ዘፈን በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ
ክፍል 1
ዘፈን ጥበብ ነውን ?
ዘፈን ጥበብ ነው የሚሉ አሉ። አዎን ጥበብ ነው ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን የተገኘ ጥበብ ነው፤ ቅዱስ ሳይሆን ርኩስ ጥበብ ነው፤ መዳኛ ሳይሆን መጥፊያ ጥበብ ነው፤ የህይወት ሳይሆን የሞት ጥበብ ነው፡፡ ይህን ሳስብ ቅዱስ ጳውሎስ የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው ያለው ትዝ አለኝ
እግዚአብሔር ድምፅ የሰጠን እሱን እንድናመሰግንበት እሱን እንድናወድሰው፣ እሱ የፈቀደላቸውን እሱ ያከበራቸውን ቅዱሳኑን እንድናመሰግንበት ነው እንጂ ለሰው እንድንዘፍን አይደለም። ወይ የእግዚአብሔር ወይም የዓለም ልንሆን ግድ ይለናል፤ ሁለት ጌታ የለም። ዘፈን መዝፈን ኃጢያት ነው
አሁን ባለንበት ዘመን ዘፈን ኃጢያት እንደሆነ፤ የዲያቢሎስ ታላቅ መሳሪያ እንደሆነ፤ ዘፋኝነት ከክርስቶስ ማህበር እንደሚለይ በግልጽ እየተመለከትን ነው። ዘፈን ስራ ነው የሚሉ አሉ አዎን ለዘፋኝ መዝፈን ስራው ነው፤ ለሌባም መስረቅ ስራው ነው፤ ለዝሙት አዳሪዋም ዝሙት ስራዋ ነው፤ ለቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይም መግደል ስራው ነው ግን ደግሞ ኃጢያት ናቸው ስራዬ ነው ብሎ ኃጢያትነቱን ማስቀረት አይቻልም፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን ኃጢያትን ስራ ነው ብለን ሙግት እንገጥማለንን ?
እየመረጥን ብንዘፍንስ ለመልካም የተዘፈኑ ዘፈኖች አሉ የሚሉም ብዙ ናቸው። ዘፈን ሀጥያት ነው በቃ ምንም ጥያቄና መልስ የለውም ቴዲ ስለዘፈነው መዝሙር መሆን አይችልም ስለ ሀገር ሆነ ስለምን.. ስለ ሀገር ጸልዩ እንጁ ዝፈኑ አልተባለም፣ እናት ቢዘፈንላትስ ይላል ደሞ አንዱ፣ እድሜህ እንዲረዝም እናትና አባትህን አክብር ይላል እንጂ ዝፈንላቸው አይልም!! ብዙ ሰው ጥብቅና ለቆመለት ሰው ቃሉ ይህን ይላል