Forward from: 🌹ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም🌹
ተፍሲር ሱረቱ ኒሳዕ ፥ part 4
ከአንቀፅ 7-10
የሱረቱ ኒሳዕ 7ኛው አያ መውረድ ብዙ ነገርን ቀይሯል ፣ በጃሂሊያው ማህበረሰብ ሴት ምንም አይነት ድርሻ አልነበራትም ..
ምክንያቱም መውረስ የሚገባው ጠላት የሚመክት እንጂ ፈረስ ያልጋለበ ፣ በሰይፍ ያልመታ ፣ ቀስት ያልወረወረ ሰው እንዴት ብሎ ይወርሳል ይሉ ነበር ። እንደውም ሴቶችን እንደ እቃ በመቁጠርም እነሱም ይወረሱ ነበር - በጃሂሊያ ። ይህ በአረቦች ብቻ ሳይሆን በሩሞችም ፣ በፋርሶችም ዘንድ የነበረ ልማድ ነበር። ከዚህ አያ መውረድ በኋላ ግን መጠኑ ይለያይ እንጂ ሴትም ድርሻ አላት ትወርሳለች አለን ።
ባለ ደርሻዎች ሲከፋፈሉ ዙሪያውን የሚታዘቡ ሰዎች ይኖራሉ ። የነሱንም ነገር በ8ኛው አያ ተናገረ ። የሀብታምን ገንዘብ ልጆቹ ፣ እህት ወንድሞቹ ወይም ወላጆቹ ቁጭ ብለው ዳጎስ ያለ ድርሻ ሲያገኙ ጎረቤት ያለ የቲም ቁጭ ብሏል ፣ ሚስኪኖች አይናቸው እየቃበዘ እኛም ቢደርሰን ብለው ይጓጓሉ ። እነዛ ሰዎች እንዳይረሱ ምንም እንኳ መጠኑ ይህን ያህል ነው ባይባልም የተወሰነ ነገር ቀነስ አድርጋችሁ ስጡ «ተገቢ ንግግርም ተናገሯቸውም» አለን ፣ ሁሌም ከአንድ ስራ በኋላ መልካም ንግግርን ጎን ለጎን ነው የሚያስቀምጠው ቁርዐን ልብ በሉ ! ንግግር ተፅኖው ከባድ ነው ፣ ጦር ካቆሰለው ንግግር ያቆሰለው ያስቸግራል አይሽርም ። እንደገና ብዙ ችግሮችን በንግግር መፍታት ይቻላል ።
9ነኛው አያ ደግሞ ውርስ የሚያከፋፍሉ ሰዎች በሆነ ሰበብ ወደ አንድ አካል እንዳያደሉ "ነግ በኔ" ይበሉ አለ። ለልጆቹ ፊውቸር የሚሰጋ ሰው በሌላ ሰው ልጅ ላይ ግፍ መስራት የለበትም። እንዲሁ ወሲያ ላይ ሟች ያልሆነ ኑዛዜ ሲናገር የሰማ እንደሆነ መከልክልም አለበት ፣ አንዳንዴ ወራሾችን መጉዳት የሚፈልግ ሰው ይኖራል ። ለፍቼ ለፍቼ ይሄ መናጢ ልጅ ሊወርሰው ነው አንዴ ገንዘቤን :) "ሰደቃ ነው የማደርገው" ሊል ይችላል፣ ለዛም ነው 1/3 ድረስ እንጂ ከዛ በላይ ሰደቃ መስጠት አይቻልም ። "አሱሉሱ ወሱሉሱ ከሲር" ብለዋል ሀቢባችን ፣ በሌላ ሀዲሳቸው ድግሞ “ወራሾችህን ራሳቸውን የቻሉ አድርገህ ጥለህ መሄድ ድሆች አድርገህ እጃቸውን ወደ ሰው የሚዘረጉ አድርጎ ከመሄድ የተሻለ ነው” ብለዋል ።
10ኛው አያ የየቲም ገንዘብ መብላት እሳት መብላት እንደሆነ ይነግረናል ። ረሱልም “የሁለት ደካማ ሰዎችን (የቲሞች እና ሴቶች) ብር ከመብላት እንድትጠነቀቁ አደራ እላችኋለሁ” ብለዋውናል።
https://t.me/+VUDQfAORZa43NDM0