Temari News


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ተማሪዎች ነክ መረጃ የምታገኙበት ቻነል!
- ስለ 12ኛ ክፍል ውጤት
- ስለ Remedial
- ስለ Exit exam
- ስለ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ
- ለሁሉም ደረጃ ተማሪዎች Notes
Contact: @Shimshon01
If not online: @BihereZ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


#የጥሪ_ማስታወቂያ
#RayaUniversity

ራያ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ የተመደቡ (freshman) ተማሪዎቹ እና በ2018 ሪሚድያል ፕሮግራም ተከታትሎ ማለፊያ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ጊቢ የሚገቡበት ቀናት ከጥቅምት 16 እስከ 18 /2019 መሆኑን አሳዉቀዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች ፎቶውን ይመልከቱ።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


TUTOR SPOT ACADEMY  ONLINE  TUTOR

🔥 GRADE 12 NATIONAL EXAM PREPARATION — REGISTRATION IS NOWOPEN! 🎓

Ready to take your exam preparation seriously? 🚀
🟢NATURAL SCIENCE | 🟡SOCIAL SCIENCE

✅ WHAT YOU'LL GET:
           ✅ Live classes
           ✅ Exam-focused lessons
           ✅ Past & practice questions
           ✅ Regular tests & assignments
           ✅ Dedicated tutors

⏰️ Your preparation starts now—not the week before the exam!

📝 Register now:
👉 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdeAYveACgDB9O78bFe_QkpuZckNo0uvAbeZhmOpBCdMGF1Jw/viewform?usp=publish-editor


#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም በማስተርስ እና በፒ.ኤች.ዲ ፕሮግራሞች ቅበላ ላገኙ አመልካቾች ጥሪ አድርጓል።

በምስሉ ላይ በተገለፁት 16 የድኅረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ቅበላ ያገኛችሁ አመልካቾች ከመስከረም 26-28/2019 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

አመልካቾች በተገለፁት ቀናት ብቻ ሪፖርት እንዲያደርጉ ያስገነዘበው ዩኒቨርሲቲው፤ ትምህርት ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም እንደሚጀምር ገልጿል።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#Y12HMC

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዲግሪ ፕሮግራም (Doctor of Medicine) ለመማር ላመለከቱ የምልመላ ጊዜው መራዘሙን ገልጿል።

የፅሑፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 👇
ሰኞ ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰዓት

የቃል ፈተና የሚሰጥበት ቀን 👇
ሐሙስ ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰዓት

አመልካቾች የተጠቀሱትን ቀናት በማወቅ ለፈተናዎቹ ዝግጅት እንዲያደርጉ ኮሌጁ አስገንዝቧል።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጂኦተርማል ኢንጂነሪንግ እና በጂኦተርማል ጂኦሳይንስ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ለመጀመር የውጪ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሒዷል።

በዩኒቨርሲቲው የማዕድን ፍለጋ፣ ማውጣት እና ማበልፀግ የልህቀት ማዕከል የውጪ ስርዓተ ትምህርት ግምገማውን አድርጓል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከማዕድን ሚኒስቴር ከቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኦፐሬሽንስ እና ከኮርቤቲ ጂኦተርማል የተውጣጡ ባለሙያዎች በስርዓተ ትምህርት ግምገማው ተሳትፈዋል።

የሚጀመሩ የማስተርስ ፕሮግራሞች
✔️ MSc in Geothermal Geoscience
✔️ MSc in Geothermal Engineering

የሚጀመር የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራም
✔️ PhD in Geothermal Geoscience

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️⤵⤵

✅እንደሚታወቀው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ላይ ወሳኙ ነገር መረጃና የትምህርት ማቴሪያል ማግኘት ነው።

➡️ ለሱም መፍትሔው⬇️⬇️⬇️

https://t.me/+_E1yBqxqkXsxNDhk


የትምህርት ሚኒስቴር በባሕር ዳር ከተማ በ 1.4 ቢልዮን ብር ወጪ የሚገነባውን የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀመረ።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎችም የክልል እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር መሪዎች ተገኝተዋል።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


🎓 የጥሪ ማስታወቂያ

ጅማ ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቹ ጥቅምት 4 እና 5 ጥሪ አድርጓል።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews

15.7k 0 103 11 64

#ጥቆማ

እንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም ክፍያ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ይማሩ!

ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ለማሻሻል ባዘጋጀው ፖርታል ይጠቀሙ! ብቃትዎን ያሳድጉ!

ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጀ ነው።

በድምፅ፣ በፅሑፍ እና በምስል በተቀናበሩ ማስተማሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያስችል ትምህርት ያገኛሉ።

ፖርታሉ በስማርት ስልክ፣ በስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌት እና በኮምፒውተር ዌብ መፈለጊያ ላይ ይሰራል፡፡ ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት የሚያስፈልግ ቢሆንም ገንዘብ አይቆርጥም።

ወደ ፖርታሉ ይግቡ👇
http://learn-english.moe.gov.et

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም ያስቀመጠውን የዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ ያመጡና በፖሊስ ሙያ ዘርፍ ለማገልገል የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአራት ዓመታት በፖሊስ ሳይንስ በዲግሪ ፕሮግራም አስተምሮ በረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ በማስመረቅ በፌደራል ፖሊስ የሥራ ክፍሎች በማስመደብ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

መስፈርቶች፦
➻ በፖሊስ መኮንንነት ሀገሩን ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ያላት፣
➻ ከወንጀል ነጻ ስለመሆናቸው ከሚኖሩበት አካባቢ ፖሊስ ጽ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
➻ ለፖሊስ ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና የአዕምሮ ጤንነት ያለው/ያላት፣
➻ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/የሆነች፣
➻ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣
➻ ከተመረቁ በኋላ ለሰባት ዓመታት በተማሩበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ተመድቦ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ፣
➻ ሴት አመልካቾች ከእርግዝና ነጻ መሆን አለባቸው፣
➻ ከዚህ በፊት የፖሊስ/የመከላከያ ስልጠና ያልወሰዱ፣
➻ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጥን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ።

በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ መቁረጫ ውጤት ያላቸው ወይም በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት የማለፊያ ውጤት ያመጡ ማስረጃ በማቅረብ ማመልከት ይችላሉ።

➻ ቁመት፦ ለወንድ 1.65 ሜ. እና ከዚያ በላይ ፤ ለሴት 1.55 ሜትር እና ከዚያ በላይ
➻ ዕድሜ፦ ከ18 እስከ 28 ዓመት

በትምህርት ወቅት ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ፣ የምግብ እና የጤና አገልግሎት በተቋሙ ይሸፈናል።

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://forms.gle/cPBiWRzUDx4KFRiq9

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#InjibaraUniversity

ለሪሚድያል ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ (በኤክስቴንሽን መርሃ ግብር)

📚 ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣 ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#WoldiaUniversity

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ2019 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተር (Postgraduate Diploma in Alternative Teacher Education) በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የስልጠና ዘርፎች፡-
Mathematics, Biology, Chemistry, Economics, English, Information Communication Technology, Physics, History and Geography.

መስፈርቶች፡-
● አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ያላቸው፣
● በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው፣
● ከመንግሥት ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ ስለመመረቃቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
● ከግል ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣

የማመልከቻ ጊዜ 👇
ከመስከረም 21-29/2019 ዓ.ም


የማመልከቻ አማራጮች 👇
በዩኒቨርሲቲው ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 41 በአካል በመቅረብ ወይም ኦንላይን ለማመልከት የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረ-ገፅ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊ መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባችኋል።

ለመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች የመኝታ፣ ምግብ እና ጤና አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በመንግሥት የሚሸፈን ይሆናል። የእረፍት ቀናት አመልካቾች የትምህርት ወጪያቸውን ራሳቸው የሚሸፍኑ መሆኑ ተገልጿል።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


የተጠባባቂ ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቃል!

ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2019 ዓ.ም የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ላወጣው ማስታወቂያ ፈተና ወስዳችሁ #ተጠባባቂ የሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ምዝገባ እንድታደርጉ ሚኒስቴሩ መግለፁ ይታወቃል፡፡

የምዝገባ ጊዜው ዛሬ መስከረም 21/2019 ዓ.ም ይጠናቃቀል፡፡

በቀሩት ሰዓታት ውስጥ https://sbs.moe.gov.et/apply ላይ በመግባት፣ ስማችሁን እና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት ምዝገባ ያድርጉ፡፡

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#InjibaraUniversity

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የ2ኛ ዲግሪ (በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች) እንዲሁም የ3ኛ ዲግሪ (በመደበኛ መርሐግብር) ትምህርት ለመከታተል ያመለከታችሁ በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 25-27/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ የተባለ ሲሆን፣ ትምህርት መስከረም 28/2019 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


⚙️ #CampusGrowthSystems (በካምፓስ ውስጥ የትምህርትና የመሪነት አቅምን ማሳደጊያ ስልቶች)

🟢 The Senior Mentor Loop (የበላይ ዓመት ተማሪዎችን ልምድ መጠቀም)፦ ከከፍተኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር አላስፈላጊ ወሬ ከመወያየት ይልቅ፣ ከዚህ ቀደም የሰሩአቸውን የላብ ሪፖርቶች፣ አሳይመንቶችና የፈተና ጥያቄዎች (Past Papers) ጠይቀህ ያዝ። ይህ ጥናትህን ከባዶ ከመጀመር ያድነሃል።

🟢 Assignment Micro-chunking (አሳይመንቶችን ከፋፍሎ መስራት)፦ ትልቅ የካምፓስ ፕሮጀክት ወይም አሳይመንት ሲሰጥህ እስከ መጨረሻው ቀን አታቆየው። በየቀኑ ለ15-20 ደቂቃ ብቻ ክፍለ-ጊዜ በመስጠት በትንሹ ስራው፤ የመጨረሻው ቀን ሲደርስ ያለ ምንም ጭንቀትና Panic ስራህን ታጠናቅቃለህ።

🟢 Strategic Study Pods (ውጤታማ የጥናት ቡድን መመስረት)፦ ከጓደኞችህ ጋር የምታደርገውን ጥናት (Group Study) ጨዋታ ብቻ እንዳይሆን ቁጥሩን ከ3-4 ሰው አትእለፍ። እያንዳንዱ ሰው አንድ ቻፕተር አዘጋጅቶ ለሌሎቹ እንዲያብራራ (Peer Teaching) ስራ ክፍፍል አድርጉ።

🟢 Campus Event Monetization (የካምፓስ ዝግጅቶችን ለዕድል መጠቀም)፦ በካምፓስ ውስጥ በሚዘጋጁ ፓነሎች፣ ወርክሾፖች ወይም ውድድሮች ላይ ተሳትፎ አድርግ። በነዚህ ዝግጅቶች ላይ የሚመጡ የውጭ እንግዶችንና መምህራንን ቀርበህ በማናገር ለቀጣይ የኢንተርንሺፕና የስራ ዕድሎች መንገድ ክፈት።

📚ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#AASTU

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ለቅድመ-ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ያመለከታችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ነገ መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ አዲሱ ዲጂታል ላይብራሪ ህንጻ ቁ. 46 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ከላይ በተያያዘው ምስል ዝርዝር ውስጥ ስማችሁ ያልተጠቀሰ አመልካቾች ያለመግቢያ ፈተና የምትመዘገቡ መሆኑን ተገልጿል።

ለፈተና የምትቀርቡ አመልካቾች ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ምንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደመፍተኛ ክፍል ይዞ መግባት እንደማይቻል ተመላክቷል።

📚 ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣 ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#ጥቆማ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዲግሪ ፕሮግራም (Doctor of Medicine) አመልካቾችን እየተቀበለ ነው።

ኮሌጁ በሁለት አማራጮች ማለትም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ (Generic) እንዲሁም በአዲስ ኢኖቬቲቭ የሕክምና ትምህርት ኢኒሼቲቭ (NIMEI) አመልካቾች በመቀበል ላይ ይገኛል።

ያሉ ክፍት ቦቻዎች ➻ 80
በመንግሥት ስፖንሰር ➻ 40
በግል ስፖንሰር ➻ 40

የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 22/2019 ዓ.ም ምሽት 12:00

የፅሑፍ ፈተና መስከረም 27/2019 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን የቃል ፈተና ጥቅምት 01/2019 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

(ለማመልከት የሚያግዝ ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

📚 ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣 ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ለፕሬዝዳንት እና ለሦስት ምክትል ፕሬዝዳንት የአመራርነት ሥራ መደቦች ላይ ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፡፡

ለውድድር ክፍት የሆኑ የአመራርነት ሥራ መደቦች፦
➻ ፕሬዝዳንት
➻ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት

ከላይ በተያያዘው ምስል የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ የስራ ቀናት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንጻ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁ. 106 ወይም በአዲስ አበባ በሚገኘው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

(ዝርዝር ማስታወቂው ከላይ ተያይዟል፡፡)

📚 ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣 ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews


Physical Fitness Module final - FINAL.pdf
2.4Mb
Revised History Module 2024-3 (1).pdf
62.0Mb
First Semester Freshman Courses For Natural Science Students


📚 ለትምህርት መፅሐፍት
💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes

📣 ለትምህርታዊ መረጃዎች
💻 @TemariNews 💻 @TemariNews

20 last posts shown.