ሰበር ዜና


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources.
Facebook page link https://m.facebook.com/BreakingNewsEthiopia/?ref=bookmarks

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


የውጭ ምንዛሪ ተመን August 2 2024


August 1 2024 exchange rate


የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ከሌቦች የሚረከብ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ማሞ ድልድይ አካባቢ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከማለዳ 12 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ግለሰብ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ባደረገው ክትትል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከሌቦቹ ላይ የሚረከብ " ታምራት ፍቅረማርያም " የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በእለቱ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክና በልዩ ልዩ ጊዚያት ከሌቦች የተረከባቸውን ፦
➡️ 61  ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣
➡️ 251 የታብሌት ስልክ ሽፋኖችን ፣
➡️ 2 ላፕቶፖችን እና በጥሬ 60 ሺ አንድ መቶ ብር ከሌባ ተቀባዩ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ መያዙን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከሌቦች ተቀብሎ የሚያስቀምጠው በተከራየው ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።

ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራይን ማንነነት እና በምን ስራ ላይ እንደተሰማራ የማረጋገጥ ግዴታ እንደለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

" የሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል / ተሰርቂያለሁ " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ስልኩን በመለየትና አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል።

#AddisAbabaPolice


የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

- ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ➡ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 61.16 በሊትር ሆኖ ባለበት ይቀጥላል።

የቤንዚን ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ በሊትር 78 ብር 67 ሳንቲም ገብቷል።


#Ethiopia

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው #መስከረም_ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው #በሁሉም_ዘርፎች ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም #ፕሮፌሽናል_ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ


#AddisAbaba

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

ሀሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ፈተናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን ነው የሚሰጡት ተብሏል።
 
ፈተናው በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺህ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በፈተና ወቅት ተመዛኞች ስልክ ሆነ ማንኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዞ ፈተና ክፍል መግባት እንደማቻል ተገልጿል።

ተመዛኞች ፦

➡️ የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣

➡️ ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና ፈተና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን ፈተናው በፍቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,491 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ቢገለጽም የምዘና ፈተና ለመውሰድ #ስላልተመዘገቡ ወይም ፍቃደኛ ስላልሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ምንም የተባለ ነገር የለም።


#AddisAbaba

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

ታግታ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የተጠየቀባት ህጻን ተገኘች።

የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለች ህፃን ነዋሪነቷ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 " ሳርቤት ' አካባቢ ሲሆን ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ ትታገታለች።

አጋቿ ቸርነት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ነው።

ግለሰቡ ከቤተሰቡ ጋር በነበረው ቅርበት ህፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት እንደነበረ እና ከ5 ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች "ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በሗላ ህፃን አቢጊያ ዳንኤልን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር ቆይቷል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሰጠው በመጠየቅ ገንዘቡን ማግኘት ካልቻለ ግን ህፃኗን በህይወት እንደማያገኟት ሲዝት ነበር።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህፃኗን ለማስመለስ እና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

በተደረገው ክትትልም ዛሬ ሚያዚያ 28/ 2016 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አለም ሰላም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪው ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለ3 ቀናት ያህል ታግታ የቆየችው ህፃን አቢጊያ ዳንኤል ልትገኝ መቻሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ምንም እንኳን ፖሊስ ህጿን መገኘቷን ቢገልጽም አጋቹ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ ያብራራው ነገር የለም።


ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ ታይቷል።

ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን ገልጿል።

" በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል " ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቋል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa


" ፍጹም ሀሰተኛ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል /Rapid Support Forces - RSF/ በሚባል የሚጠራው " የህወሓት ታጣቂዎች ከሱዳን ወታደራዊ ሃይል /SUDANESE ARMED FORCES  SAF/ ጋር በማበር እየወጉኝ ነው " በማለት ያወጣውን መግለጫ ፍጹም ሀሰተኛ እና መሰረተ ቢስ እንደሆነ ገለጸ።

ሱዳን በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች በርከታ ወራት ያለፉ ሲሆን በዚህም የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ደም አፋሳሽ ግጭት እያደረጉ ናቸው።

ታዲያ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል " ህወሓት (TPLF) ከሱዳን ጦር ጋር ሆኖ ወግቶኛል " ብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር  የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መግለጫ ለዘመናት የቆየውና በፅኑ መሰረት የቆመው የትግራይና የሱዳን ህዝቦች ወዳጅነት ከግምት ያላስገባ ነው ብሎታል።

" በሱዳን ያለው የአርስበርስ ግጭት  ዓለምአቀፍ መልክ ለማስያዝና እርዳታ ለማግኘ ያለመ ነው " ሲልም ገልጿል።

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዚሁ የሺዎች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን የአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ላክ የህወሓት ሃይሎች ተሳትፈዋል የሚል ክስ ማቅረቡ " ሃሳባዊና  መሬት ላይ መረጋገጥ የማይችል የለየለት ፈጠራ  " ሲል አጣጥሎታል።

" በመሰረቱ ህወሓት የፓለቲካ ድርጅት እንጂ የሚያዘውና የሚያስተዳድረው ታጣቂ ሃይል የለውም " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ መግለጫ " የትግራይ ህዝብ ከወንድም የሱዳን ህዝብ የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነትና ጉርብትና አለው " ብሏል።

" ከዚህ አኳያ ትግራይ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ነገሮች በማጋጋል የምትገባበት ምክንያትና የምታገኘው ጥቅም የለም " ሲል አሳውቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በሱዳን የተፈጠረው አውዳሚ የአርስ በርስ ጦርነት የሚያስከትለው አደጋ በመረዳት የውጭ ሃይሎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስቧል። 

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa


ትላንት በአዲስ አበባ ፣ በቦሌ ክ/ከተማ " ስካይ ላይት ሆቴል " አካባቢ #እግረኞች ላይ በደረሰ የትራራፊክ ግጭት 1 ሰው ሞቷል። አንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶው " ቸራአሊያ " በሚባል አካባቢ #እግረኛ ላይ በደረሰ ግጭት ደግሞ አንድ ሰዉ ሞቷል።

ልደታ ክ/ከተማም በተመሳሳይ የአንድ ሰው በትራፊክ አደጋ ሞቷል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ደግሞ ቡና በመሸጥ ላይ የነበረችው ወጣት ወደ ኋላ እየሄደ በነበረ ኤፍኤሳር መኪና ተገጭታ ሞታለች።

የመረጃዎቹ ምንጮች የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት / የአዲስ አበባ ፖሊስ (ኢትዮ ኤፍ ኤም) ናቸው።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa


#Hawassa

" እንደሚወራው አይደለም ፤ ከአንድ ቤት በላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም " - የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በሀዋሳ ከተማ የተነሳ የእሳት አደጋ አንድ መዝናኛ ቤት አውድሞ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት አካባቢ በከተማው በተለምዶ 05 በመባል በሚታውቀዉ ሰፈር (አደባባይ አለፍ ብሎ ወይም ከመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት/አስፓልት ተሻግሮ) የተነሳው የእሳት አደጋ አንድ መዝናኛ ቤትን በከፋ ሁኔታ አውድሞ በቁጥጥር ስር ውሏል።

እሳት አደጋው የደረሰው በማህበር ተደራጅተዉ በምግብና መጠጥ ሽያጭ የሚተዳደሩ ወጣቶች ውስጥ በአንደኛው ቤት ነው።

የእሳት አደጋው መፈጠሩን ተከትሎ በአካባቢው ግርግር ቢፈጠርም ከሰአት በኋላ ሁሉም ተረጋግቶ ወደተለመደው እንቅስቃሴ ተመልሷል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የከተማው ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ ፤ " ችግሩ እንደተፈጠረ የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የኢንዱስትሪው መንደር የእሳት ብርጌድ በፍጥነት ደርሶ ተቆጣጥሮታል " ብለዋል።

" ከፍተኛ አደጋ በደረሰበት መዝናኛ ቤት ውስጥ በነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ላይ በተፈጠረ እሳት ነው አደጋው የተፈጠረው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአደጋው በመዝናኛ ቤቱ ላይ ውድመት መድረሱን ጠቁመዋል።

አደጋው በደረሰበት ወቅት በአካባቢው ወደነበሩ ቤቶች እሳቱ እንዳይስፋፋ ሌሎች ሰዎች እቃቸዉን ቢያወጡም ቆይተው ወደቤቶቻቸዉ ተመልሰዋል ብለዋል።

" ከሁኔታው ጋር በተያያዘ ግርግር ቢፈጠርም ሰዎች ተመልሰው ወደ ስራቸዉ ገብተዋል " ሲሉ አክለዋል።

" አደጋው እንደሚወራዉ #እጅግ የከፋ አይደለም " ያሉ ሲሆን ከአንድ ቤት በላይ የከፋ ጉዳት አላደረሰም ብለዋል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa



12 last posts shown.

4 709

subscribers
Channel statistics