አባቴ ካጠገቡ የማትጠፋ ራዲዮ ነበረችው። ኹለት ስፒከር አላት ካሴትም ታጫውታለች...
ፀሐይ በራኺን አስሬ ይሰማታል። አክስቴ ትመስለኝ ነበር፤ ድምጿ እኛ ቤት አይጠፋም ስትዘፍን እኩል እላለሁ ከሙዚቃው ጋር...
"መጀመርታ ፍቅሪ
ኣብ መን ተጀመረ
ኣዳምን ሔዋንን
አለም ምስተፈጥረ
ኣነ ከይፈለጥኩ
አብ ልበይ ሐደረ
እንታይ እሞ ክገብር
ዕድለይ ካብ ኮነ አይ..አይይ*
አባቴ ወታደር ነበር። ጠይም ነው መከፋቱ ፊቱ ላይ ብዙ አይታይም፤ ማጣቱ በየምክንያቱ አንደበቱ ላይ አይንፀባረቅም ....ዝምም ይላል
ረጋ ያለ ነው ።
ጥርሱን ሳያሳይ ነው ደስ ብሎኛል ፈገግታ ፈገግ የሚለው፤ ተገርሜያለሁ ፈገግታ ፈገግ የሚለው ተበድያለሁ ፈገግታ ፈገግ የሚለው አጠገቤ ሲሆን እረጋጋለሁ።
ሰሞኑን ሰውነቴ እንደከሳ፤ ፊቴ ማዘን እንደታከከው፤ ድብርት ነገር እንዳንጃበበብኝ አወቀ። አባትም አይደል? ንብረቱም አይደለሁ? ዋጋ ከፍሎብኝም የለ?
ፊቴን አይቶ "ደህና ነህ ህሉፌ ...?" አለኝ።
'እ ...ትንሽ ደከመኝ...
አሻግሬ ማየት እያቃተኝ... ቶሎ ቶሎ እጅ እየሰጠው ..." አልኩት።
ረጅም ሰዓት ዝም አለ ...
"ታስታውሳለህ በረሃ እያለሁ የምፅፍላችሁ ደብዳቤ፤ በርቱልኝ፥ ምን ጎደላችሁ፥ እወዳችኋላሁ፥ በቅርብ እደውልላችዋለሁ፥ እመጣለሁ፥ ዓይነት ይዘት ያለው ፅሁፍ ?! ።"
"ባሩድ እየሸተተኝ ነበር፥ አብሬው የዋልኩት ጓደኛዬ ሞቶብኝ፥ ፍንጣሪ ጥንት መ'ቶኝ፣ ጠላት ሊፈጀን እያቀደብን፣ ጀኔራላችን ምሽግ ሰብራችሁ ግቡ ሊለን እንደሚችል እያወቅን፥ የተቀበረ ቦንብ ልንረግጥ እንደምችል እያወኩ፥ ከአውሮፕላን የተወረወረ ፈንጅ ሊያወድመን እንሚችል እያወኩ፥ ነበር...አሻግሬ ተስፋ የማየው..."
ፋታ ወስዶ ቀጠለ...
"ልጆቼን እንደማገኛቸው፥ አባት እንደምሆንላቸው፥ ሚስቴን ዳግም እንደማገኛት ፤ቤተክርስትያን እንደምሳለም የፈንጂ ድምፅ ሳልሰማ እለት እለት የወደቀ ሬሳ ሳልሻገር እንደምኖር ተስፋ አደርግ ነበር ...
ስለመግደል የሚታቀድበት ስፍራ ላለመሞት የሚዘየድበት ቦታ አንድ ቀን እንደማልኖር አምን ነበር ...!
ተስፋን ሙጥኝ ብዬ ነው ዛሬን ያየሁት ። ያጋጠመኝን መውደቅ እና ሃዘን ህመም ችላ ብዬ ነው ያን በርሀ የተሻገርኩት !!
አጆኻ ዝወደይ ..
ሁሉም ሰው መስቀል አለው ልዩነቱ አይነቱ እና አሸካከሙ ነው !!"