‹‹ከመቀመጫዋ ተነሳችና እላዩ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመችው‹‹….የእኔ ወንድም
…..በጣም ነው የምወድህ……››አለችው
‹‹እኔም እህቴ በጣም ወድሻለው…አሁን እራት እየቀረበ ነው መሰለኝ ወደቤት እንግባ…››
‹‹እሺ እንግባ››ተባባሉና ተያይዘው ወደቤት በመግባት ከቀረው ቤተሰቡ ጋር ተቀላቀሉ፡፡
//
አቶ ለሜቻና ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ሙሉ ትኩረቱ የበሬዱ የሶስተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ ላይ ነው፡፡ይሄ ባለፈው ሁለት አመት በተመሳሳይ የመታሰቢያ ድግስ የተደገሰ ቢሆንም የዘንድሮ ግን በተለየ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶታል ፡፡የዚህም ምክንያት በቤተሰቡ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ መንገድ በፀሎት የምትባል ልጅ ስለተጨመረችና ከዛም ተያይዞ ከሞላ ጎደል የቤተሰቡ የገንዘብ ችግር ስለተሻሻለ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው ከፍ ባለ ሁኔታ ለመደገስና በሟቾ ስም በርከት ያሉ ችግረኞችን በማብላት ነፍስ ይማር በማሰኘት የተወሰነ የመንፈስ እረካታና የአእምሮ መረጋጋት ለማግኘት ጠንክረው በጥሩ ሞራል እየደገሱ ነው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ ኃይለልኡል ቤት በአይነቱ ለየት ያለ ድብልልቅ ያለ ድግስ እየተደገሰ ነው፡፡የእነሱ ምክንያት ደግሞ ሚያዚያ 20 ቀን የልጃቸው በፀሎት የልብ ንቅለተከላ ያደረገችበትና ሁለተኛ የመኖር እድል ያገኘችበት ስለሆነ ያንን ቀን በፌሽታና በምስጋና የማሳለፍ አላማ ያለው ነው፡፡ይሄንን ድግስ ያለፉትን ሁለት አመታት አድርገውታል፡፡ የዘንድሮው ግን በአይነትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ይሄም ዘንድሮ ሁኔታዎች የተለዩ
ስለሆኑ ነው፡፡ከቤታቸውም ከፊታቸውም የተሰወረችው የልጃቸው በፀሎት ከወር በኃላ ወደቤቷ ምትመለስበት ቀን ይሆናል የሚል ጉጉት ስላላቸው ልጃቸውን እጥፍ ድርብ በሆነ ፌሽታ ለመቀበል ያደረጉት ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ሌላ የተለየ ምክንያት አላቸው ፡፡ባልና ሚስቶቹ ለአመታት ከገቡበት አስጠሊታ ግንኙነት እና የእርስ በርስ ጥላቻ ተገላግለው. ቀሪ ህይወታቸውን በመከባበር እና በፍቅር ለማሳለፍ ወስነውና ተስማምተው ቀሪ እንደአዲስ ለመጀመር የወሰኑበት ወቅት ስለሆነ ለእነሱም እንደ ዳግማዊ ሰርግ ነው…ለዛ ነው የተለየና እንከን አልባ ድግስ እንዲሆን እየጣሩ ያሉት…ያው እንደተለመደው የድግሱን ቅንጅት በሀላፊነት የወሰዱት ፕሮፌሽናል ባለሞያዎች ናቸው፡፡
የጭንቁ ቀን ደርሶል ፡፡አቶ ለሜቻና ወይዘሮ እልፌ ከሌሎች ጎረቤቶች ጋር በለሊት ነው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው ቅዳሴ የገቡት…በጸሎትን ጨምሮ ሌሎቹ ልጆች ግን ወደ ቤተክርስቲያን የሚወሰደውን ምግብና መጠጥ ሲያዘጋጁ ከቆዩ በኃላ አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ዳቦ፤ እንጃራና ጠላውን በፒካፕ መኪና እስጭነው ቤተክርስቲያን በመውሰድ ለቄሶቹ የተዘጋጀውን ወደሰንበቴ ቤት አስገብተው ሌላውን ውጭ አስቀምጠው ቅዳሴው እስኪገባደድ መጠበቅ ጀመሩ ፡፡ልክ ቅዳሴው ተጠናቆ ሁሉም እንደወጣ አቶ ለሜቻና ወይዘሮ እልፌ ከቄሶቹ ጋር ወደሰንበቴ ቤት ቄሶቹንና ሌሎች ምዕመናንን ለማሰተናገድ ሲገቡ፡፡ በፀሎትና እና ለሊሴ ደግሞ ከሌሎች የሰፈር ወጣቶች ጋር በመሆን ቤተክርስቲያኑ የውጭ አጥር ጋር ተኮልኩለው ለሚገኙ የእኔ ቢጤዎችና፤ ምፅዋት ጠያቂዎች አንድ እንጀራ በወጥ ፤አንድ ጉማጅ ዳቦና አንድ ሀይ ላንድ ጠላ ለእያንዳንዱ እያደሉና ነፍስ ይማር እያስባሉ ካጠናቀቁ በኃላ ዕቃቸውን ሰብስበው እነአቶ ለሜቻ ከሰንበቴ ቤት እስኪወጡ መጠበቅ ጀመሩ…ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀ በኃላ ቤተሰቡ ወደቤታቸው ከመመለሳቸው በፊት ቀጥታ ተያይዘው ወደበሬዱ መቃብር ነው የሄዱት፡፡የእሷ ምስል ያለበት ጥቁር ቲሸርት የለበሱት አስራ ምናምን ሰዎች የሀውልቱን ዙሪያ ገባ ከበው በዝምታ ሲፀልዩና አንዳንዱም ሲያነባ ከቀዩ በኃላ ሁሉም ቀስ በቀስ ስፍራውን እየለቀቁ ሄዱ…በመጨረሻ የቀሩት በፀሎት አቶ ለሜቻና ወ.ሮ እልፍነሽ ነበሩ፡፡
በፀሎት ይሄንን የልጅቷን ሀውልት ስታይ በጣም ትልቅ የሆነ ሀዘን ነው የተሰማት…‹‹በእሷ ምትክ..እኔ ነበርኩ እዚህ ስፍራ ከዚህ ሀውልት ስር መተኛት የሚገባኝ››ብላ ስታስበው እራሱ ዝግንን አላት…ልክ እንደሁል ጊዜውም የሌላን ሰው ህይወት ሰርቃ እየኖረች እንዳለች አይነት ስሜት ነው እተሰማት ያለው….የሚቀፍ አይነት ስሜት…›
አቶ ለሜቻ በዝምታ ሲያስተውሏት ስለቆዩ ያመማት መሰላቸው…‹‹ለማታውቃት ልጅ ይሄን ያህል ሀዘን ከየት የመጣ ነው?››በውስጣቸው ያብሰሰሉት ሀሳብ ነበር፡፡ በዝምታ ወደእሷ መጥተው ትከሻዋን በመያዝ…‹‹ልጄ በቃ እንሂድ ይበቃል››ሲሏት ከገባችበት ጥልቅ የመደንዘዝ ስሜት ባነነችና ቀና ብላ አየቻቸው…ትከሻዋን አቅፈው በፍቅር እየተመለከቷት ነው፡፡በሶስት ሜትር ርቀት ፈንጠር ብለው ወ.ሮ እልፍነሽ እያነቡ ይታዬታል…የአቶ ለሜቻን እጅ ያዘችና ‹‹አባዬ ና..››ብላ ወስዳ ከባለቤታቸው ጎን አቆመቻቸውና…ሁለቱም እግር ስር ድፍት ብላ አንድ አንድ እግራቸውን በመያዝ…‹‹አባዬ እማዬ እኔን ይቅር በሉኝ….በበሬዱ ይዣችኃለው ይቅር በሉኝ….ይቅር ካላላችሁኝ መኖር አልችልም….የእውነቴን ነው የምላችሁ ይቅርታችሁን ካላገኘው ሞታለው፡፡››ስትል ሁለቱም በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ…ምንም እየገባቸው አይደለም….‹‹ምን አጥፍታ ነው…?ምንስ ብታጠፋ ይቅርታ መጠየቂያው ቦታና ጊዜው ትክክል ነው?፡፡››በውስጣቸው የተፈጠረ ጥያቄ ነበር…ሁለቱም ግራና ቀኝ ትከሻዋን ይዘዘው ቀና ሊያደርጎት ሞከሩ ..ግን እልቻሉም፡፡
‹‹ይቅርታ ካላደረጋችሁልኝ አልነሳም››
‹‹ምን አጥፍተሸ ነው? ምንም አልገባንም እኮ››አቶ ለሜቻ ጠየቋት፡፡
‹‹አጭበርብሬችኃለው ..ዋሽቼያችኃለው..እኔ እናንተ ጋር የመጣሁት ከእንጀራ አባቴ ጠፍቼ አይደለም….››
‹‹እና ምን ሆነሽ ነው?፡፡››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠየቁ፡፡
‹‹እኔ ማለት …የልጃችሁን ልብ በውስጤ ተሸክሜ የምዞር..በእሷ ምክንያት እየተነፈስኩ ያለው ልጅ ነኝ…..፡፡››
ሁለቱም የሚሰሙትን ለማመን አልቻሉም ..አቶ ለሜቻ ቀስ ብለው ትከሻዋን ይዘው አስነሷት…ፊቷን የተሻፋፈነችበትን ሻርፕ ቀስ ብለው ከላዮ ገፈፉና ጣሉት.. ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ፊቷን ተመለከቱት‹‹አዎ እራሷ ነች››ትከሻዋን ያዙና ደረታቸው ላይ ለጠፏት…ግንባሯን፤ ጉንጮን፤ ፀጉሯን እየደጋገሙ ሳሟት‹‹….ልጄ አዎ አውቄው ነበር..አንቺ ወደቤቴ ያለምክንያት እንዳልመጣሽ ታውቆኝ ነበር….ከዛሬ ነገ ጥላኝ ትሄዳለች በሚል ስጋት ስሳቀቅ ነበር..አሁን ግን የራሴው ልጅ ነሽ የትም አትሄጂም..አዎ የራሴው ልጅ ነሽ››ተንሰፈሰፉላት….ፍፁም ያልጠበቀችውን ምላሽ ነው ያገኘችው፡፡
‹‹አዎ አባዬ ያንተው ልጅ ነኝ…ዘላለም ካአንተ መለየት አልችልም…እማዬ እኔ ልጅሽ ነኝ››ሶስቱም አንድ ላይ አርስ በርስ ተቃቅፈው ለበርካታ ደቂቃ ተላቀሱ ..በመከራ ነበር አካባቢውን የለቀቁት…ሁሉም የቤተክርስቲያኑ በራፍ ላይ ተሰብስበው እየጠበቋቸው ነበር….ግን በፊት ከነበሩት በተጨማሪ የበፀሎት እናትና አባት ልዩ አይነት ባስ መኪና አጠገብ ቆመው በራፍ ላይ ሲጠብቋቸው ነበር..ይሄ ደግሞ እነአቶ ለሜቻን ብቻ ሳይሆን በፀሎትንም ጭምር ነበር ያስደነቃት…እርስ በርስ ተቀራርበው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ሁሉም በመኪና ውስጥ እንዲገቡ ተደረገ…በመኪና ውስጥ ጠቅላላ 25 የሚሆኑ ሰዎች ገቡ…ሹፌሩ መኪናውን ወደእነ አቶ ለሜቻ ቤት አቅጣጫ መንዳት ጀመረ…ቤታቸው ለመድረስ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው ግን ወደግራ ተጠመዘዘና አንድ ግቢው ውስጥ ገባ..ሁሉም ግራ ተጋባ….አቶ ኃይለልኡል መኪናው እንደቆመ በራፈ ከመከፈቱ በፊት ከተቀመጡበት ተነሱና መናገር ጀመሩ‹‹ ..ይቅርታ የማታውቁኝ ካላችሁ ኃይለልኡል እባላለሁ…የበፀሎት አባት ነኝ…በዛሬው ቀን በደም የተጣመሩ ሁለት ቤተሰቦች