ddd


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified



Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ለኮከባችን ፀሐይ እናውጣላት

ከመንፈሳዊ ቤተሰብ የተገኘች መንፈሳዊት ወጣት ናት። ዕጩ ሐኪም /ዶር/ ስትኾን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ ዓመት ትምህርት ላይ ትገኛለች። ከጽርሐ ጽዮን ዘተዋሕዶ አባላት መካከል እንደ ባሕር የትዕግስት ስፋት የተሰጠው አባቷ አንዱ ነው።

ዲያቆን ደቅስዮስ ሽብሩ ማኅበሩን በብዙ የኃላፊነት ዘርፍ ያገለገለ መከራን በትዕግስት የማለፍ ጸጋ የተሰጠው ግሩም ነው። በመለከት መጽሔት (ሐመርን ትቀድማለች) ዋና አዘጋጅነትም ረዘም ላለ ጊዜ ያገለገለ ትሑት ሰብእና የተላበሰ ገራገር ነው። በተምሮ ማስተማር ማኅበርም ስማቸው ከሚጠቀሱ ቀደምት ይሰለፋል። ደቅስዮስን ከትምህርተ ወንጌል ሥራ ፈልጎ ማጣት አይታሰብም። በዚህም ሰይጣን በቅናት በደዌ ይደቁሰዋል። እርሱም ከኪሱ በማይለየው ጠበል ይዋጋዋል። ዕጩ ዶር መንበረ የዚህ ጠንካራ ሰው ልጅ ናት።

የታነፀችበት መንገድ የተወደደ ነው። የአንድ እናት የአንድ አባት ልጅ ብቻ አይደለችም። ጽርሐ ጽዮን ስትወለድ ከአንድ ማኅፀን ይሁን እንጅ የሚያምጡ የሚያሳድጉ ብዙ እናቶች እና አባቶች ይኖሩሀል። ጽርሐ ጽዮኖች በመንፈስ ሀብታሞች በሥጋ ድሆች ናቸው። ይህን ያወቀ ሰይጣን በኦሮምያ ቤተክህነት ስም ከተደራጀው ሕገወጥ ቡድን ጀምሮ ብዙ ዓይነት ጥልፍልፍ ፈተና ያመላልስባቸዋል።

መንበረ ይህንን ትውፊታዊ ተጋድሎ ወደቀጣዩ ትውልድ ሊያሸጋግሩ ከሚችሉት ተተኪዎች አንዷ ናት። ግን እንደዋዛ የጀመራት ሕመም ከበድ ያለ ደረጃ ደርሶ ኖሯል። የንጋት ኮከቧ ፀሐይ ያስፈልጋታል።

ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ በመጣ የእግር ሕመም ምክንያት ስትመረመር፤ በእግሯና በዳሌዋ መጋጠሚያ ላይ" ኮንድሮሳርኮማ" የሚባል በሽታ በመገኘቱ፤ የአጥንት ቀዶ ጥገና ሐኪሞች በአስቸኳይ ውጭ ሀገር ሔዳ ቀዶ ጥገናውን እንድታደርግ ወሥነዋል። ለዚህ ሕክምና እና ለ post-surgical care ወጪው $50,000 (ዶላር) ስለኾነ ይህንን ወጪ ለመሸፈን የወገን እርዳታ ያስፈልጋል:: እርሰዎም ይህችን ባለብሩህ ተስፋ ወጣት ለመታደግ፤ የበኩልዎን ዕርዳታ እንዲለግሱ፤ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።

የቻሉትን የሚለግሱበት የGoFundMe መስመር እነሆ።

https://gf.me/u/yj3xr4

የባንክ ሒሳብ አድራሻ

Deksyos Shibru Tsegaye
Commercial Bank of Ethiopia
Burayu Branch
1000038659697
ስልክ፦ +251912049684


በአፍሪካ ትልቁ እና እጅግ ግዙፍ የሆነው መስቀል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቀበና ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም እየተገነባ ይገኛል
*******************************
በአፍሪካ ትልቁ እና እጅግ ግዙፍ የሆነው መስቀል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቀበና ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ይተከላል። 64 ሜትር ከፍታ ያለው የመስቀል ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሚገነባ መሆኑ ተጠቁሟል።

ከዝግግት ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ አእምሮ ምስጋናው እንደገለፁት 64 ሜትር ከፍታ ያለው ግዙፍ መስቀል ሲሆን በውስጡ ፓራናሚክ ሊፍት ይገጠምለታል። በዚህ ግዙፍ መስቀል ላይ 40 ሜትር ከፍታ ላይ መላው አዲስ አበባን የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል። በውስጡም ዓለም አቀፍ የጥናት እና ምርምር ማዕከል እንደሚገነባ የገለፁ ሲሆን ከተራራ ስር በግማሽ ተፈልፍሎ የሚሰራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊ ታሪክ የሚያስቃኝ ግዙፍ ሙዚየምንም እንደሚያጠቃልል ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ጎብኚዎች በቀጥታ እንዲከታተሉት የሚያስችል የአብነት ትምህርት ቤት እና ቤተ መፃህፍትን ያጠቃልላል።

እንደ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ አእምሮ ምስጋናው ገለፃ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆች የሚገነባ እና በሁለት ዓመታት ውሰጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ በኋላ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሆነ ለከተማ ከፍተኛ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ የሚያኖረው መሆኑ ተገልጿል። ለፕሮጀክቱ ጅማሮ የመሰረት ድንጋይ በብፁዕ አቡነ አረጋዊ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ  ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ተቀምጧል።






Forward from: ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
አዲስ ዓመት የፈጣሪ ምህረት ማሳያ!
ቸሩ መድኃኒዓለም ሆይ
አንተ ስላለህ.............. ዛሬን ለማየት በቃን
አንተ ስላለህ............. ህይወት ቆየን
አንተ ስላለህ.............. ሁሉን አለፍን
አንተ ስላለህ............... ከባዱን ተሻገርን
አንተ ስላለህ................ አስጨናቂውን አመለጥን
አንተ ስላለህ............... በምህረትህ እዚህ ደረስን
አንተ ስላለህ............... በዛን በረከትን
አንተ ስላለህ............... ታመን ተፈወስን
አንተ ስላለህ............... ወድቀን ተነሳን
አንተ ስላለህ............... ጠምቶን ጠጣን
አንተ ስላለህ............... ርቦን በላን
አንተ ስላለህ............... ተኝተን ተነሳን
አንተ ስላለህ............... ወተን ገባን
አንተ ስላለህ............... አመሰገንህ
አንተ ስላለህ................ ዛሬን አየን
አንተ ስላለህ ሁሉም ሆነ
የጊዜ መስፈሪያ የሌለህ አንተ ለኛ በቸርነትህ ከአመት አመት አሸጋገርከን ... ከቁጥር ሳታጎል በምህረትህ አቆየኧን.....!!!

በአመቱ ከንተ በላይ ያስከፋነው ያስቀየምነው ያሳዘነው የለም ... አንተ ግን አንተ ነህ !
ምህረትህ የማያልቅ በረከትህ የማይጎል ፍለጋህ የማይነጥፍ ቸር ነህና እዚህ አደረስከን!

ያለፉ ወንድም እህቶቻችን ወገን ዘመዶቻችን ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት አኑርልን! አሜን!

አመቱን የንስሃ፣ የመመለስ፣ የበረከት እና የፀጋ ሙላት አድርግልን! ከሁሉ በላይ አንተን በመፍራት እንድንመላለስ ቅዱስ መንፈስህ ያግዘን! አሜን!

ስብሃት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ! አሃዱ አምላክ አሜን!

🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት ! 🌼🌼🌼


ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @Bible_daily👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
@Yourcommentsbot


ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @Bible_daily👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
@Yourcommentsbot


ጳጉሜን ፪

የጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ሰማእታት ቀን

በተለምዶ ወረዳ 24 ቦሌ ክፍለ ከተማ ጥር 26 ምሽት ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በነበሩ ካህናትና ምእመናን ላይ ድንገት የመጡ የመንግሥት ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ወዲያው 2 ወንድሞቻችን ሲሞቱ 1 ሰው ሆስፒታል ደርሶ አርፏል።

የመቃኞ ቤቱን ፖሊስ አፈራርሶ ቢሔድም በጠንካራ የምእመናንና ካህናት ጥረት 'ሕገ ወጥ ነው' ያለትን ቦታ ፈቃድ በመስጠት በወራት ውስጥ የቅዱስ ገብርኤልና የቅድስት አርሴማን ቤተ ክርስቲያን መገንባት ተችሏል።

ምንም እንኳ በሰማእትነት ከእኛ ብትለዩም በእናንተ ደም ሁሌም ስማችሁ በሚጠራበት ወዳጅ ዘመድ ቤተ ክርስቲያን በምትኮራበት ዘላለማዊ መዝገብ ስማችሁ ተጽፏል።

ዛሬ ላለውም ወጣት ለሃይማኖታችሁ ስትሉ በከፈላችሁት ዋጋ ቤተ ክርስቲያን ታንጻ ሐውልታችሁ በክብር ቆሞ ያሰባችሁ አገልግሎት መፈጸሙ የጽናት ትምህርት ነው። ጳጉሜን ፪ አሰብናችሁ። ክብር ለእናንተ ይሁን እኛንም ያስችለን። አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤልን መሰላችሁ። ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @Bible_daily👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
@Yourcommentsbot


​​ጳጉሜን ለሰሙነ ሰማእታት መታሰቢያ!

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እያገደባደድነው ባለው 2012/ዓ.ም አመት በአክራሪ ፅንፈኞች ቀጥተኛ ተሳትፎና በመንግሥታዊ መዋቅር እገዛ ለማየት የሚዘገንኑና ለመስማት ጆሮን ጭው የሚያደርጉ መከራዎች ተፈራርቀውባታል። ካህናትና ምእመናን ታርደዋል፣ በእሳት ተቃጥለዋል፣ አካላቸው ጎድሏል፣ ንብረታቸው በዘረፋና በእሳት ወድሟል። ይኽ ሁሉ መከራ ተፈራርቆባትና ምእመናን በየሜዳው ተበትነው ሳይቋቋሙና ይህን በደል ያደረሱ ግለሰቦችና ቡድኖች በተገቢው ሁኔታ ያለፍትህ ሳይቀርቡ ዘመን ልንቀይር ነው።

በመሆኑም የቅድስት ቤተክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር ውድ ግኝት የሆነችውን ጳጉሜን "የአቤል ደም ዛሬም ይጮሀል" በሚል መሪ ቃል በዝክረ ሰማእታት በማሳለፍ በቤተ ክርስቲያን ላይ የታወጀውን ጥፋት በማሳወቅና ፍትሕን በመጠየቅ ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከቤተ ክርስቲያንና ከሰማእታት ጎን እንቁም።
በየዕለታቱ የሚከናወኑ መርሐ -ግብሮች
ማሳሰቢያ :+

ለጳጉሜን የተዘጋጀ ፕሮፋይል ፒክቸርን በመቀየርና ከአስተባባሪዎቹ የሚለቀቁ ፅሁፎችንና ሀሽታጎችን # መቀባበል


ጳጉሜ ፩

ጥቅምት 12/2012 ዓ.ም ጃዋር መሐመድ "በመንግሥት ኃይሎች ተከበብኩ" ማለት ሰበብ ከ80 በላይ ኦርቶዶክሳውያን በባሌ ሮቤ፣ ዶዶላ፣ ... በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። በርካታ አብያተ ክርስቲያናትም ተቃጥለዋል ወድመዋል። እኛ ኦርቶዶክሳውያን ሁሌም እናስባቸዋለን። ዛሬም መንግሥት ፍትሕ እንዲሰጠን እንጠይቃለን።

ጳጉሜን ፪

የጥምቀት በአልን ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች የተገደሉትንና ጥር 26 በአዲስ አበባ ከተማ የቅድስት አርሴማን ቤተ ክርስቲያን መቃኞ በማፍረስ ሁለት ወንድሞች ሰማዕታትን የመንግሥት ኃይሎች የገደሉበት ቤተ ክርስቲያንን ያፈረሱበት እለት ነው። የሰማእታቱ ደም በወጣቶች ልብ ሁሌም ሲታሰብ ይኖራል። በደማቸው ቤተ ክርስቲያንን ተክለዋልና። እኛም ቤተ ክርስቲያንን ዋጋ እየከፈልን እንጠብቃለን።
ጳጉሜን ፫
ባሳለፍነው ዓመት በጽንፈኞችና በክርስቲያን ጠል ቡድኖች ሰላባ የሆኑት ሴቶችና ሕጻናት ጭምር ናቸው። ኦርቶዶክሳዊ አይወለድም ተብሎ የጸነሰች እናት በግፍ ሞታለች። የቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ አምሳል አድርገን እናስባቸዋለን።
ጳጉሜን ፬
ሰኔ 23 በኦሮሚያ ክልል በተጠናና በተቀነባበረ ሴራ በስድስት ቦታዎች ምዕመናን በገጀራ ታርደዋል፣ በጩቤ ተወግተዋል፣ አካለ ሥጋቸው መሬት ተጎትቷል። ይኽ አልበቃ ብሎ ንብረታቸው ተዘርፎ ቤታቸው ተቃጥሏል። ሥለ መስቀላቸውና ሃይማኖታቸው በከፈሉት ዋጋ ሰማእታቶቻችን ናቸውና እናስባቸዋለን።
ጳጉሜን ፭ የቃል ኪዳን ቀን

በዚኽ ቀን በቀጣዩ አመት ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ከቤተክርስቲያን ጎን ለመቆም ቃል የሚገባበት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ ለሃይማኖቱ ቸልተኛ ላይሆን በጽናት ለመቆም ቃል የሚገባበት ነው።

#የአቤልደምዛሬምይጮሃል

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot


ጴጥሮሳውያን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መወያያ ግሩፕ
ለየብቻ መሮጥ ይብቃን ያሉት አባላት
-ሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት
-ማኅበረ ቅዱሳን
-የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር
-ፈለገ ባኮስ የሰባክያን እና ዘማርያን ኅብረት
-ሠለስቱ ምዕት የመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት
-የአዕላፋት ድምጽ የካህናት እና ምዕመናን ተናሥዖት ኅብረት
-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት
-የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት
-የአስተዳዳሪዎች ህብረት
https://t.me/thepetrosawiyan


Forward from: ዲጄ ዴቫ DJ DEVA
​​ሰላም ውድ የፌስቡክ ጓደኞቼ ወዳጆቼ ከዚ በታች ፎቶውን የምትመለከቱት ወንድማችን አለምሸት ጉታ ብሩ በቀን 12/12/12 ዓ.ም ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም በሰዓቱ የለበሰው ሰማያዊ ጃኬት እና ሰማያዊ ሱሪ ነው እናም ይህን ወንድማችንን ያየ ወይም ያለበትን የሚያውቅ ከታች በምናስቀምጣቸው ስልክ ቁጥሮች በመደወል ታሳውቁን ዘንድ እንማፀናለን።
0911732099 በቀለ ጉታ
0913299758 ክብረት ጉታ
0921296686 ሶስና ጉታ
00971526417699 ኤልሳ ጉታ
00971521545267 መብራት ጉታ #ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @sew_sewgna✍️
📩 @sewlesewbot📩
👉ሰው ሰውኛ👈




Forward from: Tadele Sisa
ታላቅ የፊርማ ዘመቻ!
ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን። ከኅብረታችን አንዱ ዓላማ ፀረ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ተፅእኖ መፍጠር ነው። ለኦርቶዶክሳውያን መጨፍጨፍ ትልቅ ሚና የተጫወተው omn የተባለው ሚድያ ነው። ይህ ሚድያ አሁንም የጭፍጨፋ አዋጅ በማወጅ ላይ ይገኛል። በመሆኑም ይህንን ሚድያ ለማዘጋት ሥራ ተጀምሯል። የ50,000 ሰዎችን ፊርማም ይፈልጋል። እስካሁን 23,000 የተፈረመ ሲሆን 28,000 ሰው ይቀረናል። አሁን ሁላችንም በሚከተለው ሊንክ እየገባን ፊርማችንን እናኑር። 50,000 ሰው ሲፈርም አንድ አረም ይነቀላል። በርቱ ወገኖቼ። እየፈረማችሁ በዚሁ ሐሳብ ስጡ። እየተወያየን እንፈርም።
https://www.ipetitions.com/petition/banOMN?utm_source=facebook&utm_medium=social&utm_campaign=&loc=thank-you-page


ጴጥሮሳውያን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መወያያ ግሩፕ
ለየብቻ መሮጥ ይብቃን ያሉት አባላት
-ሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት
-ማኅበረ ቅዱሳን
-የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር
-ፈለገ ባኮስ የሰባክያን እና ዘማርያን ኅብረት
-ሠለስቱ ምዕት የመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት
-የአዕላፋት ድምጽ የካህናት እና ምዕመናን ተናሥዖት ኅብረት
-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት
-የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት
-የአስተዳዳሪዎች ህብረት
https://t.me/thepetrosawiyan


​​​​እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ልደት

መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው። እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል።

በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል። በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል።

ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ 24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው። በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል። ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል።

#ዕድገት

የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል። ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል። በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል። በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል። ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል።

#መጠራት

አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ።

የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ። "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን። ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ። ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ። ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም። ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ።

#አገልግሎት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ። በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ። ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት።

1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል።

2ኛው. ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር።

ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ። ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

#ገዳማዊ ሕይወት

ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል። እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል።

እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል።

በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል። በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል።

#ስድስት_ክንፍ

ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል። ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም። በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር።

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ። በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው።

#በዚያም :-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል።

#ተአምራት

የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው።
ሙት አንስተዋል
ድውያንን ፈውሰዋል
አጋንንትን አሳደዋል
እሳትን ጨብጠዋል
በክንፍ በረዋል
ደመናን ዙፋን አድርገዋል።

ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል። በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል። በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

#ዕረፍት

ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል።

ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል። 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot


Forward from: ዲጄ ዴቫ DJ DEVA
​​ኑ !
ለአዲስ ዓመት መባቻ የማይተካውን የሰው ህይወት በሚተካ ደም እናድን !!
"ርቀታችንን ጠብቀን በጥንቃቄ ህይወት እንሰጣለን !"
#የአዲስ_ዓመት_ስጦታ_ለሀገሬ
እሁድ ነሐሴ 24/12/12 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ የደም ባንክ ግሺ(ስታዲየም) እንገናኝ !! #ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @sew_sewgna✍️
📩 @sewlesewbot📩
👉ሰው ሰውኛ👈


Forward from: እለታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ
​​በእውቀት ላይ ሌላ እውቀት በማዕረግ ላይ ሌላ ማዕረግ ።
ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ
ሁለተኛ ፒ ኤች ዲ (PhD) ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
የተዋህዶ እምነታችን አንዱ ፈርጥ
ጸጋውን ያብዛልን መምህራችን !!!
ክርስቲያኖች መምህራችሁን
#CONGRATULATIONS በሉ። መርቁ !!!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @Bible_daily👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
@Yourcommentsbot


#ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)
#አዝ
ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)
#አዝ
ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና
የመቅደስህ ታቦት።"
መዝ ፻፴፩፥፰

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot


​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡

#የእመቤታችን_ትንሣኤና_ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot


#ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
👉 @yemariyam_lejoch👈
✍️ለሀሳብ አስተያየትዎ📩
📩 @yemariyam_lejochbot

20 last posts shown.

1 226

subscribers
Channel statistics