ለፈገግታ😁😅😂
ሚስቴ በየቀኑ ለሥራ ከቤት ስወጣ የረሳሁትን ነገር #ታስታዉሰኛለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ፣ ሌላ ጊዜ መነጽር፣ አንዳንዴም ሞባይል፣ እንዲሁም ሌላ ነገር መርሳት ልማዴ ነው።
"አሁንማ አረጀህ" እኮ ወይኔ #ባሌ!😊" እያለች እየሳቀችብኝ ታቀብለኛለች የረሳሁትን።💁♀😄
#ተረቧን ለማስቀረት የሆነ ዘዴ ዘየድኩ። የምረሳቸዉን ነገር በወረቀት ላይ መዝግቤ ያዝኩ። የሆነ ቀን ጠዋት ከመውጣቴ በፊት ወረቀቴን አውጥቼ ሁሉንም መያዜን አረጋገጥኩ።💪
ከዚያም በድል #አድራጊነት ስሜት መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ ሞተር አስነስቼ ግቢዬን ለቅቄ ወጣሁ። 😎
ትንሽ እንደነዳሁ ደወለች። ባለቤቴ። ክው አልኩ፣ ዛሬ ደግሞ ምን #ረሳሁ ብዬ ...
"ሄሎ" አልኳት።
" ዛሬ ደግሞ የት እየሄድክ ነው?" አለችኝ።
"ሥራ ነዋ"😃
" #እሁድ እኮ ነው፣ የምን ሥራ!።"😳
ትንሽ ቆሜ ፈገግ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ።
😅😂😂