ቅድሚያ እንዴት አድርገን MS Excel መክፈት እንችላለን የሚለውን እንመልከት።
በመጀመሪያ Windows 7,8,10,11 የምትጠቀሙ ከሆናችሁ መፈለጊያ(Search) ማድረጊያው ላይ Excel ብላችሁ ፈልጉ ከዛም MS Excel ይመጣላችኋል ከዛም Click በማድረግ ይክፈቱት።
መልካም አሁን የ Excel የመስሪያ ገጽ ይመጣላችኋል ሰንጠረዥ በሆነ መልኩ ማለት ነው። እንደምታዩት ሰንጠረዡ ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ የተዘረዘሩ A,B,C,D,E,F........እያለ የሚሄድ ሲሆን ከግራ በኩል ወደ ታች ደግሞ 1,2,3,4,5....... እያለ ይሄዳል ማለት ነው።
ስለዚህ አሁን ማወቅ ያለባችሁ ጉዳይ ምንድን ነው በሂሳብ ትምህርት X,Y Coordinate የሚባለው የXና የY መገናኛ ቦታ ማለት ነው። ከላይ የጠቀስኩት ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ A,B,C,D,E,F.......እና ከግራ ከላይ ወደ ታች የተዘረዘረ 1,2,3,4,5....እያለ የሚሄደው ቁጥር የሚገናኙበት አንዷ ሰንጠረዥ Cell ትባላለች እናም በዚህች Cell የሚቀመጥ ማንኛውም ቁጥር፣ ጽሁፍ፣ ምልክቶች Values ይባላሉ። የሚገኑበት ቦታ ደግሞ ለምሳሌ ከExcel የመጀመሪያው Cell ላይ መገኛ A1 ይባላል ይህ ማለት Value የተቀመጠበትን ቦታ(Coordinate) ማየት ይጠበቅብናል ማለት ነው ስለዚህ ለምሳሌ A5 ሊሆን ይችላል F27 ሊሆን ይችላል ማለት ነው። ይህንን ካወቅን ወደሚቀጥለው እንሂድ።
አሁን የማሳያችሁ የExcel Functions ነው
1ኛ SUM የሚባለው Function በExcel ላይ ያሉትን Cell Values ለመደመር የሚያገለግለን ነው። ለምሳሌ የሆነ Cell ላይ በማስቀመጥ ወይም E9 ላይ በማድረግ =SUM(E4:E8) የሚለውን ከጻፍን ከE4 እስከ E8 ድረስ ያለውን ይደምርልናል ማለት ነው።
=SUM(E4,E8) ብለን ከጻፍን E4 እና E8 ብቻ ይደምርልና።
=SUM(E4:E8)/5 የሚለውን ከጻፍን ከE4 እስከ E8 ድረስ ያለውን ይደምርና ከ5 በማካፈል አማካይ ውጤት ያስቀምጥልናል ማለት ነው።
=SUM(E4,E8)/2 ብለን ከጻፍን E4 እና E8 ብቻ ይደምርና ለ2 በማካፈል አማካይ ውጤት ያስቀምጥልናል።
2ኛ AVERAGE Function ይህ Function Excel ላይ አማካይ ውጤትን ለመስራት ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ ይህንን ብንጽፍ =AVERAGE(B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን Average አማካይ ውጤት ይሰጠናል ማለት ነው።
3ኛ MIN Function ይህ Function Excel ላይ ዝቅተኛ ውጤትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ ይህንን ብንጽፍ =MIN(B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን ዝቅተኛ ውጤት(ቁጥር ያለውን) ይሰጠናል ማለት ነው።
4ኛ MAX Function ይህ Function Excel ላይ ከፍተኛ ውጤትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ ይህንን ብንጽፍ =MAX(B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን ከፍተኛ ውጤት(ቁጥር ያለውን) ይሰጠናል ማለት ነው።
5ኛ COUNT Function ይህ Function Excel ላይ የCell ብዛትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ ከB2 ጀምሮ እስከ B6 ድረስ ቁጥር Values ብናስገባና የሆነ Cell ላይ ወይም B7 ላይ በማስቀመጥ ይህንን ብንጽፍ =COUNT(B2:B6) የሚለውን ከጻፍን ከB2 እስከ B6 ድረስ ያለውን Number of Cell በቁጥር ያስቀምጥልናል ስለዚህ መልሱ 5 የሚል መልስ ይሰጠናል ማለት ነው።
6ኛ LEN Function ይህ Function Excel ላይ Number of character ወይም Number of spelling ብዛትን ለማወቅ ይጠቅመናል። ለምሳሌ B2 ላይ ያለውን ያዳታ Character ብዛት ለማወቅ ብንፈልግ B3 ላይ ወይም ሌላ Cell ላይ በማስቀመጥ ይህንን ብንጽፍ =LEN(B2) የሚለውን ከጻፍን B2 ላይ ያለው መረጃ MUHAMMED ቢሆን Muhammed የሚለውን በመቁጠር በቁጥር 8 ብሎ ያስቀምጥልናል ምክንያቱም Muhammed የሚለው Number of character ብዛት 8 ስለሆነ ማለት ነው።
6ኛ በተጨማሪም ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ለማካፈል፣ ለማባዛት የሚከተለውን አጭር መንገድ ተከተሉ።
ለምሳሌ: B2, C2, D2, E2, F2 ላይ የተቀመጡ ቁጥሮች ቢኖሩ ከB2 እስከ F2 ያለውን ቁጥር ለመደመር ብንፈልግ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ ባለው መልክ መስራት ትችላላችሁ እንደ አማራጭ ግን
1ኛ ምሳሌ G2 ላይ በማስቀመጥ ከርሰራችሁን =B2+C2+D2+E2+F2 ብላችሁ ኢንተርን ብትጫኑ ከB2 እስከ F2 ድረስ ያለው ይደምርና ድምሩን G2 ላይ ያስቀምጣል ማለት ነው።
2ኛ ለማባዛት ብትፈልጉ ለምሳሌ B2 ና C2 ማባዛት ብትፈልጉ የሆነ cell ላይ ከርሰራችሁን በማስቀመጥ =B2*C2 በማለት ከዛም ኢንተርን ስትጫኑ የB2ንና C2ና ዋጋ በማባዛት ያስቀምጥላችኋል ማለት ነው።
3ኛ ማላፈልና መቀነስ ልክ እንደ ማባዛቱ የ* በመቀየር / ወይም - መጠቀም ትችላላችሁ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology