የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል
ልደት ማለት ምን ማለት ነው?
ልደት ብዙ ምሥጢር ይለበት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ከማኅፀን መወለድ ከጨለማ ወደ ብርሃን መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም፣ ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት፣ መኖር፣ መፀነስ፣ መወለድ፣ ከእናት ኾድ ወደ ብርሃን መውጣት፣ መገኘት፣ ተገልጾ መታየት ነው፡፡
የጌታችን ልደት ከሌላው በምን ይለያል?
ሰው ሁሉ በአባትና በእናት መካከል በሚፈጸመው ሩካቤ ሥጋ፣ (በሥጋ ግንኙነት) በዘርዓ ብእሲ ወብእሲት /በወንድና በሴት ዘር/ ምክንያት ተጸንሶ የሚወለድ ሲሆን ጌታችን ግን ይለአባት፣ /ያለወንድ/ ያለ ዘርዐ ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡
እንደዚሁም ሌሎች ሰዎች ልጅን ከወለዱ በኋላ ድንግልናቸው እንደማይኖር የታወቀ ስሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን አምላክን ከመጽነስዋ በፊት፣ አምላክን በምትወልድበት ጊዜም ሆነ አምላክን ከወለደች በኋላም ሁሉ ጊዜ ድንግል፣ ንጽሕት፣ ቅድስት ናት፡፡ ስለዚህም የጌታችን ልደትና የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልና፣ ንጽሕና እና ቅድስና ከሌሎች ሁሉ የተለየ ነው ማለት ነው፡፡
የመልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክትና የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ሁናቴ እንዴት ነበር?
ወበሳድስ መርኀ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ ድንግል ሉቃ.፩÷፳፮፡፡
መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር አገልጋይ የኾነውን ካህነ ኦሪት ዘካርያስን እግዚአብሔርን ወደሚያገለግልበት ቤተ መቅደስ ኼዶ ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ደርሷልና አትፍራ መካን የምትባለው ኤልሳቤጥ ሚስትህም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች ስሙንም ዩሐንስ ትለዋለህ ይኸውም ፍጹም ደስታ ማለት ነው ብሎ ካበሠረው በኋላ በ፮ኛ ወሩ ናዝሬት ገሊላ ወደነበረችው ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ተላከ፡፡ ኼዶም እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋን ከነፍስሽም ነፍስን ነሥቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ይሆናልና /አምላክ ከአንቺ ይወለዳልና/ በነቢያት ትንቢት፣ በመላእክት ተልእኮ ደስ ያለሽ ምልዕተ ክብር ሆይ ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ አላት፡፡
እርሷም ከዕንግዳ ሰላምታውና ከንግግሩ የተነሣ ለጊዜው ደንግጣ ነበር፡፡ ፍራትንና ድንጋጤን እያስወገደ ማብሠር ልማዱ የሆነ ቅዱስ ገብርኤል ግን ማርያም ሆይ አትፍሪ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ በአንቺ ላይ ያድራል ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳል አምላክ ከአንቺ ይወለዳል አላት፡፡
ማርያምም ንጽሕት ፍጽምት ናትና ይህ ነገር እንዴት ይሆናል? እኔ እንደሆንኩ እንኳንስ የገቢር የኀልዮም የለብኝም፡፡ ለመሆኑ መሬት ያለዘር ስታበቅል ሴት ያለወንድ ስትወልድ የት አየህና ነው እንደዚህ የምትለኝ አለችው፡፡
መልአኩም መልሶ ከአንቺ የሚወለደው ፍጡር ተራ ሰው ሳይሆን፣ ከአንቺ የሚወለደው ዕሩቅ ብእሲ ሳይሆን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለው ከሚመሰገኑት ከሦስቱ ወይም ከሥላሴ አንድ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ይህ የምነግርሽ ሁሉ ይሆናል አላትና እርሷም ይኲነኒ በከመ ትቤለኒ እንደቃልህ ይሁንልኝ ይደረግልኝ አለችው፡፡
ከዚህ ብሥራት በኋላ ጌታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆነ፡፡ እንደእኛ አቆጣጠር መጋቢት ፳፱ ቀን ትስብእቱ ወይም ፅንሰቱ ሆኖ ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ተወለደ ማለት ነው፡፡ ሙሉውን ወንጌለ ማቴዎስ ፩÷፲፰ እና ወንጌለ ሉቃስ ፪÷፩ ጀምሮ፣ መጽሐፈ ፍሬ ሕይወት በምህር ሰሎሞን ይመልከቱ፡፡
ጌታችን ለምን ተወለደ?
በኦሪት ዘፍጥረት ከምዕራፍ ፩ ጀምሮ በተከታታይ ምዕራፎች እንደምንመለከተው ልሁል እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሁሉ ሲፈጥር ሰውን በአርአያውና በምሳሌው ፈጥሮ ከሁሉም ጥፍረት አልቆ አክብሮ በገነት አኑሮት ነበር፡፡ ዘፍጥረት ፩÷፳፮፡፡ ከዘህም ጋር ሕግንና መመሪያን ሰጥቶ ሕጉን እንዲያከብር አዝዞት ነበር፡፡
አዎ ይህን ዕፀ በለስ የበላህ እንደሆነ የኃጢአትን ሞት ትሞታለህና ዕፀ በለስን አትብላ ብሎታል፡፡ ይኸውም የፈጣሪና የፍጡር መለያ፣ የአዛዥና የታዛዥ ልዩ ምልክት መሆኑ ነው፡፡ በፈጣሪና በፍጡር መካከል ሕግና መመሪያ መኖሩንም የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ዘፍ.፪÷፲፮፡፡
ይሁን እንጂ ሰው /አዳም/ የፈጣሪውን ሕግና መመሪያን ጠብቆ በተፈቀደለት መሠረት መኖር ሲገባው የፈጣሪውን ሕግና መመሪያ ጥሶ፣ የታዘዘውን አፍርሶ ያልታዘዘውን ሲፈጽም፣ በልቡ አስቦ፣ ተመኝቶ ይልተፈቀደለትን ያውም ከዐቅሙ በላይ የሆነውን የባሕርይ አምላክነትን ሲሻ /ሲፈልግ/ በመገኘቱ ከፈጣሪው ጋር ተጣልቶ ከገነት ወጥቶ ከክብር ወደ ሐሣር ተለውጦ መርገም ወድቆበት ከሕይወት ወደ ሞት ተባርሬ ነበር፡፡ ዘፍ.፫÷፩፡፡
በመሆኑም በአዳምና በሔዋን ላይ የወለደቀው መርገም ባለመነሣቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የነበረው ፶፻፭፻ ዘመን ሁሉ መርገሙን ሁሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በመስቀል ተሰቅሎ እስከ ደመሰሰው ድረስ የመርገም፣ የፍዳ፣ የጨለማ፣ የችግርና የጭንቀት ዘመን ስለሆነ ሰው መልካምም ይሥራ ክፉ ኑሮው በሲኦል በችግር ውስጥ ሆኖ ነበርና ይህን ለመደምሰስ ተወለደ፡፡ አዎ በፍጥረቱ የማይጨክን የረኅራኄና የጽድቅ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር አምላክ በአምስት ቀን ተኩል /ከመንፈቅ/ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ ለአዳም በሰጠው አምላካዊ ተስፋ መሠረት ትንቢት ተነግሮ ሱባኤ ተቆጥሮ ካበቃ፣ ጊዜው ሲደርስ ማለትም በነቢያቱ አንደበት ትንቢትን አናግሮ ከጨረሰ በኋላ ፶፻፭፻ ዓመተ ዓለም ሲፈጸም ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ዘመኑም አምስት ቀን ያለው አምስት ሺህ ዓመት ሲሆን እኩለ ቀን /መንፈቀ ዕለት/ ያለው ደግሞ አምስት መቶ ዓመትን ነው፡፡ ጠቅላላው አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ይሆናል ማለት ነው፡፡
የልደት ምሥጢር ምነድን ነው? ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል፣ በብርሃኖሙ ለቅዱሳን፣ ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ፣ የሚለው መዝሙርስ በውስጡ ምን ምሥጢርን ይዟል?
ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን በቅዱሳን ብርሃን ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከኾድ ወለድኩህ ይላል መዝ ፻፱÷፫፡፡
ይህ ቃል የአንድነትንና የሦስትነትን ምሥጢርንም የያዘ እንደመኾኑ መጠን፣ ሁሉን በሁሉ ስለ አሉ ማለትም የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ አንድነትንና ሦስትነትን ለመግለጽ ነው፡፡
ይህ መዝሙር አንድነቱን ሲገልጽ በፍጥረት ጊዜ ከአንተ ጋር ነበርኩ፣ ቅድመ ዓለም ይለእናት መወለዱን ሲገልፅም ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ወለድኩህ የሚል ስሆን፣ ድኅረ ዓለም ያለ አባት፣ ያለዘርዐ ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ሲገልፅ ደግሞ የነቢያት ትንቢት በተፈጸመበት፣ መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ባመሰገኑበት ቀን ወለድኩህ በሚል ምሥጢር የልደቱን ዕለት ያበሥራል፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ ምን ዓይነት ስጦታዎች ተበረከቱለት? የእነዚህ ስጦታዎች ምሥጢርስ ምንድን ነው?
ከቅዱሳት መጻሕፍቶዎችንና ከሊቃውንተ ብተ ክርስቲያን አባቶቻችን እንደምንረዳው ጌታችን በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ ሰብአ ሰገል አምላክ እንደ ኾነ ለማጠየቅ ዕጣንን አመጡለት፣ ንጉሥ እንደጮነ ለማየቅም ወርቅን አመጡለት፣ እንዲሁም ማኅየዊ የሚኾን የሞቱ ምሳሌ ከርቤን አመጡለት፡፡
እነዚህ በሰብአ ሰገል የቀረቡ ስጦታዎች አምላካዊ ሥራዎችን የሚያመለክቱ ዐበይት ምሥጢራት አሉዋቸው፡፡ መዝ ፸፶÷፲