አምስት ፐርሰንት ብቻ ስኬታማ ይሆናሉ !
ምን ስላደረጉ ነው የተሳካላቸው ?
ዘጠና አምስት በመቶዎቹ ደግሞ አልተሳካላቸውም !
ምን ስላደረጉ ወይንም ስላላደረጉ ነው ያልተሳካላቸው ?
የየትኞቹን መስማት ትሻላችሁ ?
የሌላውን አላውቅም ።እኔ ግን ዘጠና አምስቱ ፐርሰንት ውስጥ ስላለሁ ከራሴ ስኬት አልባነት ብማር እመርጣለሁ ።
እኔ ቢዝነስ ስራ ስጀምር የጠራ ሃሳብ አልነበረኝም ። የስራ ሃሳቤንም አልገመገምኩትም ። clear thought and Idea evaluation አላደረኩም .አንድ በሉ ።
እኔ ጥሩ ቲም አልገነባሁም ። ታለንትድ ከሆኑት ጋር ለመስራት ሞክሬ ነበር ። እነርሱ ግን የተሻለ ሲያገኙ ሊታገሱኝ እና አብረን ፍሬውን እስክናይ ሊቆዩ የሚችሉ አልነበሩም ። ትልቅ ቲም መገንባት እና ታለንትድ ቲም መገንባት ልዩነቱን ያስተዋልኩት ከውድቀቴ ነበር ። ሁለት አላችሁ
እኔ ጥሩ የስራ አጋር አልመረጥኩም ነበር ።ክህሎትን compromize የሚያደርጉ አልነበሩም ። ይህ ሶስተኛዬ ነው ።
እኔ ስለ ካሽ ፍሎው ምንነት ምንም አላውቅም ነበር ። ገንዘብ እንዳገኘሁ ስራ ላይ አወጣለሁ ። መቼ እና በስንት መጠን መመለስ አለበት የሚባለውን ጥቅምና ጉዳት አላውቅም ነበር ። ይህ አራተኛ መሆኑም አይደል ?
እነዚህን እነዚህ የመሳሰሉት እኔጋ እንዳልነበሩ አስተዋልኩ። ከዚያም አምስቱ ፐርሰንቶች ጋ ሄድኩ እዚያ ግን ነበሩ ። ልብ አልኳቸው ።
አሁን አነፃፀርኩ እናም ስራዬን በአዲሰ መንፈስ ልጀምር ነው ።
አሁንም በጉዞዬ እማራለሁ ። ቢዝነስ እንደዛ ነው ። ትሰራለህ ትወድቃለህ ትነሳለህ ትጓዛለህ ትከስራለህ ታተርፋለህ ትማራለህ .....
@kenesa_Tesfaye