የጅማው ጭፍጨፋ!
በጅማ ዞን አንድ ባለሃብት መገደሉን ተከትሎ በርካታ የአማራ ተወላጆች የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ጥቃቱን እንዲህ ዘግቦታል👇
«በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ ቀበሌ በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች መሰደዳቸውና መኖርያ ቤታቸው መቃጠሉ ተገለጸ።
በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ ቀበሌ ቦሬ ከተማ በሚገኙ ከሺህ በላይ በሆኑ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ባነጣጠር ጥቃት መኖርያ ቤቶቻቸው እንዲሁም የንግድ ሱቆቻቸውን ጨምሮ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ለማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ በስልክ ተናግረዋል፡፡
ጥቃቱ በትናንትናው ዕለት የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተተኮሰ ጥይት የተጀመረ ሲሆን በቀበሌው የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ ስጋት ላይ ናቸው ተብሏል።
ጉዳዩን ለማረጋጋት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሥፍራው ቢገኙም ጥቃቱ እስከ አሁን እንዳልቆመና ወደ ሌላ ቀበሌ እየተዛወረ ነው ተብሏል።
የአካባቢው ነዋሪዎችም ጥቃቱን ሸሽተው ወደ አጎራባች የደቡብ ክልሎች እየሄዱ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡