Day 5
እነዚያ ጠቢባን በኮከብ እየተመሩ ሲመጡ ሕፃኑን ንጉሥ ተራ ስፍራ ግርግም ውስጥ እንጂ ቤተ መንግሥት ውስጥ አላገኙትም። ንግሥናውንና ማንነቱን አምነው በሕፃኑ ፊት ሰገዱለት። ነገር ግን ይህ ትእይንት ስለ አምልኮ ብቻ አይደለም። ርሱ ከተወለደ በኋላ ስላለው ጥልቅ ዐላማም እንጂ። በበረት ውስጥ የተወለደው ያ መሲሕ፥ በሰው ልጆችና በእግዚአብሔር መካከል ድልድይ ኾኖ የሚጫወተው ሚና እጅግ ታላቅ ነው። ለእኛ ሲል የታገሠውን ሞት አስታውሱ። ሕይወቱ ከልደት እስከ ሞቱ ድረስ የኀጢአትንና የሞትን ኀይል ለማሸነፍ፣ ለሚያምኑ ኹሉ የዘላለም ጥያቄ መልስ ኾኖ የተገኘ ብቸኛ መፍትሒ ነው። ከእኛ ፈጽሞ ሩቅ የኾነው አምላክ እንደኛ ኾኖ በመካከላችን ተገኘ ። በርሱ የሚያምኑ የሰው ልጆች ኹሉ አምላክ ወደሚኖርበት ከተማ መድረሻ ብቸኛው መግቢያ በር ኾኖልን መጥቷል። ዛሬም ርሱን እንዲያገኙትና ሕይወትዎን ለርሱ በመስጠት ውስጥ ያለውን ጥልቅ ደስታ እንዲለማመዱ ተጋብዘዋል። ርስዎን ፍለጋ ከሰማይ ድረስ ወደመጣው አዳኝ አኹኑኑ በመምጣት ከዘላለም ቅጣት ይትረፉ። ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!
#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ
Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest

" ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና እጣን ከርቤም አቀረቡለት" (ማቴዎስ 2፥11 )