አዛኑ እስከሚጨርስ ድረስ የሚጠጡ ፆም መያዧዉ የአዛኑ መጨረሻ ብለዉ በማሰብ(በመጠርጠር) ለሚሉ የተሰጠ መልስ!
በሼይኸ ሱሌይማን አሩሀይሊ
ይሄ ስህተት ነዉ ከፊል አላዋቂዎች አሶላቱ ኸይሩ ሚነ ነዉም እስከሚል ድረስ የሚጠጡ የሚበሉ አሉ ከፊሎቹ ደግሞ አዛን ብሎ እስኪጨርስ ድረስ ይሄ ስህተት ነዉ። ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ብሉ ጠጡ ኢብን ኡሚ መክቱም አዛን እስከሚያደርግ ድረስ ብለዋል።
አዛን ወሰን አድርገዋል
አዛን ከበፊቱ አይነት አይደለም። ግዴታዉ አዛን ሲል ቶሎ መያዝ ማቆም ነዉ። አዛን እያለ
ሶስት ሁኔታዎች መብላት መጠጣት ይቻላል።
1ኛ) አዛን እያለ ዉሀ መጠጣት ፈልገህ እቃዉን አንስተሃል አዛን አድራጊዉ አሏህ አክበር አለ ጠጣ ጉዳይን እስክትሞላ ድረስ።
2ኛ) አዛን አድራጊዉ አዛን ካለ አፍህ ዉስጥ የጓረስከዉ ካለ ማዉጣት ግዴታ አይሆንብህም ዋጠዉ ፆምህ ትክክል ነዉ አልሀምዱሊላህ።
3ኛ) መድሀኒት አንስተህ አዛን አድራጊዉ አዛን ካለ መድኃኒት መውሰዱ ግድ ከኾነ ዉሰድ። መድሀኒት መዉሰድ እረስተህ አዛን ሲቃረብ ወደ ፍሪጅ ሄድክ ከፍሪጁ ወድሀኒቱን አወጣህ መድሀኒት መዉሰድ ፈለክ ከዚያ ቡሃላ ዉሀ መጠጣት ፈለክ ከዚያ ቡሃላ አዛን ሊል መድሀኒቱን ዉሰድ ዉሀ ጠጣ ፆምህ ትክክል ይሆናል ከዚህ ዉጭ ያለ አይፈቀድም።
Copy
https://t.me/islamictrueth