طالبات العلم "ጧሊበተል ዒልም"


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ጧሊባቱል ኢልም የቂርአት እና የቲሞችን መርጃ ማእከል
https://t.me/joinchat/AAAAAEiNUs3gAKq0F39w0g
@Talibatul1ilm_bot
ይህ 👆 የአስተያየት መስጫ ነው ያሎትን አስተያየት ያካፍሉን

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


قال صلى الله عليه وسلم:
‏ (أكثروا الصلاة عليَّ يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى عليَّ صلاة صلى الله عليه عشراً) ‏
البيهقي

صلى الله عليه وسلم
صلى الله عليه وسلم
صلى الله عليه وسلم


ዘግይቶ ወደ ጀማዐ ሶላት የሚቀላቀል ሰው
~
1- ወደ ሶላቱ ሲገባ ተረጋግቶ እንጂ እየተዋከበ መምጣት የለበትም። ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ቢያየው እንኳ መሮጥ የለበትም።
2- የተጀመረ ሶፍ ሳይሞላ ጥሎ ለብቻው መቆም ወይም አዲስ መጀመር የለበትም።
3- እንደደረሰ ኢማሙን ባለበት ሁኔታ ሊከተለው ይገባል። እንጂ ሶፍ ላይ ቆሞ ኢማሙ እስከሚቆም ወይም ለተሸሁድ እስከሚቀመጥ መጠበቅ የለበትም። ሩኩዕ ላይም ይሁን ሱጁድ ላይም፣ ተሸሁድ ላይም ቢሆን ይከተለው።
4- ኢማሙን መከተል ከመጀመሩ በፊት ወደ ሶላት መግቢያ የሆነውን ተክቢረተል ኢሕራም ሊዘነጋ አይገባም። ያለ ተክቢረተል ኢሕራም ሶላት ውስጥ እንደገባ አይቆጠርምና። ተክቢረተል ኢሕራም ቆመን ነው ማለት ያለብን። እየወረድን፣ እየተንቀሳቀስን አይደለም።
5- ኢማሙን ቆሞ ካላገኘው ከተክቢረተል ኢሕራም ቀጥሎ የሚቀራውን የመክፈቻ ዱዓእ አይቀራም። (ለምሳሌ
سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، وَتَبَارَكَ اسْمُكَ وَتَعَالَى جَدُّكَ، وَلَا إِلَهَ غَيْرَكَ)
የመክፈቻ ዱዓእ ቦታው ቂያም (መቆም) ላይ ነው። ተክቢራ ካደረገ ጀምሮ ኢማሙን መከተል ግዴታው ነው። ስለዚህ ኢማሙ ቂያም ላይ ካልሆነ ግዴታ ባልሆነ ነገር ኢማሙን ከመከተል ሊዘናጋ አይገባውም።
6- ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ከደረሰበት ሙሉ ረከዐውን እንዳገኘ ይቁጠረው። ነብዩ ﷺ እያሰገዱ ሩኩዕ ላይ እያሉ ሶሐቢዩ አቡ በክረህ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ደረሰ። ሶፍ ሳይደርስ ኢሕራም አድርጎ ከዚያም ሩኩዕ በማድረግ ፈጥኖ ከሶፉ ተቀላቀለ። ነብዩ ﷺ ሶላት ካጠናቀቁ በኋላ "አላህ ጉጉትን ይጨምርልህ። ግን እንዳይደገምህ" አሉት። "እንዳይደገምህ" ያሉት መፍጠኑን ነው። እንጂ ሩኩዕ ላይ የደረሰበትን "ስለማይቆጠር ተነስና አንድ ረከዐ ጨምር" አላሉትም። ሩኩዕ ላይ መድረስ የማይቆጠር ቢሆን ኖሮ አንድ ረከዐ እንዲጨምር ያዙት ነበር። ልብ በሉ! አቡበክራ የፈጠነው ሩኩዕ ላይ ለመድረስ ነው። ሩኩዕ ላይ መድረስ የማይቆጠር ቢሆን ኖሮ አቡ በክራ ሩኩዑን ለማግኘት ባልተቻኮለ ነበር። ይሄ ተግባሩ ሶሐቦች ዘንድ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን ግንዛቤ ያሳየናል።
በነገራችን ላይ ሩኩዕ ላይ ሲደርሱ ሙሉ ረከዐ አድርጎ ማሰብ ከሌሎችም ብዙ ሶሐቦች ተገኝቷል። እንዲያውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሰለፎች ዘንድ ልዩነት የለም ይላሉ ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ።
7- ያለፈው ረከዐ ካለ ኢማሙ ሳያሰላምት በፊት የጎደለውን ለመሙላት እንዳይነሳ። ይልቁንም ኢማሙ ማሰላመቱን ካረጋገጠ በኋላ ተነስቶ የጎደለውን ይሙላ።
8- ያለፈው ረከዐ ካለ ከኢማሙ ጋር ያገኘው ለሱ የመጀመሪያው ነው። ለምሳሌ ሶላቱ ዒሻእ ቢሆንና ኢማሙን 4ኛ ረከዐ ላይ ቢያገኘው ለሱ የመጀመሪያ ረከዐው ነው። ስለዚህ ኢማሙ ሲያሰላምት የሚነሳበት ረከዐ ለሱ 2ኛው እንጂ የመጀመሪያ ረከዐው አይሆንም። ስለሆነም በዚህ በ2ኛ ረከዐው ላይ ለተሸሁድ ይቀመጣል ማለት ነው። ሌሎቹንም በዚሁ መልኩ ይፈፅማል።
9- ሌሎች እንደሱው ያለፋቸው ሰዎች ከሌሉ ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው የመጀመሪያ ረከዐዎች ላይ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይቅራ። ሌሎች ያለፋቸው ኖረው ሁሉም ድምፃቸውን ከፍ ቢያደርጉ የሚረባበሹ ከሆነ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ይቀራል።


ሁሌም ውብ የሆኑ ነገሮች
ከከባባድ ችግሮች ጀርባ ነው የሚመጡት።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ውድ እህቶቻችን ባወጣ አላህ ይተካችሁ
እቃወቻችሁንም ለመውሰድ ሞክሩ


➘በህይወታችን
ትልቁ ድክመት ተስፋ መቁረጥ ነው።
ህይወት ሁሌም የትግል መድረክ ናት! 

ተስፋ ያልቆረጠ የትግሉን መድረክ ያሸንፋል።


╰┈⫸☛የለሊት ሶላትን በተመለከተ☚⫷┈┈╯

ረሡል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድህ  አሉ፦
በላጩ ሶላት ከፈርድ ሶላት በኋላ የለሊት ሶላት ነው አሉ።
📚 ሷሒሕ ሙስሊም(1163)


~ አቡ ደርዳአ እንዲህ ይላሉ ፦
እኔ በጣም የምፈራዉ ነገር የቂያማ እለት ለሂሳብ ስቆም፦ባወከዉ ምን ሠራህ እንዳልባል ነዉ።


➘ኢማሙ ሻፊኢይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፦

~በምላስህ የሰውን ነውር አትጥቀስበት, አታውሳበት..!!

~ምክነያቱም ለአንተም ነውሮች አልሉህ, ለሰዎችም ምላሶች አልሉዋቸው..!!


“የተስፋ መቁረጥ ንፋስ ጀልባችንን ቢያናውጥ
በአል ረሕማን እዝነት መልካም ማግኘታችን ያድነናል።
ጌታችን አላህ መሆኑ ይፈውሰናል።

ከአላህ ትንሽ አትመኙ ሁሉም የተመኘውን ያገኛል ያለመውን ይይዛል ከአላህ ዘንዳ ያለው አያልቅምና…


~የሰዎችን መጥፎ ጎን ብቻ ለማስታወስ ከተቀመጥክ ለማንም ውዴታ አይኖርህም። ፍፁም ንፁህ ስለማይኖር ቅርብ ሰዎችህን እንኳን ባልተለመደ መልኩ በጥቁር ዓይን መመልከት ትጀምራለህ። ከዚያ ቀንህም አያፈካህም፣ ሌሊትህም አያሳርፍህም። አንዳንዴ መጥፎ ጎናቸው ጋር  ስትደርስ አይንህን ስበር፣ አይቶ እንዳላየና ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍንም ተለማመድ።አንዳንዴ «መርሳት»ን እንደ ትራስ ተደገፈው። አንተም አጠገብህ ያሉትም ሰላም እንዲሆኑ።


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣9️⃣3️⃣


...~°ቁርአን የልብሰላም~°...

ቁርኣን እንደ ውቅያኖስ የጠለቀን ደስታን
ይሰጥሃል፤ ባዶነት የተሰማውን ማንነትህን
በደስታ ሀሴት ይሞላዋል።


አራት(4) ነገሮች ያለበት ሰው ከዱንያ ምንም ነገር አላጣም። ዱንያ ብትቀንስበት ምንም ነገር አይጎዳውም።

~ አማናን ጠባቂ፣
~ እውነትን ተናጋሪ፣
~ መልካም ስነምግባር ያለው ሰው እና
~ ከሀላል የሚበላና የሚጠጣ ሰው ናቸው።


|«ልጄ ሆይ…» አሉ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት። ወደ ሕይወት ትግል ገና እየተቀላቀለ የሚገኝ ጎረምሳ ወጣትን እየተመለከቱ።

•ልጄ ሆይ… መጠበቅህን አደብ አሲዘው። የመጠበቅ ልጓምህን ተቆጣጠረው።
የኔ ልጅ ሰዎች መጥፎ ነገር በማድረግ ብቻ አይጎዱህም። ልብህን በአጉል ተስፋ አንጠልጥለው ከጌታህ ጋር ሊያጣሉህ ይችላሉና ተጠንቀቅ።

• ልጄ ሆይ… ሕይወት እንደ እናትህ ልብ አይደለችም። አትራራልህም። እንደ አባትህም እቅፍ አይደለችም። እንዳይበርድህ ሙቀት አታቀብልህም። ሕይወት የወቅት ዘመድ ነች። የአሁን ሁኔታ ነች።»

• ልጄ ሆይ ወደ ልብህ የዘለቀን አክብር። የተለየህን አትጥላ።
• ልጄ ሆይ… ሰዎች በመጥፎ ምግባር ላይ ስላየሀቸው ብቻ አትፍረድባቸው። በምታውቀው እኩይ ምግባር ላይ ስለተገኙ አትጠየፋቸው። ይህን ልብ አድርግ አላህ ምርጥ ነብያቶቹን በእጅጉ ቆሽሸው ለነበሩ ሰዎች ልኮ የቆሸሹትን አፅድቶ እንዳስከበራቸው።
• ልጄ ሆይ!  ወንድሞችህ ከፊርዓውን የባሱ አይሆኑምና ከፊርዓውን ያነሰ ክብር ሰጥተህ አታዋርዳቸው። የአላህ ነብይ ሙሳ ፊርዓውንን በለዘብታ ቃል እንዲያናግረው መታዘዙን ዘንግተህ በወንድሞችህ ላይ አጉል አትጩህ!


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣9️⃣2️⃣


ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣9️⃣1️⃣


የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
"ሱጁድ ላይ ተስተካከሉ። አንዳችሁ እንደ ውሻ ክንዶቹን አያንጥፍ።" [ቡኻሪይ ዘግበውታል።]


ወዱእ ያለው መስሎት ያለ ውዱእ የሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና መስገድ አለበት። ያለ ውዱእ ሶላት የለምና። ያስታወሰው ወቅት ካለፈ ቢሆን እንኳ ሶላቱን መመለስ አለበት።
ኢማሙ ረስቶ ያለ ውዱእ ካሰገደስ? የተከታዮቹ ሶላት ይበላሻል?
* ሶላቱ ሳይጠናቅቅ ካስታወሰ መቀጠል የለበትም። ይልቁንም ሌላ ሰው ተክቶ ይወጣል። የተተካው ሰው ከመጀመሪያ መጀመር ሳይጠበቅበት የቀረውን ያሰግዳል።
* ኢማሙ ውዱእ እንዳልነበረው ያስታወሰው ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከሆነ ግን የተከታዮቹ ሶላት ትክክል ስለሆነ መመለስ (ዳግም መስገድ) አይጠበቅባቸውም። ይህንን የኢብኑ ዑሠይሚን ፈትዋ ማየት ትችላላችሁ።


ኹፍ ወይም ካልሲ በጦሀራ የለበሰ መስሎት አብሶ የሰገደ ሰው ኋላ ላይ በጦሀራ ሆኖ እንዳልለበሰው ካስታወሰ ውዱኡንም ሶላቱንም መመለስ አለበት። ማለትም እንደገና ውዱእ አድርጎ መስገድ ይኖርበታል። ያለ ውዱእ የተሰገደ ሶላት ዋጋ የለውምና።


ረስቶ ያለ ውዱእ የሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና ይሰግዳል። ምክንያቱም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تقبل صلاة بغير طهور
"ያለ ውዱእ ሶላት ተቀባይነት የላትም።" [ሙስሊም]

لا تقبل صلاة أحدكم إذا أحدث حتى يتوضأ
"ያንዳችሁ ሶላት - ውዱእ ካጠፋ - ውዱእ እስከሚያደርግ ድረስ ተቀባይነት የለውም።" [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

* ሳያውቅ ወይም ረስቶ በተነጀሰ ልብስ ወይም ጫማ ከሰገደ በኋላ ያስታወሰ ግን ሶላቱን አይመልስም። መሀል ላይ ካስታወሰ የሚመቸው ከሆነ የተነጀሰውን ጥሎ ባለበት መቀጠል ይችላል። ማስረጃው ነብያችን ﷺ በአንድ ወቅት እያሰገዱ እያሉ ጂብሪል ጫማቸው ላይ ነጃሳ እንዳለ ሲናግራቸው አወለቁ። ሶላታቸውን እንደገና ከመጀመር ይልቅ ባለበት መቀጠላቸው ያላወቀ ሶላቱ እንደማይበላሽ ይጠቁመናል።

20 last posts shown.