የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል በከተማው ከሚገኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት እና ከሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ እና የጽዳት መርሐ ግብር አከናወነ።
ኅዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም የማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል ከመንፈሳውያን ማኅበራት ኅብረት እና ከሰ/ት/ቤት አንደንት ጋር በመተባበር በከተማዋ ሠፊ ንቅናቄ የተደረገበት የጽዳት እና የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውኗል።
የአዳማ ከተማ መስተዳደር እና የከተማው ደም ባንክ ጋር በተባባሪነት በተሳተፉበት የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ አቶ በሪሶ ዶሪ የአዳማ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ሀብታሙ ግዛው የአዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ም/ኃላፊ እና አቶ ኤልያስ ታደሰ የአዳማ ከተማ ጸጥታ ዘርፍ እና የሃይማኖቶች ጉዳይ ኃላፊን ጨምሮ ከ2000 በላይ የአዳማ ማእከል አባላት፣ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ፤የአዳማ ከተማ የሰ/ት/ቤቶች አባላት እና በአዳማ ከተማ የሚገኙ የመንፈሳውያን ማኅበራት አባላት ተገኘተው ደም ለግሰዋል።
" መልካም ሥራ ለመሥራት አንታክት" ገላ 6፥9 በሚል መሪ ቃል የተከናወነው መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ንቁ ተሳትፎ የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።