የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቻይና ምድር የመጀመሪያዋን ደብር ሰየመች!
ቤተ ክርስቲያኗ በቻይና ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በከፈተችው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ አከናውናለች።
በቻይና ምድር የተከፈተው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም” የሚል ስያሜ እንደተሰጠውም የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አዲስ የተከፈተችውን ቤት ክርስቲያን ከሰየሙ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምዕምናንን ማቁረባቸውም ተነግሯል።
በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን መሾማቸውም ነው የተገለጸው።
በዕለቱም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምዕመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ መሳተፋቸውም ተነግሯል።
ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ በቻይና የሚገኙት በፅዕ አቡን ያዕቆብ ለቀጣይ አገልግሎት ወደ ሀገሪቱ መዲና ቤይጂንግ ከተማ ማቅናታቸውም ነው የተገለጸው።