ከዚህ አንጻር ወደ ፊት እንደ ሀገረ ስብከት ኮሚቴዎችን በማስተባበርና በጋራ በመሆን የተጀመሩ አገልግሎቶችን በማጠናከር፣ አዲስ አማንያንን በማፍራት፣ መዋቅረ ቤተ ክርስቲያንንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ በማገልገል፣ አብያተ ክርስቲያናትን በማስፋፋት ምእመናን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በሩቅ ምሥራቅ የአብነት ትምህርት ቤቶች ከ22 አገራት በላይ እየተስፋፋ እንደሚገኝ በመግለጽ በዚህም በአካባቢው ዲያቆናትና ካህናት አባቶች አገልግሎቱን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
አያይዘውም “ዓለም አቀፋዊ ሥራ ለመሥራትና ብዙዎችን ለማምጣትና ለማስተማር የተማረ የሰው ኃይል ያስፈልገናል፤ በተለይም ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል እንዲሁም ወንጌልን ለማስፋፋት ፍቅር፣ ሰላምና መከባበር ማእከላችን መሆን አለበት” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።