የመዝሙር ርዕስ:- አመልክሃለሁ
እረሳሁት ጥያቄዬን
የከበበኝን በዙሪያዬ
ስቀርብ ፊትህ ለማመስገን
ቀሎ ታየኝ ሁሉም ነገር (2)
ሳላመልክህ ጊዜው አይለፍ
የሚገባህን ምስጋና ሳላቀርብ
ሞልቶ ላይሞላ የምድሩ ነገር
ካልክልኝ አልጎድልም ለጭንቅ ውሎ ማደር ርቋል ከኔ ሰፈር (2)
አመልክሃለው (3)
በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ
ለተራራው ቁመት እያልኩኝ ትልቅ ነህ
ለሸለቆው ጥልቀት እያልኩኝ ሙላት ነህ
ለሞገዱ ብርታት እያልኩኝ ሰላም ነህ
ለጨለማው ርዝመት እያልኩኝ ብርሃን ነህ
አመልክሃለው (3)
በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ
ብዙ ጊዜ ታገልኩ ከቃላቶች ጋራማንንም እንደሚልህአይደለህም ከመታወቅ ታልፋለህ እግዚአብሔርትልቅ(2)
ስላንተ ማንነት በዝርዝር ላወራ
አንሰው ተገኙብኝ ያለኝ ሁሉ አላረካኝ
እንደገባኝ መጠን እንኳን ልገልጽህ አቃተኝ (2)
ትልቅነህ (2) እግዚአብሔር ትልቅ ነህ(4)
ካነበብኩት አይደል ከሰው የሰማሁትያላነሰ ያላጠረ
ዛሬ በዚህ ሰዓት ፊትህ ያመጣሁት
ከነፍሴ ምስጋና ከውስጠቷ የሆነ
አፌን ምልቶ የሚፈስ አዲስ ቅኔ አለ (2)
ከላይ ከላይ ያልሆነ
ለእኔፍቅር ለኢየሱሴ አለኝ ምስጋና ከነፍሴ(2)
አለኝ ምስጋና
#React 🥰🤗♥️🙏
[ᵃˡᵇᵘᵐ ˢᵒⁿᵍ ᵇʸ ᵃˢᵗᵉʳ ᵃᵇᵉᵇᵉ]