የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጥቅምት 20/2016 የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣የአ/አ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት ከሰሞነኛው የኒቃብ ጉዳይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
በዚሁም መሰረት ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለና ዘላቂ መፍትሔ የሚያሻው ከመሆኑ አንጻር የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል መጅሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ዘላቂ እልባት የሚያመጣ የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ተደርሷል።
ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ በጊዜያዊነት ከመገለላቸው #በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል ሲል ምክር ቤቱ አሳውቋል።
ከፍተኛ ምክር ቤቱ ቀሪውን ስራ በትኩረት የሚያከናውን መሆኑን ገልፆል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/+D9SY4VrC-i8wYTc0