*ሙሳ እና ሐሩን* (ዓለይሂሙ ሰላም)
ከ *ክፍል አንድ እስከ ሀያ አንድ*
(ለትውስታ ያክል በጨረፍታ)
በነብዩሏህ ዩሱፍ አማካኝነት የያዕቁብ ልጆች የሆኑት እስራኤላዊያን ከ ሀገራቸው እስራኤል ወደ ግብፅ በመምጣት ሂወታቸውን መምራት ጀመሩ።
ከጊዜም በኋላ ዩሱፍ ይችን አለም ሲሰናበቱ የተተካው ንጉስ እስራኤላዊያንን የማይወድ ዝቅ አድርጎ የሚመለከት በመሆኑ የበታችነት ስሜት ተሰማቸው
በዚህ አላበቃም እየቆየ ስልጣኑ ሲረማመድ ወደ አመፀኛው ፊርአውን ዘንድ ደረሰ
ፊርአውንም ከ እስራኤላዊያን መንደር እሳት ተነስቶ ቤተመንግስቱ ሲቃጠል በህልሙ ያያል ህልሙን ሲያስተረጉምም ስልጣኑን ከእስራኤላዊያን ዘንድ የሚነሳ ሰው እንደሚወርሰው ህልም ፈችወች ነገሩት በዚህን ጊዜ ከባድ ውሳኔ ወሰነ ከ እስራኤላዊያን የሚወለዱ ወንድ ህፃናትን መግደል በዚህም ምክናየት ብዙ ሺ ህፃናትን ገደለ። ህዝቦች ሲያልቁ አንድ አመት ሚወለዱትን መግደል አንድ አመት ደግሞ ባለመግደል ተስማሙ ባማይገደልበት አመት የ ሙሳ ወንድም ሀሩን ተወለዱ።
በሚገደልበት አመት ደግሞ ሙሳ ተወለዱ። እናቲቱ ለማሳደግ ፈራች አላህም አሳድጊው ከፈራሺም በሳጥን አድርገሽ ጣይው ለኔም ለሱም ጠላት የሆነ ሰው ያነሳዋል ወዳንችም እንመልሰዋለን መልክተኛም እናደርገዋለን ይሄ ም እኛ የምንፈፅመው ቃላች ነው አላት።
እሷም በሀር ውስጥ ጣለችው *ፊርአውንም* አነሳው ሊገለው ሲል ሚስቱ አትግደለው ለኔም ላንተም የ አይናችን ማረፊያ ይሆናል አለችው እሺ ብሎ ተወላት ጡት ሚያጠባው ሴት ፍለጋ ተጀመረ አላህ ደግሞ ከ እናቱ በፊት የማንንም ጡት እንዲጠባ አልፈቀደም ሁሉንም ሴቶች አልቀርብ አለ በበሀር ውስጥ ሲጣል እህቱ የት እንደሚደርስ እየተከታተለችው ነበርና ስላማያውቋት ጠጋ ብላ እኔ ጡት የምታጠባላችሁ ሴት ልጠቁማችሁ አለች እሺ አሏት የሷም የሱም እናት የሆነችውን ሴት ጠቆመች እናቱ ማጥባት ጀመረች ሙሳ በ ጠላቱ ቤት አደገ ካደገም በኋላ ሰወች ተጣልተው ሲገላግል አንዱን ግብፃዊ በስተት ገደለው በዚህም ምክናየት እንዳይገሉት በመፍራት ሀገር ጥሎ ወጣ መድየን ወደምትባል ሀገር ሄደ እዛም ሁለት ሴቶችን ከብቶቻቸውን ውሀ የሚያጠጡ ሲሆኑ አገኛቸው እርሱም አጠጣላቸው አንዲቱ ልጅ ተመልሳ አባቴ ያጠጣህበትን ሊከፍልህ ይፈልግሀልና ጥሪው ብሎኝ ነው አለችው ሙሳም ተከትሏት ሄደ አባቷም ከሁለቱ አንዷን ሴት ዳረውና ለ 8አመት ቀጥሮት እዛው መስራት ጀመረ 10 አመት ሲሞላው ቅጥሩን ጨርሶ ወደ ግብፅ ተመለሰ በመመለስ ላይ ሳለ ወደ ጡር ተራራ እሳት ለማምጣት በሄደበት አላህ *እኔ አላህ ነኝ ከኔ ውጭ የሚመለክ አምላክ የለም* ሲል ጠራው የያዘውንም ብትር ጣል አለው ሲጥል እባብ ሆነች አንሳት አለው ወደ ብትርም ተመለሰች እጁንም እጉያው እንዲያስገባ አደረገው ሲያወጣው ነጭ ሚያበራ ሆነ *አላህም* እኒህን ምልክቶች ይዘህ ወደ *ፊርአውን* ሂድ አለው። ከነሱ ሰው ገድያለሁ ይገሉኛል ብየ እፈራለሁና አጋዥ አድርግልኝ ወንድሜ ሀሩንን አለ *አላህም* ጥያቄውን ተቀብሎ እሺ ለ ሀሩንም መልክቴን እልካለሁ ሂዱና ወደ እኔ ጥሩት አላቸው
*ሙሳም* ሂደው መልክቱን ነገሩት ሊሰማቸው ፍቃደኛ አይደለም እኔ አሳድጌህ ከኔ ሌላ አምላክ ሊኖርህ ይችላል ሲል ዛተበት *ሙሳም* ተዐምር ባሳይህስ አሉት እስኪ አምጣ አላቸው የያዙትን አሳዩት ደነገጠ ግን ጓደኛው ሀማን ይሄ ድግምት ነው እኛም የዚህ አይነት ድግምት እናመጣለን ብሎ ፊርአውንን አጃገነው በዙሪያው ያሉትንም መማክርት አማከራቸው ሙሳ ና ወንድሙን እዚህ አቆይ ከዛም ሰብሳቢወችን ላክ ድግምተኞችን ያመጡልሀልና አሉት። ፊርአውንም ሀሳባቸውን ተቀበለ። .......
*ይ ቀ ጥ ላ ል*
t.me/konkwyy