እዚህ ይገኛሉ ..የእኛና የአቶ ለሜቻ ቤተሰብ፡፡ይሄ ሁለት ቤተሰብ የተሳሰረው ዛሬ አብራን በሌለችው በበሬዱና አጠገባችን ባለችው በፀሎት ነው፡፡የእኔ ልጅ ዛሬ በህይወት ያለችው ከበሬዱ በተሰጣት ልብ ነው፡፡እዚህ እነአቶ ለሜቻ ቤት ለሟች ልጃቸው የሙት አመት መታሰቢያ ሲከበር በእኛ ቤት ግን ለልጃችን ንቅለ-ተከላ ተደርጎላት ዳግም የመኖር እድል ስላገኘች ድል ያለ የምስጋና ድግስ እናዘጋጅ ነበር ..ዘንድሮ ግን በፀሎት ውሳኔ እንደዛ ማድረግ አልቻልንም…እዚህ ግቢ አንድ ላይ መታሰቢያውንም ምስጋናውንም አብረን እንድናከብር ወስነናል..አሁን ሁላችንም ወርደን የተዘጋጀውን ዝግጅት እንታደም፡፡››የሚል ንግግር ካሰሙ በኃላ በራፉ ተከፈተ …
ዛሬ እየሆነ ያለው ነገር በጠቅላላ ምንም ያልገባቸው አቶ ለሜቻና ወ.ሮ እልፍነሽ አቶ ኃይለልኡልንና ባለቤታቸውን ተከትለው ከባስ ወረዱ፡፡ይሄንን ሰፈራ የሚገኘው በገዛ ቀበሌያቸውና በሰፈራቸው ስለሆነ በደንብ ያውቁታል፡፡ግቢው ንብረትነቱ የቀበሌው ሲሆን ባለ5 ሺ ካሬ ግዙፍ ጊቢ ነው…ከመኪና ወርደው ሲመለከቱ ግቢው በሰዎች ታጭቆል ፡፡ ሰዎቹ ደግሞ አብዛኛው ጎዳና ተዳዳሪዎች፤የኔ ቢጤዎች የደከሙና የተጎዱ አቅመ ደካሞች…..ለአይን እንኳን ተቆጥሮ የማያልቅ የእንጀራ ክምር ..በበርሜል የተደረደረ ልዩ ልዩ የወጥ አይነት…ራቅ ብሎ ደግሞ በተንጠልጣይ ብረት ላይ የተደረደረ ጥሬ ስጋ እንደተራራ የተቆለለ የታሸገ ውሀ……
በሌላ ጎን ከአዳራሹ ፊት ለፊት ግዙፍ ፖስተር ይታያል…በፖስተሩ ላይ በቀኝ የበሬዱ ፎቶ በስተግራ ደግሞ የበፀሎት ፎቶ መሀከል ላይ የበሬዱ በፀሎት የምገባ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ይላል፡፡ብዛት ያላቸው ጋዜጠኛች ከወዲህ ወዲያ እየተዘዋወሩ ፎቶ ያነሳሉ ኢንተርቪው ያደርጋሉ፡፡
ማታ በሁለት ሰዓት ዜና ላይ በኢትዮጴያ ቴሌቭዝን የቀረበው ዜና የሚከተለው ነበር….
‹‹የታዋቂ የቢዝነስ ማን አቶ ሃይለልኡል ብቸኛ ልጅ ከጠፋችበት መገኘቷ ታወቀ…በፀሎት ከሶስት አመት በፊት ልቧ መስራት አቁሞ የነበረ ሲሆን በዛን ወቅት የመኪና አደጋ ደርሶባት አብራት ለህክምና ወደ ታይላንድ የሄደችው በሬዱ ለሜቻ ህይወቷ በማለፉ አባትዬው በሰጡት ፍቃድ መሰረት ልቧን ለበፀሎት በመለገሷ የልብ ንቅለ-ተከላ ሊደረግላትና ድና ወደሀገር ልትመለስ ችላለች…ባለፈው ወር የጠፋችው በፀሎት ኃይለልኡል የተገኘችው በእነዚሁ በአቃቂ ክፍለከተማ በሚኖሩት ልብ በለገሰቻት ልጅ ቤተሰቦች ቤት መሆኑ በጣም አነጋጋሪና አስደማሚ ታሪክ ሆነዋል፡፡
በዛሬው እለት የበሬዱ የሶስተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፉት ሁለት አመት እንደተደረገው በአቶ ኃይለልኡል ቤት የምስጋና ድግስ ሲደገስ የቆየ ቢሆንም..ዛሬ ግን ይሄ ቀርቶ አቶ ኃይለልኡልና ቤተሰባቸው በቤታቸው የደገሱትን ድግስ ሙሉ በሙሉ ሰርዘው በሞች በሬዱ ለሜቻ የትውልድ አካባቢ ለስሟ መታሰቢነት እንዲሆን ከዛሬ ጀምሮ በአካባቢው አቅም የሌላቸውና ችግረኞችን በቀን ሁለት ጊዜ የሚመግብ በሬዱ በፀሎት ምገባ ተቋምን ከፍተው ያስመረቁና በቦታውም ከ500 በላይ ሰዎችን በመመገብ ማስጀመራቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህም የሞች አባት የሆኑት አቶ ለሜቻ ስለሁኔታው ሲናገሩ‹‹በእውነት ልጄ ዛሬ ሞትን ድል ነስታ እንደተነሳች ነው የምቆጥረው..ልጄ በህይወት እያለች ለተቸገረ ሁሉ የምታዝን የዋህ ነበረች..አሁንም ከሞተች በኃላ ይሄው በስሟ ብዙዎች ጠግበው እንዲያድሩ ምክንያት ስለሆነች ኮርቼለሁ….ይሄንን እውን ያደረጉትን አቶ ኃይለልኡል እና ባለቤታቸውን አመሰግናለሁ….የእነሱ ልጅ የሆነችው በፀሎት ለእኔም ልጄ ነች….ከአሁን በኃላ በሬዱ ሞተች ብዬ አላዝንም…. ስትናፍቀኝ በፀሎትን አቅፌ አፅናናለሁ…ደግሞ እዚህ ስፍራ መጥቼ በስሟ ሰዎች ምግብ ቀምሰው ሲያድሩ ተመልክቼ ረካለው››በመላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል…የሚል ነበር፡፡
ከድግሱ በኃላ አቶ ኃይለልኡልና ወ.ሮ ስንዱ ወደቤታቸው ሲሄዱ በፀሎት ግን ለሊሴን ተከትላ ወደእነሱ ቤት ነበር የሄደችው…በማግስቱ ግን ቤተሰቡ በአጠቃላይ ተሰብስበው ወደቦሌ ሄዱ ፡፡ሲደርሱ ሰለሞንም ነበር….ይህ ዝግጅትና ግንኙነት ለሁለቱም ቤተሰብ ልክ እንደቅልቅል ነው፡፡በዚህ ደግሞ ቁጥር አንድ የፈነጠዘችው በፀሎት ነች፡፡የእሷን ደስታና ፈንጠዝያ ሲከታተል የነበረው ሰለሞን ‹‹እሺ ይህቺን ልጅ ለማግባት ልጃችሁን ስጡኝ ብዬ ሽማግሌ ምልከው ለየትኛው ቤተሰብ ነው፡፡ብሎ እራሱን ጠየቀና ፈገግ አለ፡፡‹‹ግድ የለም እሷ ትስማማ እንጂ እኔስ ሁለት የሽማግሌ ቡድን ማቋቋም አያቅተኝም፡፡›› ሲል ለራሱ መልስ ሰጠ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ፊራኦልም ከሰለሞን ጎን ተቀምጦ ፊት ለፊቱ በፀሎትን እየተመለከተ በውስጡ ‹‹እሺ አሁን የእህቴን ልብ ተሸክማ እህቴ ስለሆነች ልደሰት ወይስ. ፍቅሬን ተቀብላ ፍቅረኛዬ መሆን ስለማትችል ልከፋ?››በውስጡ የሚያመነዥገው ጥያቄ ነበር፡፡‹‹ፍቅሯ በዚሁ ቀጥሎ ከባሰብኝ ምንድነው የማደርገው?››በጣም ተጨነቀ፡፡
አስታየታችሁን አስፍሩልን አዲስ ትረካ ለመጀመር ስላሰብን

ተፈፀመ።
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
ከመጽሐፍት መንደር
ከመጽሐፍት መንደር
ከመጽሐፍት መንደር
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
አስታየታችሁን አስፍሩልን አዲስ ትረካ ለመጀመር ስላሰብን