ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
ዛሬ ትልቁ ሰው፣ ያለውን ሁሉ ለኢስላም ሳይሰስት የሰጠው ሙጃሂድ ይህንን ዓለም ተሰናበተ። አዎ አማን አሰፋ በዝዋይ እስር ቤት አላህን ተገናኘ።
የዘመናችንን ጌጥ፣ የትውልዱን ሀኪም አላህ ወደራሱ ጉርብትና ወሰደው። የመሞቱን ዜና ስሰማ በተቀመጥኩበት ደረቅኩ። ውስጤ ከዓይኔ በፊት ዕንባውን አፈሰሰ።
አዛኝ ነበር ሰው ሲታመም የሚያነባ። የተቸገረን ሲያይ የሚያለቅስ። በአላህ መንገድ የተሰዋን ሰውዜና ሲሰማ ወንድሜ ቀደመኝ የሚል ለሸሂድነት የሚጓጓ ታጋይ ነበር። ለጋሽም ነው ያለውን ሁሉ ሰጥቶ ለታክሲ የሚበደር። ፀሐፊም ነው አንደበተ ርቱዕ ቃላቶቹ ልብን የሚሰረስሩ። ዛሂድ ዱንያን የናቀ በነጠላ ጫማ የሚራመድ ሰው ነበር። እንደ ወንድም መካሪ ነው። እንደ አባት እየተቆጣ ከልምዱ የሚያስተምር ጀግና። ለዚህ ከኔ በላይ ምስክር የለም።
ቀን አልፎ መዝገቡ ሲገለጥ ሁሉም አላህ ዘንድ ይፋ የሚሆን ብዙ ምስጢር አለን!
አላህ ቀብርህን ኑር ማረፊያህንም ጀነተል ፊርደውስ ያድርግልህ።
© Mahi Mahisho