"በማን ሚዛን?"
እርጋታው ይመስለኛል ያሸነፈኝ። ብዙ አይናገርም ግን በሚናገርበት ሰዓት አንባቢነቱን ከቃላት አጠቃቀሙ እና ከቁጥብነቱ ይታወቅበታል። ሁሉም ነገር ላይ መመጠን እና ማመዛዘንን ያውቅበታል። ሰላምታው ላይ መጠነኛ ፈገግታ አለች። ፈገግታውን ለሚሰጠው ሰው ብቻ ፈገግ የሚል የምታስመስል ለየት ያለች እርግትትትትት የምታደርግ ፈገግታ። በየትኛውም ጉዳይ ላይ ጥያቄ ሲመጣበት ለመመለስ ከሚቸኩለው በላይ "እኔ ብዙም እውቀቱ የለኝም" የሚለውን ማስቀደም ይቀናዋል። እውነታው ግን የ እውቀት ባለቤት መሆኑ ነው። በተፈጥሮ ቀዝቃዛ የሚባል አይነት ነው። አይቸኩልም። በህይወቱ ላይ ለነገሮች የሚሰጠው ቦታ የተመጠነ ነው። "ቢመጣም ባይመጣም"አይነት። ዲኑ ላይ ያለው አቋም ይደንቀኛል። አይለፈልፍም። ቁርኣን ሲቀራ ድምፁ ያፈዛል። " ሰው በሰደቃው ነው የሚጠበቀው" ይላል ደጋግሞ
አንድ ቀን ቡና ልንጠጣ ተገናኘን። ስመጣ ብድግ ብሎ አስቀመጠኝ። ፊቱ ላይ የተለመደው እርጋታ ነው ያለው።
"ለ ትዳር እፈልግሻለሁ" አለኝ
" እኔን?" አልኩ በድንጋጤ። አንገቱን በ አዎንታ ነቀነቀው
" ካንተ ማንነት ጋር የሚሄድ ማንነት የለኝም። ባንተ አዋቂነት ስመዘን እኔ እልም ያልኩ ጃሂል ፣ ባንተ እርጋታ ስለካ እኔ እልም ያልኩ እብድ ነኝ፤ ካንተ ንጽህና አንጻር ያደፈ ልብ ያለኝ ነኝ አልሆንህም" ሳልፈልገው ቀርቼ አልነበረም። የጠራ ማንነቱ ከኔ ጋር ሲዋሃድ የሚደፈርስ መሰለኝ እና "ልቅርብህ" አልኩት።
"በማን ሚዛን ተመዝነን?" አለኝ።
"እኔ ዱዓ አድርጊያለሁ። ከጌታዬም ኸይር የሆነ ምላሽን እክጅላለሁ። ጊዜሽን ወስደሽ መልስ ትሰጪኛለሽ አለኝ።" እርጋታው መለያው አይደል። ስክንንን እንዳለ ነው የሚያወራው።
ከአመታት በኋላ ከ እናቴ ጋር ቁጭ ባልንበት እህቴን በሚያማምር ቃላት ስትመርቃት ሰማሁ። "ምናለ ለኔም ብታደርጊልኝ?" ብዬ ቀናሁ። " የተሻለውን ዱአ አድርጌልሽማ መልሴን አገኘሁ" አለች። ባሌን ነው። ያን የተረጋጋውን ሰው፣ ያ ልቡ የሰከነች ሰው አገባሁት።
"በማን ሚዛን?" የሚለው ጥያቄው እስካሁን በህይወቴ እጠቀመዋለሁ።
@sumeyasu
@sumeyaabot