#ሁሉም_ለበጎ_ነው !
አንድ ሰው ባህር ላይ ብቻውን እየተጓዘ እያለ፤ በማዕበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩ ውሰጥ ይሰምጣል። ሰውዬው እንደምንም ራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፋል። ከዛም ደሴቷ ላይ ጎጆ ነገር ይሰራና ለብቻው ዓሳ እያጠመደና እየተመገበ ብዙ ቆየ።
አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ ሲሄድ፤ በመሀል ጭስ ይሸተዋል። ዞር ብሎ ሲመለከት፤ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነበር። እየሮጠ ቢመለስም ጎጆውን ሊያድናት አልቻለም። ለካስ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ኖሮ ጎጆውን አንድዶታል። ሰውየውም:- "እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለከኝና ከቤተሰቦቼ ነጥለክኝ ስታበቃ፤ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ?!" ብሎ ፈጣሪውን አማረረ!
ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ድምጽ ሲሰማ፤ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ ሲያይ ተደሰተ። የመርከቡ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት። ከዚያም ለሰዎቹም:- "እዚህ አካባቢ (ባህር) ላይ ማንም አይመጣም። እናንተ እንዴት አገኛችሁኝ?" ብሎ ጠየቃቸው። መርከበኞቹም:- "እኛ እየተጓዝን ነበር። ጭስ ስናይ ሰው ይኖራል ብለን ስንመጣ፤ አንተን አገኘንክ!" አሉት። "አቤት ጌታዬ! ለካ ከዚህ ስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ኖሯል፤ ትንሿን ጎጆዬን አፍርሰክ ወደ ትልቁ ቤቴ የወሰድከኝ!" አለ።
አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ (ሲበላሽብን)፤ ፈጣሪንም፣ ሰውንም እናማርራለን። ነገርግን ካጣነውና ከጎደለብን ነገር ጀርባ፤ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን። በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን ጌታችንን እንረሳለን። ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን። ጌታችን! አዕምሯችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን!
መልእክቱ አስተማሪ ሆኖ ካገኙት 𝙡𝙞𝙠𝙚 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 እያደረጋችሁ አበረታቱን።
✨@tksa_tks