አባ ገብረኪዳን እንዲህ አሉ፣ "ለሰው ልጅ በየቀኑ ሰላማዊ ህሊና የሚሰጠው ምን እንደሆነ ልንገራችሁ? ለሰው መልካም ማድረግ ነው። መልካም ባደረግን ቁጥር ሁልጊዜ አሸናፊዎች፣ ድል ነሺዎች ነን። ሞገስ ይሰማናል፣ ምክንያቱም መስጠት እግዚአብሔርን ስለሚያስመስል ነው።
"መስጠት የሚባለው ቁሳቁስ ብቻ አይደለም፣ መልካም ምክርን መስጠት፣ ዕውቀትን መስጠት፣ ጉልበትን መስጠት፣ ጊዜን መስጠት ስጦታ ናቸው። መልካም ፊት፣ ብሩህ ገፅ፣ ጥሩ ፊት ማሳየት በራሱ ስጦታ ነው። ለአንድ ሰው ብሩህ ገጻችን ስናሳየው ይወዱኛል ማለት ነው፣ ያከብሩኛል ማለት ነው ብሎ እንዲያስብ እናደርገዋለን። በዛን ጊዜ ይፅናናል። የሰው ልጅ አንድ የሚያዝንበት ነገር ቢኖር እኮ ሰው ይጠላኛል ብሎ ማሰቡ ነው። ስለዚህ እኛ ብሩህ ገፅ ስናሳየው እሱም ስጦታ ነው።
"ሳቅ በራሱ ስጦታ ነው፣ ለምሳሌ ቤታችን እንግዳ ሲመጣ መሳቅ ማለት ለዛ ሰው የመጀመሪያ በጎ ስጦታ ሰጠነው ማለት ነው። 'በቃ ይወዱኛል፣ እነዚህ ሰዎች አልሰለቹኝም" በማለት በሙሉ ልብ እንዲያድር እናደርገዋለን። የሀገራችን ሰው "ከፍትፍቱ ፊቱ" ያለው ለዚህ ይመስለኛል።
"ሌላው ቀርቶ እገሌ ችግሩን ቢላቀቅ ደስ ይለኝ ነበር ብሎ ማሰብ በራሱ ስጦታ ነው። ቢኖርህ ስጠው፣ ባይኖርህ ግን ከችግሩ እንዲወጣ መልካም መመኘት እንደስጦታ ይቆጠራል።ከሚደሰቱት ጋር መደሰት፣ ከሚያዝኑት ጋር ማዘን በራሱ ስጦታ ነው።ሰው ሲያለቅስ ቁጭ ብሎ 'አይዞህ' ማለት ስጦታ ነው። ክርስቶስ ደስ ከሚሰኙ ሰዎች ጋር ሠርግ ላይ ይገኝ ነበር፣ ከሚያዝኑት ደግሞ ለቅሶ ላይ ይገኝ ነበር።"
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ ::