ተናጋ…አቶ ኃይለ ልኡል ከተቀመጡበት ተነስተው ልጃቸውን በማቀፍ ልክ እንደባሌት ዳንስ በአየር ላይ ነው ያሽከረከሯት…..ለሊሴ እና ሰሎሞን ትዕይንቱን በተመስጦ እየተከታተሉ ነው፡፡
ይሄንን ትዕይንት ለሚከታተል ሰው ልጃቸው ለአለፈው አንድ ወር ብቻ ተለይታቸው የቆየች ሳይሆን በአራስነቷ ተሰርቃባቸው ከሀያ አመት በኃላ በተአምር የተገኘች አይነት ነው የሚመስለው፡፡
በነጋታው አምስቱም በቻርተር አውሮፕላን ተጭነው ወደአዲስ አበባ ተመሱ፡፡በፀሎት ግን ቀጥታ ወደቤቷ ሳይሆን ወደ ለሊሴ ቤት ነው መሄድ የፈለገችው..ውሳኔዋን ስትነግራቸው ሁለቱም ወላጆቾ ክፉኛ ተቃውመው ነበር፡፡
‹‹አባዬ እማዬ.ስሙኝ…እኔን ወደቤት ለመመለስ ባደረጋችሁት ነገር በጣም ኮርቼባችኃላው በጣም እንደምትወዱኝም አውቄለው…ግን አሁን መጀመሪያ ያበላሸሁትን ነገር ማስተካከል አለብኝ…ከአሁን ወዲህ እንድታውቁት ምፍልገው እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እነሱም ወላጆቼ ናቸው….ከአሁን ወዲያ ብቸኛ ሳልሆን ወንድምና እህት አለኝ…ቦሌ ያለው የተንጣለለ ቪላ ብቻ ሳይሆን አቃቂ ያለውም ደሳሳ ቤት ቤቴ ነው፡፡እና የግድ አሁን ከለሊሴ ጋር ወደቤት መሄድ አለብኝ…ከዛ እስከአሁን የዋሸዋቸውን ናግሬ ይቅርታ ካገኘሁ በኃላ እመጣለሁ››
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው የምትነግሪያቸው…?.››
‹‹አላውቅም… ብቻ የሆነ መንገድ ፈልጋለው››
‹‹ካልሽ እሺ ልጄ….ግን ታውቂያላሽ ከአምስት ቀን በኃላ ቤት ድግስ አለ…ንቅለ ተከላ የተደረገልሽ ቀን ነው..ያው እንደተለመደው ዘንድሮም እየተደገሰ ነው፡፡
‹‹አዎ አውቃለው…..የሚገርመው እነዛኞቹም ቤተሰቦቼ ጋር ድግስ አለ….በዛው በተመሳሳይ ቀን የሙት አመት መታሰቢያ ድግስ አለባቸው…የማ ለእኔ ልቧዋን የሰጠችኝ የበሬዱ የሙት መታሰቢያ….››ስትናገር የሚረግፈውን እንባዋን መገደብ አልቻለችም….እናትና አባቷም በሰሙት ነገር ሽምቅቅ ነው ያሉት….፡፡
‹‹እና በእለቱ የትኛውን ድግስ እንዳምሳተፍ ግራ ገብቶኛል..ግን አታስቡ ጥዋት እዚህ ቆይና ከሰዓት እናንተ ጋር መጥቼ የእኔን የምስጋና በአል አከብራለው….አዎ እንደዛ አደርጋለው››
በቃ የእኔ ቆንጆ …እንደሚሆን እንደርጋለን..አንቺ ምንም አትጨነቂ…አሁን ሹፌሩ እናንተን ቤታቸው ያድርሳችሁ እኛ ከሰለሞን ጋር በራይድ እንሄዳለን፡፡››አሉ አቶ ኃይልኡል
‹‹አረ አባዬ ግድ የለም እኛ በራይድ ብንሄድ ይሻላል፡፡››ለሊሴና በሬዱ ፈጠን ብለው አካባቢው ወደአለ ራይዱ ሄዱና .ውስጥ ገብተው ወደአቃቂ ሲያመሩ ሰለሞን እና ባልና ሚስቶቹን ሊቀበላቸው በመጣ መኪና ቦሌ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሄዱ፡

ይቀጥላል....
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
ከመጽሐፍት መንደር
ከመጽሐፍት መንደር
ከመጽሐፍት መንደር
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️