በጃፓንና በኮሪያ አገራት የአብነት ትምህርት ቤቶች እየተስፋፉ እንደሚገኝ ተገለጸ
ጥር ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
በሩቅ ምሥራቅ የአብነት ትምህርት ቤቶች እየተስፋፋ እንደሚገኝ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የሩቅ ምሥራቅ የእንግሊዝ፣ አየር ላንድና አከባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በዩኒቨርሳል ሰላም ፌዴሬሽን የሰላም አምባሳደር ከማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ጋር በቨርቿል (በበይነ መረብ) ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ሰብሳቢ አቶ አንዱ አምላክ ተአምራት በአብነት ትምህርት ቤት፣ ግቢ ጉባኤያትና የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ እንደሚገኝ በመግለጽ አባቶችና ሀገረ ስብከቱ በሚሰጡን አቅጣጫ መሠረት ሐዋርያዊ ተልዕኮ ከሰንበት ትምህርት ቤቶችና ከምእመናን ጋር በመሆን በመተባበርና በመናብብ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በዚህም ሐዋርያዊ ተልዕኮ ከቻይናና ከሌሎች አገራት የተወጣጡ ተማሪዎችን በማስተማር፣ የተጠማቂያንን ፕሮጀክት በመሥራት፣ የአብነት ትምህርቶችን በመስጠት ድቁና እንዲቀበሉ በማድረግ እንዲሁም በሩቅ ምሥራቅና ለትምህርት በተለያዩ አከባቢዎች ለሚገኙ ምእመናን በአካልና በበይነ መረብ ሥልጠናዎችን እየሰጡ እንደሚገኙ አክለው አመላክተዋል።
ዲያቆን ዶ/ር ውብዓለም ደስታ የሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በበኩላቸው ቤተ ክርስቲያን ሥራዋን አስፍታ ከሠራች ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልጸው ሀገረ ስብከቱ ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦና ተናቦ መሥራቱን አስረድተው “በተለይ ለአገልጋዮች ሙሉ ኃላፊነትን ከተጠያቂነት ጋር በነጻነት የማገልገል ዕድል መስጠትና በቅርበት እየተከታሉ ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሔዎችን መስጠት ለውጥ እንደሚያመጣ አይተናል” ብለዋል።