አፕል እሱ ነው"ብላ በቀኝ እጇ የያዘችዉን አፕል ሰጠችው::

አባትየውም የሚጣፍጠውን ለሱ ለመስጠት እንደሆነ እንደዛ ያረገችው ሲገባው ቀድሞ ባሰበው ነገር ተፀፀተ::...

...ነገሮችናንና ሰዎችን እንዲህ ናቸው ብለን ለመፈረጅ አንቸኩል:: ግዜ መስጠትና ለመረዳት መሞከር ከፀፀት ያድናልና!

ሰላም ለናንተ!🙏🏾🙏🏾🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


🗓ቀን- 30

📖 ፊኛ እና ከፍታ!

በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ አየተዘዋወሩ በአየር የተሞሉ እና የተለያየ ቀለም ያላቸውን ፊኛዎችን ይሸጡ የነበሩ አንድ ትልው ሰው ነበሩ::

ታድያ እኝህ ሰው ገበያው ሲቀዛቀዝ፤ ውስጡ በሂልየም ጋዝ የተሞላ አንድ ፊኛ ወደሰማይ ይለቃሉ:: ይሄንንም ያዩ ህፃናት፤ ፊኛ ለመግዛት ከወላጆቻቸው ጋር ወደ እሳቸው እየተሯሯጡ ይመጣሉ::

በአንድ ወቅት እዲህ ሲያደረጉ የተመለከተ አንድ ህፃን ልጅ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው::

" ጥቁሩን ፊኛ ቢለቁት እንደሌሎቹ ፊኛዎች ወደ ላይ ይወጣል?"

እርሳቸውም...
" ልጄ ፊኛው ወደ ላይ ከፍ ብሎ እንዲነሳ የሚያደርገው ፤የቀለሙ አይነት ሳይሆን በውስጡ ያለው አየር ነው!"አሉት...

ታድያ እኛም በህይወታችን ከፍ እንድንል የሚደርገን፤ በውጣችን ያለን ቀና አመለካከት፣ አስተሳሰብና መልካምነት እንጂ ቀለማችን እና ከላይ ሚታየው መልካችን እንዳልሆነ ተረድተን ወደውስጣችን በመመልከት ክፍ ማለትን እንለማመድ!

ከፍታችሁ ይብዛ!🙏🏾🙏🏾🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


📖ሕይወት እና ወቅቶች!

🗓ቀን- 29


በድሮ ጊዜ 4 ልጆቹን አንድ ትምህርት ሊያስተምር የፈለገ አባት ልጆቹን እሩቅ ቦታ ያለችን አንድ የኮክ ተክል ሄደው እዲያዩ አዘዛቸው::

ታድያ ይሄን እንዲያደርጉ ያዘዛቸው በተለያየ ወቅት ነበር::የመጀመርያው ልጅ በክረምት(በበረዶ) ነበር የተላከው ፣ሁለተኛው በፀደይ፣ ሶስተኛው በበበጋና ፣ አራተኛው ደግሞ በመኸር ወቅት ነበር::

በጨረሻም አባትየው አንድ ላይ ሰብስቦ ስላዩት ዛፍ እንዲነግሩት ጠየቃቸው:: እንዲህም ሲሉ ነገሩት...

የመጀመሪያው - በጣም የሚያስጠላ ዛፍ ነው ፣አንድ ቅጠል እንኳን የሌለው የተጣመመ ዛፍ ነው አለ
2ኛው - በአረንጓዴ እንቡጦች እና አበቦች የተሞላና ተስፋ የሚሰጥ ዛፍ ነው...
3ኛው- የፈኩ አበቦች ያሉበትና ለአከባቢውም ጥሩ ማኣዛ ሚሰጥ በጣም የሚያምር ዛፍ ነው...
4ኛው - እኔ ያየሁት ግን በበሰሉና በተንዥረገጉ ፍሬዎች የተሞላ ዛፍ ነው ሲል ተናገረ

አባትየውም እንዲ አሉ፤
"ሁላችሁም ያያችሁትና ያላችሁት ነገር ልክ ነው! ምክንያቱም ደግሞ ሁላችሁም ያያችሁት የዛፉን አንድ ወቅት ብቻ ነውና:: የሰውንና የዛፍን ህይወት በአያቹት በአንዱ ወቅት ብቻ አትፈርጁ:: የነገሮችን ሙሉ ምንነት ምትረዱት በሁሉም ወቅቶች ስታልፋ ብቻ መሆኑንም አትዘንጉ::

በበረዶው ወቅት ተስፋ ከቆረጣችሁ ፤በመኸር ወቅት የሚመጡትን የደስታ ፍሬዎች አታጣጥሙምና!”...

ሰላም ይብዛላችሁ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


ስኬት ምንድን ነው?

🗓ቀን- 28

📖 ጥልቅ እይታዎች!



https://youtu.be/TxXUtthHvb0


@inspiredjourney
@rezuzu


🗓ቀን- 27

📖 ተመስገን
(
መቅደላ መኩርያ እንዳካፈለን)

ሰው ሆይ፦

"ሁሌ በተቻለኝ መጠን የምሰብካት ስብከት አለችኝ … የምሬን!!!

ጠዋት ስትነቃ ተመስገን በል። በርዕሷ በረከቶችህን ቁጠር። ተመስገን በል … ሞተህ ልታድር ትችል ነበራ። ከዛ በኋላ ከአልጋህ ወርደህ ስትቆም ተመስገን በል … በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበራ። ስትንጠራራ ደግሞ … (ደስ አይልም?) …

መንጠራራትን የሰጠህን ተመስገን በል። እንዲህ እያልክ ደሞ ሽንትህ ወጥሮህ ስትሸና … የጠጣኸው ሁሉ ሽንት ሆኖ መውጣቱ … ይኼ ሁሉ የማናውቀው ተዓምር ውስጣችን በመሰራቱ … ተመስገን በል። ከዚያ ደግሞ ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድ መንገዱ ሁሉ ጤና ነው … ታክሲው፣ ሰዉ፣ ምኑም ምኑም፣ ለማኙም፣ መነኩሴውም … ተመስገን በል።

ምክንያቱም … ጀነራል ሰጥአርጋቸው … (ህምምም .. ቆይ አይ አሪፍ ስም ነበረች) … ሰጥአርጋቸው የሚባሉ ጀነራል "ጨለማን ተገን አድርገው" በታንክ ገብተው አገሩ ፀጥ ብሎ ቢቆይህስ… ምን ታደርግ ነበር? … ጠላት አለኝ ይሆን እንዴ? … ተመልሼ ልግባ? … አይ ደግሞ ተመልሶ ገባ ይሉኝ ይሆን? … ምናምን ትል ነበር። አገር ሰላም በመሆኑ ተመስገን በል። እቺን እያልክ ስትሄድ ደግሞ ቆማጣ ስታይ … እረስቼው … መዓት ነው … ይሄ ነው እንግዲህ ሁል ግዜ። ተመስገን በል አሁን … ተመስገን!!!"

ስብኃት ገብረእግዚአብሔር (ከDire Tube ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ እንደወረደ የተወሰደ)

ምስጋና ይብዛላችሁ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu
@positivetunes


📖 የገጣሚ ስዕል
( በ ኤፍሬም ስዪም )

🗓ቀን- 26

ሰናይ ቀን!🙏🏾🙏🏾🙏🏾


👉🏿 https://youtu.be/7csRJmYhQco?list=PLAPCM7YxDs3ObacKaYkZY32wxHWDcNYJk


@inspiredjourney
@rezuzu


ውሃ በብርጭቆ!

🗓ቀን- 25

በአንድ ወቅት አንድ መምህር በክፍል ወስጥ እያስተማሩ አንድ ተማሪ ጠርተው አንድ ብርጭቆ ውሃ በእጁ ከፍ አድርጎ እንዲይዝ አደረጉ:: ከዛም ተማሪውን የያዘው ውሃ ይከብድ እንደሆነ ሲጠይቁት ፤ ተማሪው ፈገግ ብሎ "እረ በፍፁም አይከብድም! ግማሽ ሊትር እንኳን አትሆንም እኮ" ብሎ መለሰላቸው::

ነገር ግን ከ10 ደቂቃ በሗላ ተማሪው እጁን እያመመው እንደሆነና ማስቀመጥ ይችል እንደሆነ መምህሩን ጠየቀ...

መምህሩም እንዲያስቀምጠው ከፈቀዱለት በሗላ እንዲህ አሉ...

"እዚህ ጋር ዋናው ነገር የውሃው ማነስና መብዛት ሳይሆን ፤ ለምን ያህል ግዜ ይዘነው ቆይተናል ሚለው ነው..."

በህይወታችንም ብዙ የሚያስጨንቁና የሚያሳስቡን ነገሮች ያጋጥሙናል:: ታድያ ያጋጠሙንና ያስጨነቁን ነገሮች ክብደት ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት በውስጣችን ለምን ያህል ጊዜ ተሸክመናቸዋል የሚለው ነው::

ይቅር ማለት ፣ቂም አለመያዝ ፣ያስከፉንና ያሳመሙንን የህይወት ገጠመኞችን በውስጣችን ይዘን አለመብሰልሰል እንዲሁም እልፍ በማለት የተሻለ ስነ- ልቦና እና ጤናማ ቀኖቻችንን እንፍጠር!

ደስታ ይብዛላችሁ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


ማፍቀር አለመቻል!
(ክፍል 2)

🗓ቀን- 24

📖 'ኢሞሽናል ዴፕሪቬሽን ዲስኦርደር' (EDD)

ታድያ የ ’EDD’ ችግር ያለባቸው ሰዎች የተያዩ ባህሪዎችን ያሳያሉ ከነዚህም መካከል ...
👉🏿ከሰዎች ጋር ግኑኝነት የመመስረትና የማስቀጠል ችግር
👉🏿 ለቤተሰብ አባላት ሳይቀር ፍቅርን መስጠት መቸገር
👉🏿ትኩረት መስጠት አለመቻልና ከሰዎች ጋር ሆነው በሃሳብ መወሰድ

👉🏿በተቻለ መጠን ከሰዎች ጋር ላለመሆን መሞከር እና በህብረት የሚደረጉ ዝግጅቶችን ማስወገድ

👉🏿የሚሰማቸውን ስሜት በቀላሉ አለመግለፅና ለሌሎች አለማካፈል

👉🏿እንዲሁም ለሌሎች መሰጠት አለመቻልና ሌሎችን ማስቀደም በሚኖርባቸው ጊዜ ላይ ሌሎችን አለማስቀደም...እና የመሳሰሉት ናቸው::

ህክምናውም ህመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት የሚለያይ ሲሆን በመጀመሪያ የህመሙን መነሻ ማከምና ከዛም እንደ 'ሳይኮቴራፒ' (Psychotherapy / Talk therapy) የመሰሉ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻለ ጤንነት ላይ መገኘት ይቻላል::

ጤና ይብዛላችሁ!🙏🏾🙏🏾🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu


ማፍቀር አለመቻል!

🗓ቀን- 23

📖 'ኢሞሽናል ዴፕሪቬሽን ዲስኦርደር' (EDD)

"ፍቅር ቀላልና ተፈጥሯዊ ፤ ሰው ግን እጅግ ውስብስብ ነው..."

'ኢሞሽናል ዴፕሪቬሽን ዲስኦርደር' (EDD) ወዳጅነትን፣ ጎደኝነትን ፣ የፍቅር ግኑኝነትን መመስረት አለመቻል፣ በቂ አደለሁም ብሎ ማሰብ እና በሌሎች ሰዎች አስተያየት በቀላሉ መነካት ልንለው እንችላለን::

'ማፍቀር አለመቻል' የሚለውን ቃል ስንሰማ ወደ አእምሮአችን የሚመጣልን፤ የተቃራኒ ፆታ ፍቅር ቢሆንም በዚህ ህመም የተጠቁ ሰዎች ግን ከወዳጆቻቸው እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያላቸው ግኑኝነት በእጅጉ ይጎዳል::

እንደ አብዛኞቹ የአእምሮ እክሎች ፤ ያልተስተካከለ የልጅነት አስተዳደግ የአንበሳውን ድርሻ ይዛል::
👉🏿 ከወላጅ ወይም ከ አሳዳጊ 'በቂ' ፍቅር አግኝቶ አለማደግ
👉🏿በቤተሰብ አባል( አባት/እናት/ወንድም/እህት ተደጋጋሚ መገለሎች እና ትኩረት አለማግኝት
👉🏿 ያልተገቡ ተደጋጋሚ ግሳፄዎችና የልጁን ማንነት የሚያወርዱ ንግግሮች
👉🏿 እንዲሁም ፍቅር 'በሌለበት' ቦታና ምህዳር ውስጥ ማደግ ሊጠቀሱ ከሚችሉት ዋነኞቹ ናችው!

ታድያ የ ’EDD’ ችግር ያለባቸው ሰዎች ምን ምን ባህሪዎችን ያሳያሉ?? ...በሚቀጥለው ፅሑፍ እንመለስበታለን...

ፍቅር ይብዛላችሁ!🙏🏾

@inspiredjourney
@rezuzu

20 last posts shown.