ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አሳወቀ።
ኩባንያው ኤአይን በመጠቀም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች ወደ ስልኩ አምራች ተቋም ሪፖርት የሚያደርጉበት አሰራርን ዘርግቻለሁ ብሏል።
አዲሱ የጎግል አሰራር የስልክ ንጥቂያ ወንጀሎችን ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል።
ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩ እና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡
ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡