👉🏾 እግዚአብሔር #ቅዱስ #ሚካኤልን በልዓም ወደ ተባለ ሰው ላከው"
👉የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ወዳጆች ወገኖች የመካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ወልድ ዋህድ ሰንበት ት/ቤት ድህረ ገጽ የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በያላችሁበት የምትከታተሉ በእግዚአብሔር ሰላምታ ሰላም እንላችኋለን፣ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልን ዛሬ በርዕሱ እንደተጠቀሰው "እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን በልዓም ወደ ተባለ ሰው ላከው" በሚል ርዕስ ነው የምንነጋገረው፣ አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን፦
መጋቢት 12
✍በዚህች እለት እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን ወደ በልዓም ወደ ተባለ ሰው ላከው፣ ይህም "ሀብተ መርገምና፣ ሀብተ ቡራኬ የተሰጠው ነቢይ ነው" እስራኤል ከግብፅ ከወጣ በኋላ 40 ዘመን በበረሐ ተጉዘው ሞአብ ሲደርሱ "ንጉሡ ባላቅ ወልደ ሶፎር" ግብፅን በዘጠኝ መቅሰፍት በአሥረኛ ሞት በኩር፣ በአሥራ አንድ ስጥመተ ባሕር ያጠፋ ጦር የማይመልሰው ጠላት ተነስቷል መጥተህ እርገምልኝ" ብሎ እጅ መንሻ አስይዞ ላከበት፡፡
ነቢዩ በልዓም መልክተኞችን ዋሉ፣ እደሩ ብሎ ሌሊት ወደ እግዚአብሔር
ጸለየ፣ በጸሎቱም ምላሽ ፈጣሪ ወደዚያች ከተማ እንዳይሄድ አመለከተው፣ "መልእክተኞችንም አልሆነም እናንተም ሂዱ አላቸውና ሄዱ" ንጉሥ ባላቅም እጅ መንሻ ቢያንስበት ነው ብሎ ከፊተኞች የበዙና፣ የከበሩ ሰዎችን ላከ፣ ባላቅም "ለነቢይ በልዓም ክብርህን ከፍ አደርጋለሁ ቤትህን በወርቅ እሞላለሁና እርገምልኝ አለው" ነቢይ በልዓም ወርቅ ብርም ቢሰጡኝ በትልቁም ይሁን፣ በትንሹ ከአምላኬ ፈቃድ አልወጣም፣ ነገር ግን ፈጣሪ የሚለኝን ልወቅ አላቸውና ፈጣሪውን በጸሎት ለመነ፣ ፈጣሪውም "ነቢይ በልዓም ተነስ ከእነሱ ጋር ሂድ ነገር ግን የምነግርህን ትናገራለህ" አለው፡፡
አህያይቱን ጭኖ ከሄድኩማ እንዴት አልረግምም? እያለ ሲጓዝ በመንገድ
ቅዱስ ሚካኤል ሰይፋን መዞ ለአህያይቱ ታያት፣ ፈርታ ቆመችና ወደ እርሻ ውስጥ ገባች" በልዓምም ለመመለስ መታት፣ በዚያን ሰዓት እንደገና ቅዱስ ሚካኤል ከግንብ መካከል ቆመ፣ አህያይቱ ወደ ቅጥሩ ተጠግታ እግሩን ረገጠችው፣ አሮጌ ነቢይ አደረገሽኝ? ወይኔ ጦር በያዝኩ በወጋሁሽ ነበር አለ፣
ያን ጊዜ በሰው አንደበት "ከታናሽነትህ ጀምረህ ተራራውን ውጪ፣ ሜዳውን
ሩጪ ብለህ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁም ለምን ሦስት ጊዜ መታኸኝ? ምን አድርጌ ነው? አለችው"
ያን ጊዜ ዓይኑ ተከፍቶ " መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገለፀለት፣ ከእህያው ወርዶ
ሰገደለት" አህያህን ለምን ሦስትጊዜ መታህ? ከፊቴ ባትሸሽ ኖሮ አንተን በገደልኩ ነበር አለው፣ " ነቢይ በልዓምም በድያለሁ ፈቃድህ ካልሆነ ልመለስ "አለው፣ ሂድና የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው፡፡
ንጉሥ ባላቅም ነቢይ በልዓም መምጣቱን ሰምቶ በደስታ "ወደ አርኖን ዳርቻ መጣና ስለ መጣሁ ደስ አይበልህ እግዚአብሔር የገለፀልኝን ብቻ እናገራለሁ አለው" ንጉሥ ባላቅም መሥዋዕት ሰውቶ የሕዝቡን ዳርቻ አሳየና እርገምልኝ አለው፣ ነቢይ በልዓምም እግዚአብሔር ያልረገመን እንዴት እኔ እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልነቀፈውን እንዴት እነቅፋለሁ አለ? ንጉሡም እርገምልኝ ብልህ ትመርቃቸዋለህ? አለው፣ የገለፀልኝን ብቻ እናገራለሁ ብዬሃለሁ አለው፣ ለሦስት ጊዜ መስዋዕትን እየሰዋ እርገምልኝ አለው፣ ነቢይ "በልዓምም ያዕቆብ ከተማህ ምን ያምር? እስራኤል ቤቶችህ ምን ያምሩ? ብሎ አድንቆ አሞገሰ" ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል እያለ ምስጢረ ሥጋዌ ተገልጾለት ተናገረ፣ እርገምልኝ ብልህ ትመርቃለህ? አለው፣ እግዚአብሔር የገለፀልኝን ብቻ ነገርኩ አለው፣ ነቢይ በልዓምም " እረግሜ ባላጠፋልህም መክሬ አጠፋልሃለሁ፣ ደናግናኑ ለጣዖት ይሰግዳሉ፣ ያን ጊዜ ፈጣሪ ተቆጥቶ ያጠፋቸዋል" አለው፣ ያቺ ቀን "መጋቢት 12 ቀን" ነች፡፡
ምንጭ፦ "ድርሳነ ሚካኤል ዘወርሐ መጋቢት"
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled0
ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/weled9