The Tragedy of Julius Caesar
`` በታሪክ ውስጥ እጅግ አስቀያሚው የስለት ውግያ እና አስከፊ ግድያ ተብሎ የተፈረጀው..የዛር ጁሊየስ የተገደለበት ወቅት ነበር። ``
በእንግሊዛዊው ጸሃፊ ዊሊያም ሼክስፒር “ጁሊየስ ቄሳር” ከተሰኘው ተውኔት የተወሰደ ንግግር። ጁሊየስ ቄሳር ሲወጋ የተወጋው ቁስሉ በታሪክ ውስጥ ካሉ እጅግ አስቀያሚዎቹ የስለት ቁስሎች አንዱ ተብሎ ይመደባል።
የሮማው ንጉሠ ነገሥት ጁሊየስ ቄሳር የተገደለበት ወቅት ነው። በተመሳሳይ ሰዓት ከልብ ከሚያምነው ሰው ክህደትን የተቀበለበት ጊዜ። በዘመኑም ሁሉም ሰዎች አመጹበት ብቻውን እንደቆመ በኀብረት በመሆን በሳለ ጩቤ አጠቁት። ምንም እንኳን ደጋግመው ቢወጉት ወደ መሬት አልወደቀም፤ የድሮ ወዳጁን ‘ብሩተስን’ እስከሚያይ ድረስ።
ጁሊየስ በገዛ ደሙ እየሰጠመ ጓደኛውን ተመለከተና የተስፋና የእፎይታ እይታ በዓይኑ ውስጥ በራ። የህይወት ዘመን ጓደኛው ሊያድነው እንደመጣ በማመን ለእርዳታ እጁን ዘረጋ ብሩተስ ግን እጁን በመያዝ አንድ ጊዜ ወጋው።
እዚህ ጋር ጁሊየስ ቄሳር እንዲህ ብሎ ነበር “አንተ እንኳን ብሩተስ አንተን የማውቅህ እንግዲያው ቄሳር ይሙት” ቄሳርም ለሞት ወደቀ። የብሩተስ ውግያ ከሌሎቹ ስለት በተለየ መልኩ ለሞት የዳረገው ጩቤ ነበር.. በገላው ሳይሆን በሰውነቱ የገባው እምነት እስኪፈርስ ድረስ ጽናቱ አቆመው። እነሆ ቄሳርም ወደቀ በውድቀቱም ክህደትን ተግቶ ሽንፈቱን አወጀ።
አምላካዊነት በሰጠው ነፃ ፍቃድ እንዲያነጻ የአብ ቀኝ የሰው ልጅ ተነሳ፤ ለትንሽ ዲናርም ሲባል ከአስራ ሁለቱ አልማዝ አንዷ ተበጥሳ ወደቀች!።እኛስ ስንት ብሩተስን እናስተናግድ¿ አንድ በአንድ እስክንረግፍ..
Kahlil Gibran says፡
“ጥይቱ ልቤ ላይ ሲያርፍ አልሞትኩም ነበር፤ ማን እንደተኮሰው እስከማይ ድረስ.. ”