ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል 🙏
***
"በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ
ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፣
እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም ፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ ።
ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ ፥ የተረገመ ይሁን ።
አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን ።
ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን ? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን ?
አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም ።"
ገላ . ፩ ፥ ፮ - ፲፩ ( 1 ፥ 6 - 11 )
ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል🙏
👉እውነት እውነት እልሃለሁ “ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው ቃል
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰበር ዜናዋ
ሊሆን አይችልም!
👉 በቤተልሔም ሲወለድ እጅ መንሻ ይዛ
የተገኘች፣
👉 በሔሮድስ ዘመን ከእናቱና ከአረጋዊው ዮሴፍ ጋር
ሲሰደድ የተቀበለች፡
👉 ኢየሱስ ክርስቶስ በ33 ዓመት ከሦስት ወር እድሜው
ተሰቅሎ ሞቶ፣ ከሙታን ተለይቶ ተነስቶ ባረገ በዓመቱ
በጃንደረባዋ (በማኮስ) አማካኝነት በኩል በስሙ
የተጠመቀች፡ ሐይማኖቷ አድርጋ ታሪኳን የጻፈች፣
👉 ከማንም በፊት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን እምነት
በንጉሥዋ በኢዛና በኩል በዘመነ ካሳቴ ብርሐን
ብሔራዊ ሐይማኖት መሆኑን በይፋ ያወጀች፣
👉 በዓለም ጥንታዊዉን በእጅ የተጻፈ የኢየሱስ ወንጌል
በአባ ገሪማ ገዳም የያዘች፡
👉 በዓመት ከ1825 ጊዜ በላይ የኢየሱስ ወንጌል
እንዲነበብ ሥርዓት ለሠራች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፡-
“ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም፡፡
👉 በ325 ዓ.ም በኒቂያ
👉 በ380 ዓ.ም በኤፌሶን
👉 በ431 ዓ.ም በቆስጠንጥኒያ… ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ከሐዲያንን ሞግተው እንደ ግሪኩ ቃል The word “Orthodox” literally means “true teaching” or “right worship.” or (the right opinion), እንዲሉ ትክክለኛውን አጽንታ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ብላ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው በሚለው አለት ላይ ለተመሰረተች ቤተክርስቲያን “ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው እወጃ ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም፡፡
ይህው የነዚያ የሩቅ ዘመን ጉባዔ ውሳኔ የእለት ፀሎቷ Creed የዘውትር ፀሎት ተብሎ በየቀኑ ቢያንስ ሁለት ጊዜ የሚፀለይ ፅኑ መሰረት ነው። እስኪ ከታች የተያያዘውን ለሁለት ሺህ ዓመታት ዘወትር የሚጸለየውን ፀሎት አንብቡትማ !!!
አሁን ሰምታችሁ አዲስ ለሆነባችሁ ምጥ ለናት እናስተምሩን ተውትና የመሰላችሁን አምልኩ የወደዳችሁትን ተከተሉ፤ ውድድር ፡ ፉክክሩን ተውት አይጠቅማችሁም። በየምክንያቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን አታንሱ።
ሐይማኖት በፉክክር፣ በጥላቻ፣ በግድ፣ በማባበያ አይሆንም። በመንፈስ ቅዱስ በኩል የሆነ ነገር ሁሉ ሰላም፣ ፍቅር፣ በጎ ፈቃድ እንጂ ጠብና ክርክር የለውም።
በጠብና በክርክር፣ በእልህና በቁጣ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ክርክርና ብሽሽቅ "ኢየሱስ ያድናል" የሚል ቃል መወራወር የኢየሱስ አዳኝነት ምስክርነት ከመሰለን ስተናል። ከፖለቲካው የከፋ ውዝግብ ማራገብ በየትኛውም መመዘኛ ጽድቅ አይሆንም።