⚖️Shields Law🇪🇹 የህግ አገልግሎት / Legal service ⚖️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Law


⚖️ Shields Law ⚖️.
ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች እዚሁ ያገኛሉ። Here on our channel, we provide Free legal Aid. You could alsk get access to laws, cassation decisions, job opportunity updates.
ለማስታወቂያ
👉@alexyoba21

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Law
Statistics
Posts filter


#አዲስ_የሰበር_ውሳኔ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የህግ መሠረት ባለመኖሩ ገዥ ቤቱን ገዝቼዋለሁ በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በሻጭ ሚስት ላይ ህጋዊ ውጤትን የሚያስከትል አይሆንም ሰ/መ/ቁ 224476 በቀን 05/02/2017ዓም የተወሰነ
==========================
የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለዉ ልዩ ባህርይ አንፃር ንብረቱን ከአንድ ወደ ሌላ ሰዉ በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚደረግ ዉል በሦስተኛ ወገን ላይ ህጋዊ ዉጤት ያስከትል ዘንድ ዉሉ በህግ አግባብ በሚመለከተዉ አካል ዘንድ ካልተመዘገበ ውሉ ፈራሽ እንደሚሆንና የፍ/ሕ/ቁ አንቀጽ 2878 ን ዋቢ በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 153664 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ሲሆን በተያዘው ጉዳይም ተጠሪው ይህ አከራካሪ ቤት ከአመልካችዋ ባለቤት ላይ በግዢ ያገኙት መሆናቸውን ከመግለጽ በቀር፤ ቤቱን በግዢ ስለማግኘታቸውና በህግ አግባብ ባለው አካል ዘንድ የግዢና የሽያጭ ውሉ የተመዘገበበት የሰነድ ማስረጃ ተጠሪው በሥር ፍርድ ቤት ያላቀረቡ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን በሰው ምስክር ለማስረዳት የሚችሉበት የህግ መሠረት ባለመኖሩ አመልካቹ ቤቱን ገዝቼዋለሁ በማለት የሚያቀርቡት መከራከሪያ በአመልካችዋ ላይ ህጋዊ ውጤትን የሚያስከትል አይሆንም
https://t.me/Shields_Law


*Law Scholarships In UK 2025 World-Class Education*
Apply Link: https://learningplateform.org/law-scholarships-in-uk/
We will try to cover everything including Eligibility Criteria, the application process, frequently asked questions, and best practices to follow to win these scholarships So let’s get started.




"አንድ ሰው የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ቢሆንም ንብረቱን ይዞ እስካልተጠቀመ ድረስ የውርስ ንብረቱን በያዘው ሰው ላይ የሚያቀርበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000/1/ መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ ቀሪ ነው"በማለት የሰ/መ/ቁ 243973 ላይ በሁሉም ፍ/ቤት አስገዳጅ የሆነ አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል።‌‌

Translation: am-en
"If a person has an atmosphere, the accusation of a person with the man who has the property of the property in the property is at 3 years," / No. 1000/1000 A new state of law is given.‌‌
https://t.me/Shields_Law


https://www.facebook.com/share/p/1D8siMw1MW/

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር እጩዎችን ለህዝብ አስተያየት ከጥር 16 ጀምሮ ለ 10 ቀናት ክፍት አድርጓል:: ከላይ ባለው Links በመጠቀም አስተያየታቹን ስጡ::


በእኛ በኩል ( The Shields Law🇪🇹 free legal service)

በተራ ቁጥር 29 ላይ የተጠቀሱት እጩ ዳኛ አቶ ጌታቸው አስፋው

✍በፍ/ሚኒስቴር ጠ/ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በም/ረዳት ጠ/ዐ/ህግነት የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር አስተባባሪ በመሆን እየሰሩ የሚገኙ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሙያ ናቸው፡፡

✍ከዚህ ቀደም በአብ/ክ/መ በዳኝነት ሀገራቸውን በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት ያገለገሉ ባሉሙያ ከመሆናቸውም በተጨማሪ

✍ከፍተኛ የት/ት ዝግጅት ማለትም (በህግ ሁለት ማስተርስ) ያላቸው ሲሆን

በተጨማሪ በከፍተኛ የሞያ ስነምግባር ስ ራቸውን በመስራት ላይ የሚገኙ የዳኝነት ሞያ የሚያስፈልገውን ጥብቅ ስነምግባር የሚያሟሉ እንዲሁም የተቀላጠፈ ፍትህን በታታሪነት ከዳበረ ልምድ ጋር በማቀናጀት ስራቸውን አክብሮ የሚሰሩ በመሆኑ በዳኝነት ሞያ ሀገሪቷን ቢያገለግሉ ልምዳቸው፣ ስነምግባራቸው እና የትምህርት ዝግጅታቸው በአጠቃላይ ለዘርፉ እንዲሁም ለሀገሪቱ የህግ ስርዓት ላይ የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ የሚችሉ ታላቅ ባለሙያ መሆናቸውን ምስክር መሆን እንችላለን፡፡
።።።።
በመሆኑም ከላይ ባለው Link እየገባችሁ እስተያየት በተራ ቁጥር 29 ላይ ለተጠቀሱት እጩ ዳኛ አቶ ጌታቸው አስፋው እንዲሁም ለሌሎች መስጠት ትችላላችሁ፡፡


~#የሰ/መ/ቁ 273144 ~
ታህሳስ 21 ቀን 2017
#በወ/መ/ሥ/ህ/ቁ 67/ሐ/መሰረት ተከሳሽ በዋስትና ቢወጣ ማስረጃ ሊያጠፋና ምስክር ሊያባብል ይችላል በሚል ዋስትና ሊነፈግ የሚችለው ምስክሮቹ ገና ለፖሊስ ቃላቸዉን ያልሰጡ ሲሆን እንጂ ምርመራ ተጠናቆ መደበኛ ክስ ከተመሰረተ በኋላ አይደለም። በዚህ ምክንያት ዋስትናን መከልከል ከፍርድ በፊት እንደ #ንጹህ_የመቆጠር ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አስገዳጅነት ያለው ትርጉም ሰጥቷል።
https://t.me/Shields_Law


Legal Advisor/ Senior Legal Advisor, Legal Affairs - Funding and Operations - CGIAR

More on: 🔗
https://apply.workable.com/cgiar/j/184E55932D/

Requirements
📮 Advanced University Degree in Law (Masters or Master's equivalent).

📮 Specialized experience at a top-tier law firm and/or in an in-house legal department within a complex international facing corporation or not-for-profit organization. 

📍Addis Abeba | Montpellier

===



8 last posts shown.