አለመሳቅ እኮ ይቻላል...
-----------------------
አለመሳቅ እኮ ይቻላል -
አለማልቀስ ነው ጭንቁ፣
የመንፈስን እንጉርጉሮ -
በመንፈስ እምባ ማመቁ፣
ውስጥ ውስጡን እየደሙ -
በቀቢፀ ተስፋ መድቀቁ፣
ለተስለመለመች እውነት -
የደም ደብዳቤ ማርቀቁ፣
በቅሬታ ሰደድ እሳት -
ህዋሳትን መጨፍለቁ፣
አለመሳቅ እኮ ይቻላል -
አለማልቀስ ነው ጭንቁ።
- ደበበ ሰይፉ
አለመሳቅ እኮ ይቻላል...
-----------------------
- ደበበ ሰይፉ