አዲስ ቅኔ 📃📃🎹 🎵🎤🎤


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ያልተሠሙ አዳዲሰ የሐዋሪያዊት ቤ/ክያን መዝሙሮች
" በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤"
🎷🎺🎸🎸🎸🎸🎸
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:19)
@newsongs00

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




















“ በፍቅር ይሁን ጉዞው ”

የእግዚዓብሔርን ፍቅር ብናቀው ቢገባን
የራሡ የሆነውን ሁሉንም ሰጥቶናል
ሃጢያትን ስንጨምር ግን ፍቅሩን አብዝቶ
ወደ ምድር መጥቷል ክንዱን አዘጋጅቶ

የጥልን ግድግዳ በደሙ አፈረሠው
ለኛ በደል ሃጢያት መስቀል ላይ የዋለው
ያ የፍቅርን ጥግ በደሙ የገለፀው
የናዝሬቱ ኢየሡስ ፍቅር ግድ ብሎት ነው

የሱስ ፍቅር ነህ ፍቅር
ውዴ ፍቅር ነህ ፍቅር
አባ ፍቅር ነህ ፍቅር
አንተ ፍቅር ነህ ፍቅር

1፧ ወንድምህን ስትገፉው በረከትህ ይገፉል
የወንድምህ በደል ወደላይ ወዳምላኩ ይጮሃል
እግዚዓብሔርን ማወቅ ለጥበበኞች ነው
ፍቅርን እንላበስ እግዚዓብሔር ፍቅር ነው
ታድያ ምኑ ላይ ነው ወንድሜን የምለው
ሸክሙ ከብዶበት ሲወድቅ እያየው
ታድያ ምኑ ላይ ነው እህቴን የምለው
ሸክሟ ከብዶባት ስትወድቅ እያየው

2፣ ሲደክም ላግዘው መንገዱ ጉዞ ሲከብድበት
የአይኔን ምሰሶ ሸፍኜ ወንድሜ ላይ ስፈርድ
ሌላውን ዝቅ ሳደርግ ሳይገባኝ እራሴው ዝቅ እያልኩ
ፀጋዬ ተወስዶ ባዶዬን ራቁቴን እየኖርኩ
እረ አይሁንብኝ እሮጬ እሮጬ ድካም ብቻ
ሚበልጠውን ጥዬ አልስጠው ለስጋዬ ምርጫ
መገፋፋት ይቅር እርሻው ቤቱ እኮ ሰፊ ነው
ሰማይ ካላስገባኝ መድከሜ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው

3፣እንያያዝ ቤቱ በአንድ ልብ በአንድ ሃሣብ
ፍቅርን እናስቀድም ቅድስናው ያብብ
ፍቅር ይሸፍነው ያለብንን ክፍተት
ጥል ክርክር ይውጣ ያ ትልቁ ሃጢያት
በፍቅር ይሁን ጉዞ በፍቅር
ንፁህ ልብ ትህትና ይጨመር
ንፉስ እንዳይገባ መሃላችን
ቦታ ስፍራ ይጣ ጠላታችን





















20 last posts shown.

499

subscribers
Channel statistics