ታጣቂዎች አንድ ሰው ገድለው፤ ቤቶች አቃጥለው ስምንት ሰዎች አፍነው ወስደዋል!
የክስታኔ ጉራጌ (በተለምዶ የሶዶ ጉራጌ) ከኦሮሚያ ክልል በሚያዋሰንባቸው አካባቢዎች ከኦሮሚያ ክልል በሚመጡ ታጣቂዎች (ኦነግ ሸኔ) ተደጋጋሚ ጥቃትና ዘረፋ እንደሚፈፀም ተገለፀ። ባለፉት አራት አመታት በእነዚ አካባቢ በመሸጉ ታጣቂዎች የዜጎች ሰላምና ደህንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል።
ነዋሪው በሰላም ሰረቶ መግባት፤ በነፃነት አምርቶ መሰብሰብ ቅንጦት እየሆነ ነው ብለዋል። አካባቢው በኮማንድ ፖስት የሚመራ ቢሆንም ሰላም ማምጣት አልተቻለም፤ በየጊዜው የሰላም ማስፈን ውይይቶች የሚያደረጉት የፀጥታ ሀይሎችም ተጨባጭ ለውጥ በአካባቢው ማስፈን አንዳልቻሉ ተናግረዋል። የመከላከያ ሀይል ጥቃትና ዝርፍያ ከተፈፀመ በኋላ ከመምጣት ውጪ የዜጎች የየቀኑ ደህንነትና በሰላም መንቀሳቀስ ማረጋገጥ አለመቻሉን አንስተዋል።
በቅርብ ከአንድ ወር በፊት የማዕከላዊ ክልል የፀጥታ አመራሮችና የአጎራባች ኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይሎች በጋራ የሰላም ውይይት በሚል በቡታጀራ መደረጉን የሚገለፁት ምንጫችን፤ ውይይቱ ለይስሙላ ሆኖ በቦኖ አይገዶ ቀበሌ ስምንት የቀበሌው ነዋሪዎች በታጣቂዎች ተወስደዋል ብለዋል።
ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃትና ዘርፋ የሚፈፅሙባቸው፤ አማውንቴ ሞረጌ ቀበሌ፣ ገሬኖ እንስት ተክል ቀበሌና ቦኖ አይገዶ ቀበሌ መሆናቸው እየታወቀ ህዝቡ ተደጋጋሚ ቅሬታ እያቀረበ መፍትሄ ማጎኘት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
ከቦኖ አይገዶ የተወሰዱ 8 ሰዎች እስከ 600,000 እየተጠየቁ መሆኑ በመግለፅ አንዳንድ የታጋቾች ቤተሰብ ገንዘብ ልመና ወደ አዲስ አበባ መሄዳቸውን ገልፀዋል። በኮማንድ ፖስት የሚመሩት እነዚህ ቀበሌዎች ተደጋጋሚ ጥቃት፣ ዘረፋና የሰዎች እገታ እንደሚፈፀም መረጃ ሰጪው አንስተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በአይመለል ቀበሌ ቅዳሜ የካቲት 29 2017 ዓ.ም ከኦሮማያ ክልል በመጡ ታጣቂዎች አንድ ሰው ሲገደል፤ አራት የገበሬ ቤቶች ተቃጥለዋል። ጥቃት ከተፈፀመበት ቀበሌ ታጣቂዎቹ ሰዎች ለመውሰድ ያደረጉት ጥረት በአካባቢው ነዋሪዎች ብርቱ ጥረት መክሸፉን ገልፀዋል። በጥቃቱ የተገደሉት አቶ አሸብር ብረሐኑ የተባሉ በጣም ታዋቂ በተደጋጋሚ የታጣቂዎች ጥቃት ሲመክቱ የነበሩ፤ ለአካባቢው ከፍተኛ መስዋት ሲከፍሉ የነበሩ ናቸው ብለዋል ምንጫችን። ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ የመከላከያ ሀይል ወደ ቦታ መግባቱ ምንጫችን ጨምረው ገልፀዋል።
በዚሁ በሶዶ ወረዳ ዳጮ ሀሙስ ገበያ ቀበሌ ዜጎች የታጣቂዎች ጥቃት ሰግተው ወደ ቡዪ ከተማ እየተሰደዱ መሆናቸው ተገልፆል። ትልልቅ የእርሻ ማሳ ያላቸው ባለሀብቶች ሳይቀር ለደህንነታቸው ሲሉ ወደ ከተማ መሄዳቸው ተገልፆል። ይህ አካባቢ ቀደም ሲል ከ30 በላይ ዜጎች የተገደሉበት ከዱግዳ ወረዳ በቅርብ እርቀት እንደሚገኝም ተገልፆል።
ከግዮን አማራ ገጽ