ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-17
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ደረቱ ላይ እንደተጋደመች..አይኖቾን ጨፍና ሀሳብ ውስጥ ገባች…በትዝታ ወደሚስኪን ሀገሯ ተመለሰች፡፡እንዴት ለጀመሪያ ጊዜ ከጓዳና ህይወት እራሳቸውን እንዳላቀቁ ነው ትዝ ያላት፡፡
ከ15 ዓመት በፊት /ኢትዬጵያ/አዲስ አበባ/
መንትዬዎቹ ከኩማደሩ ቢሮ እንደወጡ ቀጥታ ተንደርድረው ፊት ለፊት ያገኙት ካፌ ነበር የገቡት፡፡ሁለቱም ምሪንደ አዘው ውስጣቸውን እያቀዘቀዙ ለበርካታ ደቂቃዎች ያለንግግር በየራሳቸው እያወሩ አሳለፉ…
‹‹ወንድሜ ..ተይዘን ቢሆን ኖሮ የሆነ ነገር ያደርጉብኛል ብዬ በጣም ሰግቼ ነበር….››
‹‹እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ? ተይዘን ቢሆን ኖሮኮ ሁለታችንንም ነው የሆነ ነገር የሚያደርጉን..ወፌ ላላ ሁሉ ሊገርፉን ይችሉ ነበር…፡፡››ሲል መለሰላት
‹‹አውቃለሁ…ግን እኔ እችለዋለው..አንተን ግን በጣም ያምሀል››አለችው፡፡ አሁን የሆነ ይመስል በሰንበር የበላለዘ ጀርባውንና የቆሰለ ሰውነቱን በምናቧ እያይች ዝግንን አላት፡፡
‹‹አይ እህቴ ..አንዳንዴ እናቴ የሆንሽ ነው የሚመስለኝ..የ0 ደቂቃ ታላቅ ወንድምሽ መሆኔን ዘነጋሽው እንዴ?ለማንኛውም አሁን ስራችንን በስኬት አጠናቀናል፡፡ብዙ ገንዘብም አግኝተናል፡፡›
‹‹አዎ እሱ ጥሩ ነገር ነው….››
‹‹አዎ ..ጥሩ ነው ደጋግማ እንዲህ አይነት ስራዎችን እያሰራች እንዲህ ብዙ ብር ብትከፍለን በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹እስኪ መጀመሪያ የሰራንበትን ቀሪ ሂሳባችንን ትስጠን››
‹‹አረ ኑሀሚ…አሁንም ያቺን ልጅ ኣታምኚያትም ማለት ነው?››
‹‹ለምን ብዬ አምናታለው…ወላጆቼ ሰው በማመን ምን አተረፉ..ይገባሀል እኔ በዚህ ምድር ላይ ካንት በስተቀር ማንንም ሰው ማመን አልፈልግም››አለችው፡፡
‹‹በቃ አትቆጪ እንዳልሺ ይሁንልሽ..አሁን ሂሳብ ክፈይና እንውጣ፡፡››
‹‹ከብዙ ድፍን ብሮች መካከል አንድ ነጠላ መቶ ብር መዛ የሁለት ለስላሳ ሂሳብ ለአስተናጋጁ ሰጠችው፡፡ሂሳብን ቆረጠና መልሱን አመጣላት፡፡አምስት ብር ቲፕ አስቀመጠችለት..ናኦል ያደረገችውን አየና ፈገግ አለ…፡፡››
‹‹ምን ትገለፍጣለህ..እኛም ወግ ይድረሰን እንጂ፡፡ይሄን ያህል ብር ለሰው በቲፕ መልክ ስንሰጥ እኮ ይሄ የመጀመሪያ ቀን ታሪካችን ነው፡፡››አለችው፡፡
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡ሳናስበው ታሪክ መስራት ጀመርን ማለት ነው?››በገረሜታ ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ..እየሰራን መሰለኝ፡፡››በዚህ ጊዜ ወደበረንዳቸው ተመልሰው ዘወትር የሚቀመጡበት ጥርብ ድንጋይ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠዋል፡፡…ያንን ሁሉ ብር በኪሳቸው አጭቀው ይዘው ብዙ ብዙ ቦታ ሄደው ዘና ማለት እየቻሉ እዛ መቀመጥ አልነበረባቸውም፡፡ለምሳሌ ፊልም ቤት ገብተው ፊልም ማየት የሁለቱም ምርጫ ነበር፡፡ካልሆነም እናትና አባታችው መቃብር ጋር ሔደው ዛሬ የሰሩትን አስደናቂ ጀብዱም ሊነግሯቸው ይችሉ ነበር፤ግን አላደረጉትም ፡፡ ምክንያታቸው ምስራቅ እነሱን ፍለጋ ወደቋሚ ቦታቸው ስትመጣ እንዳታጣቸው ነው፡፡ግን በቀላሉ የምስራቅ ዱካ ሊሰማ አልቻለም፡፡ቦታው ላይ ስድስት ሰዓት የተቀመጡ እስከስምንት ሰዓት አልተንቀሳቀሱም ነበር፡፡
‹‹ወንድሜ ይህቺ ልጅ አብርታናለች መሰለኝ፡፡››
ኑሀሚ የተናገረችው እሱም በውስጡ እያሰላለስለ የነበረው ነገር ስለነበረ ለስለስ ባለ ቃል‹‹ለምን እንደዛ አልሺ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ይሄው እንደምታያት ቀረቻ….ጉዳዮ ከተፈፀመላት ለምን ብላ መጥታ ሁለት ሺ ብር ሙሉ ትሰጠናለች?››
‹‹ግድ የለሽም እንደዛ አታደርግም…ትንሽ እንጠብቃት፡፡››
‹‹አይ እኔ ደግሞ የምታደርገው ነው የሚመስለኝ…ጥዋት ሁለት ሺ ብር ብላን አልነበር..አይሆንም አራት አድርጊው ስላት…..አይሆንም ባይሆን ሶስት እንኳን ይሁን አላለችንም፡፡በአንዴ ነው የተስማማችው፡፡በወቅቱ እንደውም በውስጤ ምነው ስድስት ሺ ወይ ስምንት ሺ ባልኳት እያልኩ ነበር፡፡ግን ይሄው እሷ እኛን ለማበረታታት እና ስራዋን በሞራል እንድንሰራላት እንጂ እንደማትከፍለን ታውቅ ነበር፡፡
‹‹እና ተመልሳ አትመጣም እያልሺኝ ነው?››
‹‹አዎ እንደዛ ነበር ያሰብኩት ..ግን ተሳስቼያለሁ መሰለኝ››አለችው፡፡
ናኦል በእህቱ ንግግር ግራ ተጋባ..‹‹መቃዠት ጀመረች እንዴ?›› ሲል በውስጡ አልጎመጎመ፡፡
‹‹እህቴ አልገባኝም፡፡››
‹‹ያቹት መጣችልህ..››አለችው ከመንገድ ማዶ እየጠቆመችው፡፡
ናኦል በደስታ ፈንጥዞ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ…‹‹እውነትሽን ነው እህቴ? የታለች?››
ሱሪውን ያዘችና ወደታች እየጎተተች‹‹አረ ሼም ነው..ቁጭ በል፡፡ምንድነው እንዲህ መንሰፍሰፍ?እናትህ መሰለችህ እንዴ?››
ተመልሶ ቁጭ አለና.‹‹ነግሬሽ ነበር እኮ..እሷ እንደሌላው ሰው አይደለችም፡፡አትቀርም ብዬሽ ነበር…፡፡››
‹‹በቃ አፍህን ዝጋ እየቀረበች ነው፡፡››
ዝም አለና ሁለቱም አይኖቻቸውን እያቁለጨለጩ ስራቸው እስክትደርስ ይጠብቋት ነበር፡፡ምስራቅ እንደደረሰች በዝምታ መሀከላቸው ሰቅስቃ ገብታ ተቀመጠችና….‹‹እሺ ጩጬዎቹ እንዴት ሆነላችው?››ስትል ምንም ነገር እደማታውቅ ሆና ትጠይቃቸው ጀመር፡፡
‹‹አድርገናል…እንዳልሺን አስቀምጠናል፡፡››ሊያብራራላት ሞከረ፡፡
ኑሀሚ ኮስተር እንዳለች….‹‹ቀሪውን ብር ይዘሽ መተሻል››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹እህቴ ብሩ የት ይሄድብናል..?መጀመሪያ ስራውን በትክክል መስራታችንን ታረጋግጥና ቀስ ብላ ትሰጠናለች፡፡››በልምምጥ ሊያረጋጋት ሞከረ፡፡
‹‹አታርፍም እንዴ…በትክክል እንደሰራነውማ ገና ድሮ ነው ያወቀችው፡፡››በኑሀሚ ንግግር ምስራቅም ሆነች ወንድሟ ደነገጡ፡፡ናኦል..እነሱ ካልነገሯት እንዴት ታውቃለች ብላ ልታስብ እንደቻለች ስላልገባው ነው..ምስራቅ የደነገጠችው በልጅነቷ የአእምሮ ስልነት ስለተደመመች ነው፡፡
‹‹ማወቋን እንዴት አወቅሽ?››ሲል ጠየቀት፡፡
‹‹ነግረሺናል እኮ ..ዕቃውን እዛ ያስቀመጥነው አንቺ እዚ ሆነሽ ዛፓው የሚሰራውን ሁሉ ለመከታተል ነው፡፡አስቀምጠን እንደወጣን አንቺ ሰውዬውን መከታተል ጀምረሻል፡፡ያ ባይሆን ኖሮ ስትመጬ ፊትሽ ላይ ቁጣና ንዴት ይታይ ነበር፤አሁን ግን እርካታና ደስታ ነው የማነበው፡፡››አብራራችላት፡፡
ምስራቅ ኪሶ ገባችና የታጠፈ ብር በማውጣት ..‹‹ይሄው ሶስት ሺ ብር..አንድ ሺ ብሩ እንዳልሺው ስላስደሰታችሁኝ ቦነስ ነው፡፡››አለችና እጇ ላይ አስቀምጣላት…ከተቀመጠችበት ተነሳችና ናኦልን በፍቅር ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ቀጥ ብላ ተለይታቸው ሄደች፡፡
‹‹ምስራቅ…መች ነው የምትመጪው?››ጮክ ብሎ ጠየቃት፡፡
‹‹እዛ ቆቆር ቤት ወስደህ ቁርስ ምትጋብዘኝ ከሆነ ነገ ጥዋት እመጣለው፡፡››አለችው፡፡ ደስ ብሎት‹‹እጋብዝሻለሁ..እንዳትቀሪ፡፡››አላት ፡፡
‹‹እሺ አልቀርም፡፡››አለችውና ከእይታው ተሰወረች፡፡
ምስራቅን በአይኖቹ እስከመጨረሻው ሸኝቶ ወደ እህቱ ሲዞር የሰጠቻትን ብር እየቆጠረች ነበር፡፡በትዝብትና በገረሜታ ይከታተላት ጀመር፡፡
ጨረሰችና‹‹አዎ ትክክል ነች..ሶስት ሺ ብር ነው፡፡››