በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ" ማር 9 : 50፡፡
☞ጨው የተባሉ፦
1. ክርስቶስ
2.ቅዱሳን (እመቤታችን ፤ መላእክት ፣ ጻድቃን ሰማዕታት....)
3. ሐዋርያት (ካህናት)
4. ምእመናን ናቸው፡፡
➊ ጨው ምግብ ያጣፍጣል፦ የጨው ዋና ጠባይ ራሱ የሚበላ ሳይሆን ሌሎች ምግቦች በእርሱ አጣፋጭነት እንዲበሉ እንዲፈለጉ እንዲወደዱ ማድረግ ነው (በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ፦ እንዲሉ አበው፡፡)፤
• 👉ክርስቶስም ጻድቅሆኖ ሳለ ለእራሱ ጽድቅ ሳይሆን ለእኛ ጽድቅ በኃጢአታችን ሞቶ የእኛን ሕይወት አጣፍጦታል፡፡
(ፄው ዘአጥዐሞ ለልሱሕ)
• ጨው ሲያጣፍጥ ሟሙቶ ነው ጌታችንም ሊያጣፍጠን በመስቀል ድቅቅ ብሎ ነው (ኢሳ 53 ፥5 ስለ በደላችን ደቀቀ)፡፡
👉ቅዱሳንም ተጋድለው ተንከራተው ነው
• ካህናትም በምእመናን ሕይወት ውስጥ ሟሙተው ሕይወታችንን ያጣፍጣሉ
• ምእመናንንም በሌሎች ሰዎች ሕይወት የበጎ አርአያ ሆነው፤ በምጽዋትና በጾም በበጎ ምግባር ሟሙተው የሌሎችን ሕይወት ያጣፍጣሉ
➋ጨው ከሁለት ኢለመንቶች (Elements, Sodium Na እና Chlorine Cl) የተሠራ ውሕድ ነው 👉(Table salt)
• ♥ክርስቶስም ከሁለት አካል እንድ አካል፤ ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ መሆኑን ያመለክታል፤ ይህም ማለት የቃልና የሥጋ ተዋሕዶ ማለት ነው (ዮሐ 1፡14)፡፡
👉ቅዱሳንም ከሥጋ ከመንፈስ ናቸው
• ካህናትም የሁለት ነገሮች ተዋሕዶ ናቸው ፦ የሥጋና የነፍስ ፤ የውኃና የመንፈስ፤የክርስትናና የክህነት ውጤቶች ናቸው
• ምእመናንም ክህነት ባይኖራቸውም ከእናት ከአባት ፤ "ከውሃና ከመንፈስ" የተወለዱ ናቸው፡፡
➌ጨው ርካሽ ነው፦ በቀላል ዋጋ ይገኛል፦
• ♥ክርስቶስም ያለ ዋጋ ተገኝቶልናል፤ ለፍቅሩ ለቸርነቱ የምንከፍለው ምንም የለንም፤ ለመክፈልም ዓቅሙ የለንም፡፡
👉የቅዱሳን ቃል ኪዳንም እንዲሁ ነው ....አይከፈልም
..... ለቅዱሳንም ሳንከፍላቸው ይማልዱልናል
• ካህናት ያለ ዋጋ ይገኛሉ፤ ለቡራኬያቸው አንከፍልም፤ ለጸሎታቸው አንከፍልም፤ ለቅዳሴው ለማኅሌቱ አንከፍልም...በነጻ!
• ምእመናን ሲመጸውቱ ፤ ሲረዱ፣ የታመመና የታሰረ ሲጠይቁ አይከፈላቸውም...ደግ ሆነው ግን በነጻ ያለ ዋጋ ደግ ሆነው ይኖራሉ፡፡
➍ጨው ምግብ እንዳይበላሽ መጠበቂያ (Preservative) ነው፡፡
• ♥ክርስቶስም በኃጢአትና በበደል ከርፍተን ሸተን የነበርነውን የሁላችንን ክፉ ሽታ በመስቀል ጠርቆ አስወግዶ እንዳንበላሽ እንደገና ሠርቶናል፤ ወደፊትም እንዳንበድል በመስቀሉ/በመከራው በውስጣችን ይኖራል፤ መከራ መስቀሉ ይመዘምዘናል፡፡
👉ቅዱሳንም ሕይወታችን እንዳይበላሽ በአርአያነታቸው ይጠብቁናል
• ካህናትም በኃጢአት ውስጥ ሆነን እንዳንበላሽ በንስሐ ይጠብቁናል፡፡
• ምእመናን ሌሎችን መክረው ፤ በንስሐ ለሌሎች ምሳሌ ሆነው ሌሎችን እንዳይበላሹ ወደ በጎ ምግባር ይመልሳሉ፡፡
➎ጨው ፈውስ/መድኃኒት ነው፤ ቁስል ያደርቃል፡
• ♥ክርስቶስም መድኃኒታችን ነው፤ በመስቀል ስለ እኛ ቆስሎ የእኛን ቁስል አድርቆ ፈውሶናል (ኢሳ 53) ፡፡
👉ቅዱሳንም በምልጃቸው በቃል ኪዳናቸው ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቁናል
• ካህናትም በምክር በአገልግሎት በማስታረቅ በንስሐ መድኃኒት ሆነው ወደ እግዚአብሔር ያቀርቡናል፡፡
• ምእመናን በሕይወታቸው፤ በደግነታቸው፤ በምጽዋታቸውና በጾማቸው ሌሎችን ኢአማንያንን ጭምር ይፈውሳሉ ፡፡
☞"ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ" ማር 9 : 50፡፡
ጨው ሆነን አልጫ የሆነውን ዓለም ለማጣፈጥ ያብቃን🙏
መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samualቴሌግራም
https://t.me/tsidqtiktok
https://vm.tiktok.com/ZMBYPbBMJ/