የ129 የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ ሃሰተኛ ሆኖ ተገኘ
የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ የ129 የፌዴራል መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ ሃሰተኛ ሆኖ መገኘቱን ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2017 የበጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበቡት ወቅት እንደተናገሩት ትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞችን የትምህርት መረጃ የማጣራት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
በመጀመሪያ ዙር ከ280 የፌዴራልና ተጠሪ ተቋማት መስሪያ ቤቶች ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተላከው መረጃ መሰረት የ32 ሺህ 815 ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት መጣራቱን አብራርተዋል።
በዚህም 129 ሀሰተኛ የትምህርት ማሰረጃ የተገኘ ሲሆን፤ የ469 ሰራተኞች መረጃ ያልተሟላ በመሆኑ ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተመላሽ ተደርጓል ብለዋል።
ከዚህ በኋላ የዲፕሎማ ትምህርት ማረጋገጫ ወረቀት በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ታትሞ የሚሰጥ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት በዩንቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው ሂደት እንደማይቀጥል ተናግረዋል።
በትምህርት ስርዓቱ ላይ እየዋሉ ያሉ የትምህርት መረጃዎች የተዓማኒነት፣ የወቅታዊነት እና የጥራት ችግር የነበረባቸው በመሆኑ፤ ይህንን ለመቅረፍ አዲስ ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴርተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/Tmhrt_Ministerhttps://t.me/Tmhrt_Minister