❗#ሥግደት_የማይሰግባቸው_ቀናቶች❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ይዘትም ሆነ በሃይማኖት ሥርዐት ፍጽምት ነች፡፡ የሃይማኖት ይዘቷ (ዶግማዋ) ይህ ይቀረዋል ተብሎ የማይጨመርበት በእግዚአብሔር አንድ ጊዜ ፍጹም ሆኖ ለቅዱሳን የተሰጠ ነው፡፡
🔵👉 (ይሁዳ 3) እግዚአብሔርን የምታመልክበት ሥርዐትም እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ በመራቸው ቅዱሳን ሰዎች የተቀነነ ቅዱስ ሥርዐት ነው፡፡ ጊዜንና ቦታን በመዋጀትም (ግንዛቤ ውስጥ በማስገባትም) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሥርዐትን እንድትሠራ ቀኖና አለ፡፡ ከዚህ አንጻር ስግደትንም በተመለከተ መች ሊሰገድ እንደሚገባና መች እንደማይሰገድ ሥርዐትን ሠርታልናለች እንጂ እንዲሁ በዘፈቀደ እንዲተገበር ቸል አላለችም፡፡
🔴👉 ከሁሉ አስቀድሞ ግን እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ያሉትን የአሰጋገድ አይነቶች ማወቅ ያስፈልጋል በመሆኑም #ሦስት አይነት #የስግደት_አሰጋገድ_አይነት_አሉ ። እነሱም ፦
(1ኛ)፦ #አድንኖ ስግደት ይባላል።ይህም ማለት እራስን ዝቅ አድርጎ ወገብን ጎበስ በማለት ጉልበትና ግንባር ምድር ሳይነካ የምንቃናው ማለት ነው።
(2ኛ)፦ #አስተብርኮ ይባላል ይህም አሰጋገድ በጉልበት ወድቆ ግንባር መሬት ሳይነካ የምንነሳው የስግደት አይነት ነው።
(3ኛ)፦ #ሠጊድ ይባልላ። ይህ አግጋገድ ሙሉ በሙሉ በጉልበት መሬት ላይ በመውደቅ ግባርን መሬት በማስነካት የምንሰግደው የስግደት አይነት ነው።
🔵👉 ታዲያ ከእነዚህ የአሰጋገድ አይነቶች በአምስቱ (5) የግዝት በዓላት የማይሰገደው የትኛው የአሰጋገድ አይነት ነው ስንል አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው እስከዛሬ ያስተማሩን ያስቀመጡልን ሠጊድ የምንለውን ስግደት ነው።
🔴👉 ስለዚህ የአሰጋገድ አይነቶቹን ከተመለከትን ዘንዳ ይህንን ሠጊድ የምንለውን የአሰጋገድ አይነት የማንሰግድባቸውን አምስቱን የግዝት ዓላት ደግሞ እንመልከት !
🔴👉 ሥግደት የሚሰገድባቸው ጊዜያት እንዳሉት ሁሉ የማይሰገድባቸው ጊዜያት አሉት የግዝት በዓላት አምስት ሲሆኑ
እነርሱም :- 1 👉ወር በገባ በ29 #የወልድ_በዓል፣
🔴 የነጻነት ቀን ጌታ የተወለደበት ቀን ስለሆነ።
2 👉ወር በገባ በ 21 #የእመቤታችን_በዓል፣
🔴የነፍሳችን ዕረፍት፥ ነጻ የወጣንባት ስለሆነ።
3 👉ወር በገባ በ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል በዓል፣
🔴ራዕ᎐፲፪ ሰይጣን የወደቀበት ቀን ስለሆነ።
4 👉#ቀዳሚት_ሰንበት (ቅዳሜ)
🔴ጌታ ከስራው ያረፈበት ቀን ስለሆነ
5 👉እሑድ_ሰንበት (ሰንበተ ክርስቲያን ናቸው።
🔴ጌታ ከሙታን መካከል ተለይቶ የተነሳበት ቀን የዕረፍት ቀን ስለሆነ ።
❗በእነዚህ ቀናቶችም ሠጊድ የምንለው ስግደት አይሰገድም❗
🔴👉 ከነዚህ በተጨማሪም ሥግደት የማይሰገድባቸው ጊዜያት የሚከተሉት ናቸው !
❗1ኛ. #በዕለተ_እሑድ❗
🔵👉ከአልቦ ነገር ወይም ከምንም የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ ጠፍቶ ወደ ምንምነት ሲቀየር ከማይጠፉ ከአምስቱ ፍጥረታት አንዷ ሰንበት ናት፡፡ ጌታ የተነሣባት ፣ ዳግምም የሚመጣባት ዕለት ናት፡፡ በዚህና በሌሎች ምክንያቶችም ሰንበተ ክርስቲያን እሑድ በዓል ነች፡፡
🔴👉 ስለዚህ በዕለተ እሑድ መስገድ የተከለከለ ነው፡፡ ይህንን ፍትሐ ነገሥቱ እንዲህ በማለት ይገልፀዋል፡- “ከአድንኖና ከአስተብርኮ በቀር እስከ ምድር መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ ጊዜያቶች እነዚህ ናቸው፡፡ ኒቅያ 20፣ በዕለተ እሑድና በበዓለ ሃምሳ ወራት፣ ” ፍት.መን. አን. 14 ቁ. 537 ይህንን ይበልጥ ሲያጸናው በሰንበታትና በበዓላት አንቀጹ እንዲህ ሲል ደግሞታል፡- “በእሑድና በተከበሩት በዓላት ቀን ስግደት አይገባም፤ እነዚህ የደስታ ቀኖች ናቸውና” ፍት. መን. አን. 19 ቁ. 715።
❗2ኛ. #በበዓለ_ሃምሳ_ወራት❗
🔴👉 በዓለ ሃምሳ የፍስሐና የሰላም ጊዜ ነው፡፡ ስሙ እንደሚጠቁመው ሃምሳውም ቀን በሙሉ በዓል ነው፡፡ በዓል ስለሆነም እንደ ፋሲካና እንደ ልደት እንበላበታለን እንጂ ረቡዕና አርብ ቢሆን እንኳን አንጾምበትም፡፡ በበዓልነቱ ጾም እንደተሻረበት ስግደትም እንዲሁ ይሻርበታል፡፡ ከላይ እንዳየነው ፍትሐ ነገሥቱም በፍት.መን. አን. 14 ቁ. 537 በእሑድ መስገድን ሲከለክል በበዓለ ሃምሳም እንዲሁ ከልክሏል፡፡
❗ 3ኛ. #በጌታችን_በዓላት❗
🔵👉 ፍትሐ ነገሥቱ “በእሑድና በተከበሩት በዓላት ቀን ስግደት አይገባም፤ እነዚህ የደስታ ቀኖች ናቸውና” (ፍት.መን.
አን. 19 ቁ. 715) ካለ በኋላ “የተከበሩት በዓላት” ያላቸው የትኞቹን እንደሆነ ሲዘረዝር ትስብእት/ጽንሰት ፣ ልደት ፣ ጥምቀት ፣ ሆሣዕና ፣ ትንሣኤ ፣ ዕርገት ፣ በዓለ ሃምሳ ፣ ደብረ ታቦር በማለት ከጌታ ዘጠኝ ዐበይት በዓላት 8ቱን ይገልፃል፡፡ ሳይገለፅ የቀረው ስቅለት ነው፤ ያልተገለፀበትም ምክንያት በስቅለት ስግደት ስለማይከለከል ነው፡፡
🔴👉 ስለዚህ ከስቅለት በቀር በጌታ ዐበይት በዓላት (በተቀሩት በ8ቱ) ስግደት የተከለከለ ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥቱ ይህንን ሲያጸና በአንቀጽ 14 እንዲህ ብሏል፡- “መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ በዓላት እነዚህ ናቸው.... ኒቅያ 32፣ በጌታችን በዓላትና በእመቤታችን በዓላት” ፍት.መን. አን. 14 ቁ. 536-537፡፡
❗4ኛ. #የእመቤታችን_በዓላት❗
🔴👉 ከላይ ያየነው የፍትሐ ነገሥት ንባብ በፍት. መን. አን. 14 ቁ. 536-537 ድረስ በጌታ በዓላት መስገድ እንደተከለከለው ሁሉ በእመቤታችን በዓላትም መከልከሉን ይጠቁመናል፡፡
❗5ኛ #ሥጋውንና_ደሙን_ከተቀበሉ_በኋላ❗
🔴👉 የሥርዐት ምንጫችን የሆነው ፍትሐ ነገሥት አሁንም በዚህ ዙሪያ እንዲህ ብሏል፡- “መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ በዓላት እነዚህ ናቸው... ሥጋውንና ደሙን ከተቀበሉ በኋላ” ይላል፡፡ ፍት. መን. አን. 14 ቁ. 536-537፡፡ ሥጋውንና ደሙን ከተቀበልን በኋላ ከሚሰገድለት እንጂ ከማይሰግደው ጋር አንድ መሆናችንን ለማጠየቅና ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ ክብር ስንል ዝቅ ብለን አንሰግድም።
🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ህዳር 28/2017 ዓ.ም
ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/sratebetkrstyane