ከረጅም ግዜ በኃላ ፍሬንዴን አገኘሁት። ፈታ ያለ ነው። ሳቅ ያበዛል ሰላምታ ሲሰጥ እቅፍ አደርጎ ነው።
ያቆላምጣል ...
ሲስቅ አይኑ፥ ጥርሱ፥ ጉንጩ ቅይር ይላል። እሱን ማግኘት Energy ይሰጣል ።
ከዓመት በኋላ ሳገኘው '...ባክህ ፋዘርም ብራዘርም ደየሙብኝ.. በተከታታይ...' አለ።...ትክ ብዬ...በመደናገጥ አየሁት።
'ቤትም ሱቅም ወረስኩ ... በልጅነቴ ኪራይ ሰብሳቢ ሆንኩልህ...' ብሎ ሌላ ሳቅ ለቀቀ።
እንዳንድ ሰው ቀለል የሚያደርገው ነገር አገራረሙ ..
ሌላ ቀን ሌላ ቦታ እየሄድን...
"የሞተ ሰው በአይንህ አይተህ ታውቃለህ?" አልኩት።
'አባቴ ድንገት ታሞ ተሯሩጠን ከወንድሜ ጋ ሆስፒታል ወሰድነው አልቆየም ነርሷ ሞተ አለቺኝ እንዲ አትበይ ተይ ተይ ተይ አልኳት...
ያልነገርኩት ነገር አለ ተይ አልኳት...ተይ ደስ የሚለውን በልደቴ ቀን እነግረዋለሁ ብዬ ያቆየሁት ነገር አለ ተይ ሞተ አትበይ አልኳት...'
ያለቺው ነበር የሆነው።
'እኔና ከወንድሜ ከነርሷ ጋር በጋራ ሆነን ገነዝነው።'
'እምባ እየከለለኝ እጄ አልታዘዝ እያለ እኔ ነኝ ለቀብር ያበጃጀሁት...
ልጨምርልህ...?!
ፈገግታው በእንባ ተቀይሯል፤ ድምፁ ሳግ አለው፤ ዐይኑ እምባ ተሞልቷል...
'አባቴ በሞተ በሰባት ወር ወንድሜ እጄ ላይ ነው የምተው። ወደቀ ተብዬ ስጠራ ስበር ደረስኩ ያኔ ነብሱ አልወጣችም ነበር እንዳቀፍኩት፥ እየጠራሁት፥ አይዞህ እያልኩት፥ ውኃ አምጡ ላፍስስለት እያልኩ እጄ ላይ ሞተ...።'
ከእማማ እልፍኝ ጋ ሆኜ ገነዝኩት...
'ታላቄን የሚቆረቆርልኝን ገነዝኩት። ዐይኑ፥ ገላው፥ በድን ሲሆን አየሁ ...አብሮ አደጌን አንድ ወንድሜን ቀበርኩት...'
'ከዓለም ተኳረፍኩ። ጠዋት ማታ ዊድ ነፋሁ፤ ወንድሜ አግብቼ እኖርበታለሁ ያለው ቤት፤ አባቴ የሚጦርበት ሱቅ የኔ ሆነ። መጠጥ ውስጥ ተደበኩኝ በዊድ ተከለልኩ።
'ስጋችን እንዴት እንዳስጠላኝ፤ ሰውነት እንዴት እንደደበረኝ፤ ነገ እንዴት እንደቀፈፈኝ፤ ዕቅዴን እንዴት እንደናኩት!!'
.
.
ሳቃችን የከለለው ሃዘን ብዛት !!!
©Adhanom Mitiku