📢
ለዓረፋ ዚያራ ... በምንችለው ሁሉ ኢስላምን አደራ !!!🔺
⛓... ያንተ አባቶች ጋራ ሸንተረሩን ሞፈርና ቀንበር አጥምደው በመቆፈር ፊደል ሳይቆጥሩ በጣታቸው እየፈረሙ አንተን ለማሳደግና ከተሜ ስልጡን ለማድረግ ከነበራቸው መስዋዕትነት በተጨማሪ የተለያዩ ማማለያዎችንና የተጠኑ ስልቶችን በመጠቀም ሀገሬውን ለማክፈር የመጣውን ኃይል ሸሪዓዊ ዕውቀትን ባልተሞረከዘ ጥበብና ተፈጥሯዊ በሆነ ማንነት ላይ ሆነው በከፈሉት ተጋድሎ ሕዝበ ሙስሊሙን በአላህ ፍቃድ ከክህደት ታድገውት አንተንም ዛሬ ላይ ላለክበት ማንነት አበቁክ።
💐 አንተ ግን ይህን ወደር የማይገኝለት የአባትና እናት ውለታ ረስተክ... እነዚያው ካፊሮች ከብዙ ዓመታት የሴራ ቆይታ በኋላ ትላንት እጅ ባለመስጠት ፊት ነስቶ ጠላቱን ያባረረና ዕምነቱን የጠበቀ ጀግና አባትና እናትን ደከም ብለው ወገባቸው በጎበጠና ከልቡ የሚጦራቸው የአብራካቸወ ክፋይ ኖሮ እንደሌለ ነገር ያጡ የሆነ ጊዜ... በአላህ ምድር ላይ ክህደትን የማንገስ "ፕሮጄክት" ነድፈው ለየት ያለና የተጠናከረ ተልዕኮ በመያዝ ወደ እያንዳንዱ ሙስሊም ቤት በስውርና በግልጽ እያንኳኩ ነው። በናቅናቸውና ኋለ ቀር አርገን በምንቆጥራቸው ወላጆቻችን ጀግንነት ያልተደፈረ ዕምነት በእኛ ስልጡንና ዘመናዊ በመሰልነው ከንቱ ኩፍሶች ተናቀ !!! ፊደል ሳይቆጥሩ የጠበቁት "ዲን" ፊደሉን አተራምሰን ለይተን የተማርነው እኛ አስደፈርነው ! እነሱም የአባቶቻችንን የጀግንነት ተጋድሎ ድል ለመቀልበስና ለመበቀል ፍርኀት የዋጠውን የሙስሊም ትውልድ ሴት ወንድ እፃን አዋቂ ሳይሉ ለሁሉም በሚስማማው መልኩ ኩፍርን አበጅተው እያሳደዱት ነው !!!
ስለዚህ ፦ እንንቃ በደንብ እንንቃ !!!
👉 ጥቂት የማይባሉ ሰዎች በኛው ወንጀል ምክንያት የመጣውን ይህን አስከፊ የኑሮ ውድነትና መከራ ለማለፍ ሲሉ በሩን እየከፈቱ ነው !!!
የአንተስ ቤተሰቦች በራቸውን ላለመክፈታቸው ምን ማስተማመኛ (ዋስትና) አለክ ?
👉 ሰሞኑን ከተወሰኑ ወንድሞች ጋር ሆነን ለዚሁ ለዳዕዋ ጉዳይ በሚል ወደ ደቡብ ክልል ወደምትገኘው ስልጤ ዞን ሄደን ነበር። በአከባቢው ያለው ማህበረሰብ በአላህ ቸርነት መታደል ሆነና እስልምናን ዕምነት ከመሠረቱ በመጎናፀፍ እስካሁን ድረስ በትውልድ ሽግግር አላህ ጠብቆለት ከላይ ያወሳውላቹ እናት አባቶች በአላህ ዕርዳታ በከፈሉት መስዋዕትነት እዚህ ደርሶ ነበር።
👉 አሁን ላይ ግን የኩፍር ኃይሎች ትላንት ወላጆቻችንን ለማማለል የተጠቀሙበት " ልጆቻችሁን ትምህርት እናስተምርላችዋለን ... ! " በሚልለው ዘዴ ሳይሆን... ዛሬ ኑሮ ተወዷል አይደል ...??! ጊዜውም እንደምታዩት ከፍቷል ...‼️ ደሞም ወልዳቹ እንዳልወለዳቹ ነገር ልጆቻቹም ጠፉ !!!
"እውነተኛ በሰማይ ያለው አባት በሩን ከፍቶ ነው እኛን ወደ እናንተ የላከን..." የቸገራቹን ነገር ንገሩን የምትፈልጉትን ነገር ይዘን እንመጣለን !!! እያሉ እኛ የነፈግናቸውን ዱቄትና ዘይት ...ለመስጠት እየሞከሩ ነው‼️
ልክ ሰለፎቹ እንደሚሉት ፦ « ሆድ ከበላ ዓይን ያፍራል » እውነት ነውና የገጠር ወገኖቻችንም ይህን አደጋ የሚታደጉበት ኢማን ተሸርሽሮ ጫፍ የደረሱ ይመስል አንዳንድ ለሆዱ አደር የሆነ ማይረባ የፖለቲካ ጉዳይ አስፈፃሚና ከንቱ የሆነውን ተራ ሰው ተጠቅመው እጅ መንሻ በመስጠት ኩፍራቸውን በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ።
አዎ ! እኛም በሄድንበት ያየነውና የሰማነው ይህንኑ ነው።
ከሄድን በኋላ እንግድነት ከተቀበሉን ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት እከሌ እዚህ ቦታ እከሌ እዚህ መንደር ላይ እከሊትም በዚህ ምክንያት ከፈሩ "እየሱስ ጌታ ነው ‼️" ማለት ጀመሩ። በማለት እያዘኑ ነገሩን። ሌላኛው አንድ ወንድማችንም እንዲህ በማለት አስከትሎ በቤተሰቡ የሆነውን እውነተኛ ክስተት እያዘነ ነገረን « ከአለፈው ዐረፋ በፊት አዲስ አበባ ዚያራ መጥቶ በሰላም ሸኝተነው ነበር። ለዐረፋም ስንመጣ በነበረበት ነበር። ሰሞኑን ስመለስ ግን ከፍሮ "አላህ ጬኛል" (አላህ ወልዷል‼️) እያለ ተቀበለን !!! ያሳዝናል ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ገብቶናል‼️
ያሳዝናል ! ተጠያቂው ማነው ‼️?
ሁላችንም ነን !!!
አዎ እኛ ሰራን ካልን የሚታየን ትልቁ ስራ ከኩፍር ወደ ኩፍር አስተምህሮ የሚቀባበለንን ት/ቤት ነው። አዎ ! ለዚህ ነው ብዙ ሺህ ብር ዶላርና ሪያል ለማሰባሰብ እየሮጥን ያለነው ይህን ደሞ ቀዳማዊቷም እየተገበረችው ነው። የርሷ ትግበራ ግን እጅግ በረቀቀ ሰው ሰራሽ ስሌት የተቀነባበረ ነው !!! የእናንተ እና የእርሷ ዕቅድ በመነሻ አሳቡ አንድ ሆኖ ድንቁርናን ማጥፋት የሚለው ነው‼️
በማሳረጊያውና በመጨረሻው ውጤት ግን... የእናንተው ዕምነቱን እየሸራረፈም ቢሆን ሊቅ ማግኘት ሲሆን የርሷና የመሰሎቿ ግብ ግን ሊቅ እያፈሩ በአላህ ምድር ላይ ኩፍርን ማፅናት ነው !!!
ይህ ደግሞ በቀጥታና በተዘዋዋሪ እስልምናን መዋጋት ነው ‼️እኛም አብረናቸው እስልምናን እየተዋጋን ይሆን !!?‼️
አዎ ! ጥርጥር የየውም !!! አይተናነቀን አምነን እንቀበል !!!
👉 ይህ ደሞ ሳይታለም የተፈታ መሆኑ ገና ከጅምሩ ገብቶናል !!!
እንዴት አይግባን የውዱ ነብይ ሱና ተከታይ ሆነን ???!!!
👉 ሙስሊሞች ሆይ ሁላችንም በደንብ ይግባን !!!
👉 ቆም ብለን እራሳችንን በአስተውሎት እንጠይቅ !!
👉 ስለዚህ ማንቀላፋቱ ይብቃ ! ትክክለኛ የ"ዐቂዳ"ና "ሱና" ፍሬ ላላቸው መስጂዶች ፣ መርከዞች ፣
መድረሳዎች... ብራችንን እንምዘዝ እላለሁ ።ይህን በማድረግ የክህደት ኀይሎችን እንዋጋ አላፊነታችንን ተወጥተን ወገኖቻችንን ከኩፍር እንታደጋቸው !!!
አንተ እንደሆነ የገጠሩን መሬት እትብትክን እንዳልቀበርክበት ነገር ትተከዋል !! ረስተከው የተውከው የገጠሩ ሰውም በዓመት አንዴ ብቻ ተመግቦ እንደሚፀዳዳ ነገር ...ጋዝ ሳሙናና ጨው... አንጠልጥለክ ደሟን አፍስሳ ፥ ስጋዋ ተተልትሎ የወለደችክ ሳያንሳት በድጋሚ ጡቷን መዝምዘክ ፥ በሽንትክ አቃጥለካት ፥ ወገቧን አጉብጠክ ያስቀራካትን ውዷን እማምዬ ወግ ነውና ሰው ለመምሰል ስትል "ለዐረፋ" ብቻ ሄደ ታያታለህ❗
ያለመታደል ሆነና አብዛኞቹ የገጠር እናቶች እናትነታቸው በዓመት አንዴ ለዐረፋ ብቻ ሆነ❗
አንተና አንቺ እኔንም ጨምሮ ሁላችንም የኢስላም ልጆች ሆይ ! የአላህንና የመልዕክተኛውን "ሐቅ" በከባዱ ይይዘናል !!!
እንዲሁም የእናትና አባት ሐቅን አለመወጣታችን በታማኙ መልዓክ "ጅብሪል" አስረግሞናል...!!! በታላቁ ነብይ አንደበት "አሚን" ባይነት ይሁንታን አግኝቷል !!!
ለፍርድ በማይቾክለው አምላክ ፈራጅነት "ጀነት" እርም እንዳይሆንብንም ያስፈራልናል !!!
📢 ስለዚህ አላህ ፊት ቀርበክ ሳትጠየቅ በፊት ከሆዳቸው በላይ ዕምነታቸውም አደጋ ተጋርጦበታልና በዕውቀትክ በጉልበትክ በገንዘብክ ብቻ በቻልከው ሁላ ለወላጆችክም ለወገኖችክም ድረስ እላለሁ !
“ ከተሜ መባል የሆነ ነገር ቢኖረውም ቅሉ ገጠሬ መባል ግን ልዩ ጥበብ አለውና ”
👉 እትብትክ የተቀበረበትን ገጠር አስታውስ !!!
… ኢስማኤል ወርቁ...
https://t.me/amr_nahy1📎
https://t.me/mesjidalsunnah/18721