የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ፤ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ገፅ ነው ።
በዚህ ገፅ ፦
● መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ መልዕክቶች ፣ ምክሮች
● መዝሙሮች ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች
● ወቅታዊ የቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤት ጉዳዮች
● የሰ/ት/ቤት መልዕክቶች ፣ ማስታወቂያዎች ይቀርቡበታል።
ኦዲዮቪዥዋል ክፍል
ለመቀላቀል ➠ @weludebirhane

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ውሉደ ብርሃን ሚድያ

ለመቀላቀል  ➠

🧷YouTube
https://youtu.be/542fdWtDH3c

  🧷Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl  
 
🧷Telegram
https://t.me/weludebirhane


  🧷Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1

◈ ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe  እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ማድረግ እንዳይረሳ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ
ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

ጥር ፳፱/፳፻፲፯ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)
   


ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

•  የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !
እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣

አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፤እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

   በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤

  የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን

   “እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምንጭ
EOTC Broadcasting Service Agency


ውሉደ ብርሃን ሚድያ

ለመቀላቀል  ➠

🧷YouTube
https://youtu.be/542fdWtDH3c

  🧷Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl  
 
🧷Telegram
https://t.me/weludebirhane


  🧷Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1

◈ ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe  እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ማድረግ እንዳይረሳ


ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
እኔ የአእምሮ ድኃ የሆንኩ አገልጋይሽ ብቻ ቀርቻለሁና፡፡ ብዙውን የልቤን ኅዘን ነግሬሽ ከኅዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡

፳፪፤ ንዴተ ሥጋ ወነፍስ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የሥጋና የነፍስ ችግር እዳይደርስብኝ ዕንቁ ስምሽን ከክብር መዝገብ ወይም ሣጥን ወስጄ ገንዘብ አደረግሁ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የገጽሽን ጸዳል ለማየት እፈልጋለሁ እኮን፤ ድንግል ሆይ፤ ፈጥነሽ ድረሽልኝ፤ ድንግል ሆይ፤ ገስግሰሽ ድረሽልኝ ሰውነቴ አንችን ጠጠምታለችና፡፡

፳፫፤ አፈወ ሃይማኖት፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
በዚያ የቁርጥ ፍርድ በሚሰጥባት ዕለት ሁሉን ወደ ሕይወት ጎዳና የምትስቢ መዓዛሽ የጣፈጠ የሃይማኖት ሽቱ ነሽ እኮን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ጻድቃን በትሩፋቸው፤ በተጋድሎአቸው ያገኙሽ መንግሥተ ሰማይ ነሽ እኮን፤ የፍቅርሽ ፄና መዓዛ፤ እንደ ነጭ ዕጣን መዓዛ ሸተተኝ፤ በፍቅርሽ ወይን ጠዕምም ልቡናየ ይደሰታል፡፡

፳፬፤ አበዊነ ቅዱሳን፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ቅዱሳን አባቶቻችን አንቺን መረጡ መድኃኒታቸው የሆንሽ አንቺንም መልካም ፍሬ አፈሩ፡፡ (አስገኙ)

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ለደካማው የመጠጊያ ተራራ ነሽና ጻድቅስ በበጎ ሥራው ይድናል እንደኔ ያለው ኃጥእ ግን መሸሻው መጠጊያው ከአንቺ በቀር ወዴት ነው፡፡

፳፭፤ ለመልክእኪ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
መጻሕፍት እደተናገሩት ወይም እንደሚያስረዱት የእግዚአብሔርን ሥነ ራእይ ለሚመስለው ሥነ መልክእሽ ሰላምታ ይገባል፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ አንቺ ነሽ እኮን፤ የሚወዱሽ የሚያከብሩሽም ሁሉ በረከትሽን ያግኙ፤ የሚጠሉሽ የሚመቀኙሽ ግን ፈጥነው ይጥፉ፡፡

፳፮፤ ስብሐት ለኪ፡፡
የአብ ሙሽራው ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባል፡፡ የወልድ እናቱ ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ንጽሕት አዳራሽ ማርያም ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል፤ ወርቅና ብር ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ስለዚህም ከዚህ ዓለም ብልጽግና ይልቅ አንቺን መውደድ እመርጣለሁና፡፡ ቸርነትሽን አታርቂብኝ፡፡

፳፯፤ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
አሁንም በመዓልትና በሌሊት ጠብቂኝ፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውሪኝ ለዘላለሙ አሜን አሜን አሜን

ለመቀላቀል

👉 @weludebirhane


⛪✝️መልክአ ኤዶም✝️⛪

፩፤ ለዝክረ ስምኪ በአምኃ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የሰላም እመቤት ነሽና ሰላምታ ላንቺ ይገባል፡፡ እያልኩ በጠዋትና በማታ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርብልሻለሁ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
በገነት መካከል የተተከልሽ ድንኳን ነሽ እኮን የኔ የአገልጋይሽ ኃጢአት ከሰማይ ኮከብ ይልቅ የበዛ ስለሆነ የካህናት አለቃ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽና ተገቢውን ንስሐ ሰጭኝ፡፡

፪፤ ለዝክረ ስምኪ ሀሊብ፤

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
እንደወተት አንጀትን ለሚያርስ ልብን፤ ለሚያቀዘቅዝ የመልካም ወተት ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል እያልኩ ሰላም እላለሁ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ርግብየ ርግብየ እያለ የሚያመሰግንሽ የጥበበኛው ሰሎሞን ርግብ ነሽና ድንቁርና ረኃብ እንዳይጸናብኝ እህል ጥበብን መግቢኝ ከብዙ በጎ በጎ ሥራዎች አንዱ መስጠት ነውና፡፡

፫፤ ልብኪ የዋህ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ኀጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም የዋህ ነው እኮን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ስለዚህም ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፡፡ በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለሁ? ኅዘኔን ጭንቀቴንም አንች ታውቂዋለሽና፡፡

፬፤ ከመ ከማኪ ማርያም፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ከነቢያት ከጻድቃን ከሰማዕታትም ወገን ቢሆን ከቶ እንዳች የምወደው ማንም የለ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
አንቺን መጠጊያ ስለአደረግሁ በአንቺ ከመታመን በቀር ሥራየ ኃጢአት ብቻ ሆኗልና ለእርዳታየ ፈጥነሽ ድረሽልኝ፡፡

፭፤ ኢትኅድግኒ ዐቂበ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
በምሄድበት ጎዳና በማድርበትም ቦታ ሁሉ በመዓልትም በሌሊትም ጥበቃሽ አይለየኝ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ነፍሳትን ሁሉ የምትመግቢ ነሽና የልብስና የምግብ ችግር ባለ ዘመኔ ሁሉ አታሳይኝ፤ ረኅብና ብርድ ጸሎትን ያስረሳሉና፡፡

፮፤ ኅበ ሖርኩ ሑሪ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
አሁንም በሄድኩበት መንገድ ሂጅ፤ በአደርኩበትም በዚያ ቸርነትሽ ጠባቂ ይሁነኝ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
በማንኛውም ወገን ንግግሬን አሳምሪ ቀኝ እጅሽን በራሴ ላይ አኑሪ፡፡ የሚፃረሩኝን ተፃረሪ ክፉ ምክራቸውንም አንድ በአንድ ዘርዝሪ፡፡

፯፤ ንዒ ማርያም፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ከኃጢያት ሁሉ መተዳደፍ በማየ ንስሐ ንጹሕ እምኃጢአት ታደርጊኝ ዘንድ በረድኤት ወደኔ ቅረቢ እያንዳንዳችንንም በሥላሴ ስም ባርኪን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
እንደኔ ያሉትን ኃጥአኖች በጸሎትሽ ወደ ንስሐ እንዲመለሱ መንፈሳዊ ጥበብን ግልጭላቸው፤ ጻድቃንንም በምግባራቸው በትሩፋታቸው ጸንተው እንዲቆዩ ጠብቂያቸው፡፡

፰፤ ንዒ ማርያም፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ጸሎቴን ተቀብለሽ ወደላይ ወደሰማይ ታሳርጊ ዘንድ ከላይ ከሰማይ ዳርቻ ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ዘወትር የርኅራኄሽን ጠል በኔ ላይ አርከፍክፊ፡፡ የምድር ብልጽግና ግን ኃላፊ ጠፊ በመሆኑ በቸርነትሽ ጽድቅን ታተርፊልኝ ዘንድ የተገባ ነው፡፡

፱፤ ንዒ ማርያም ሆይ፤

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የአዳም ልብሱ ግርማ ሞገሱ የሄኖክ የራስ ወርቅ አንች ነሽ እኮን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ብልህ አዋቂ የሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ያፈቅራል፤ ሰነፍ ልበ ቢስ ግን በከንቱ ይጠላሻል፤ ዳሩ ግን በመከረው የተንኮል ምክር ወጥመድ እሱ ራሱ ይጠመድ፡፡

፲፤ ንዒ ማርያም፤

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት የቅዱስ ቁርባንን አዝመራ ያፈራሽ ገራህት ሆይ፤ ከትጉሃን መላእክት ጋር ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ዓለም እኮ የወደዳትን መልሳ ታጠፋዋለች፡፡ በወጥመዷም አስገብታ ብዙውን ሕዝበ በመርዟ እንደገደለች ይህን ሥራዋን የሚያውቅባት ከቶ እንደምን ያለ ብልህና ዐዋቂ ይሆን ስለሆነም በመጥመዷ እንዳታጠምደኝ መረቧን በጣጥሰሽ ጣይልኝ፡፡

፲፩፤ ንዒ ማርያም፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡

፲፪፤ ንዒ ማርያም፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የመለኮቱ የእሳት ግለት ያላቀጠለሽ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነሽና ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
በየዘመኑ በየዕለቱም ሁሉ ማሪኝ ይቅር በይኝ አንቺ ከማርሽኝ ይቅር ካልሽኝ ማነው እሱ የሚፈርድብኝ በሥጋና በነፍስ የሚፈርድ ልጅሽ ነውና

፲፫፤ እስእለኪ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የሰማይና የምድር ንጉሥ እናት ነሽና ኃጢአቴን ሁሉ ፈጽመሽ ለማጥፋት ፈጥነሽ ወደኔ ትመጭ ዘንድ እማልድሻለሁ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የሥጋና የነፍስን ችግር ሁሉ ከኔ ላይ አስወግጅ፡፡ ይልቁንም ወዲያና ወዲህ በማለት ቀኑ በከንቱ እንዳይመሽብኝ በቁም ነገር ሥራ ላይ እገኝ ዘንድ፤ እኔ በደለኛው አገልጋይሽ እማልድሻለሁ፡፡

፲፬፤ አተከዝኩኪ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ሥፍር ቁጥር በሌለው የዚህን ዓለም ፍለጋ በመከተል እኔ ኃጥኡ ጎስቋላው አገልጋይሽ አሳዘንኩሽ ይሆን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ታዲያ ከቀድሞ ጀምሮ ቂም በቀልን ይቅር ማለት ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ መሐሪዋ እናት ሆይ፤ አረጋጊኝ እንጂ አትተይኝ፡፡

፲፭፤ አተከዝኩኪ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
በመሴሰንና የዝሙት ሥራ በመሥራት ሐሰት በመናገር አሳዘንኩሽ ይሆን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ነገር ግን አንቺን በፍጹም ልብ መውደድ ቀላል አይመስለኝም ሰባ ስምንት ነፍሳትን የበላ በላዔ ሰብእ በጥርኝ ውሃ ገነት ለመግባት በቅቷልና፡፡

፲፮፤ ኦ ርኅርኅተ ኅሊና፡፡

ርኅሩኋ እመቤቴ ሆይ፤
አደፍ ጉድፍ ሳይኖርብሽ በድንግልና ጸንተሽ ያለሽ የአንች ፍቅር እሳት ሆኖ አንጀትን ያቃጥላል እኮን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ሁል ጊዜ በጎ በጎ ነገርን አድርጊልኝ፡፡ እንደ ሥራየ ሞት ይገባኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ንስሐ የምገባበት ጥቂት ጊዜ ታገሽኝ፡፡

፲፯፤ እለ ትወርዱ ታሕተ፡፡
እናንተ በዚህ ዓለም እያላችሁ ወደላይ ወደታች የምትወጡና የምትወርዱ ሁሉ የእመቤታችን ፍቅር ከቶ ቀላል አይምሰላችሁ፡፡ በየጊዜው ስሟን እየጠራ በእመቤታችን ፍቅር የተማመነ በአማላጅነቷም ጥላ ሥር የተጠለለ ዘማዊ ወይም ሴሰኛም ቢሆን፤ ፍጹም ድንግል ይሆናልና፡፡

፲፰፤ ተአምረኪ ብዙኃ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ መሆንሽ ብዙ የሆነ ልዩ ልዩ ተአምራትሽን በጆሮየ ሰምቻለሁ በዓይኔም አይቻለሁ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
እኔን ከርታታውን አውታታውን በዚህ ዓለም የሚያረጋጋኝ የሚያጽናናኝ አጥቻለሁና፡፡ ርኅሩኋ እናት ሆይ፤ እስኪ ቀረብ ብለሽ የማጽናኛ ቃል አሰሚኝ፡፡

፲፱፤ ተአምረኪ ብዙኅ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ፍጻሜ የሌለው የብዙ ብዙ የሆነ ተአምርሽ በደመናና በጉም አምሳል በዓለም ላይ ተሠራጨ፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
የሮማው ጳውሎስ የመዛነቢያው ድንኳን ነሽ እኮን እኔም ንስሐ ሳልገባ እንዳልሞት ዕድሜ ትጨምሪልኝ ዘንድ ሰሎሜ ባዘለችው ልጅሽ እማፀንሻለሁ፡፡

፳፤ ናዛዚትየ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ከኅዘን የምታረጋጊኝ እርጅናዬን በወጥትነት የምትለውጭልኘ ዘመን የማይቆጠርለት ሕፃን በማኅፀንሽ አደረ እኮን፡፡

ድንግል እመቤቴ ሆይ፤
ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸው ነሽና ጸሎትንና ዕጣንን እንዲሁም ቅዱስ ቁርባንን በማቅረብ ጊዜ እኔ አገልጋይሽን ለማጽናናት በዚህ ቦታ ተገኝ፡፡

፳፩፤ ስምኪ ድንግል፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ፤
ስምሽ ኃጥኣንን ያጸድቃል ሰነፎችንም ብልህና ትጉህ ያደርጋል፡፡


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMkV3Aphw/
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️






‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም  ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡››

#ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

#ጥር 24/2017 ዓ.ም በእንጦጦ መንበረ ስብሀት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻችሁን የፈፀማቹት #የሰ/ት/ቤታችን አባባላት የወንድችን ወንድማችን ዲ/ን ምትኩ ተሾመ እና ስምረት ተካ
የወንድማችን ዲ/ን ምስጋናው እና ወ/ት የአብስራ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤  የአብርሃምንና የሣራን፣ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷  ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላችሁ፡፡



#ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡

>
#ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች  5:22)
----------
22፤ ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤

23፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።

24፤ ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።

25-26፤ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

27፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።

28፤ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤

29-30፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል።

31፤ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

32፤ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።

33፤ ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ።

የመንበረ ስብሐት ቅ/ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን የውሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
     #ኦዲዮቪዥዋል ክፍል

ለመቀላቀል  ➠
  🧷Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl  
 
🧷Telegram
https://t.me/weludebirhane
 
🧷YouTube
https://youtu.be/542fdWtDH3c
◈ ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe  እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ያድርጉ!.




“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።”
 
— መዝሙር 122፥1

" ተፈሳሕኩ እስመ ይቤሎኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር ።"

        ዘዳዊት መዝሙር  ፻፳፩


                   የፅዋ መርሃ ግብር

ጥር 18/2017,ዓ.ም እሑድ  ከ7:30ጀምሮ

የጽዋ መርሐግብር  ላይ

👉 የመፅሐፍት ዳሰሳ
👉 ትምህርተ ወንጌል

ስለተዘጋጀ በሰዓቱ  እንገናኝ

@weludebirhane

በቀን  18/05/17 በ 7:30 ሰዓት ጀምሮ


https://t.me/weludebirhane


መዝ፵፬፡፲፮

ህይንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቀ ወትሰይምዮሙ መላዕክት
በኩሉምድር ወይዘከሩ ስመኪ ለትውልደ ትውልድ ።

ትርጉም

በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፣በምድርም ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ፣ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ።

የአገልግሎት ዘመናቹ በቤቱ ይለቅ ውብ የውብ ልጆች ።

ውሉደ ብርሃን ሚድያ

ለመቀላቀል  ➠

🧷YouTube
https://youtu.be/542fdWtDH3c

  🧷Facebook  https://www.facebook.com/1880533115515403/posts/2831103630458342/?app=fbl  
 
🧷Telegram
https://t.me/weludebirhane


  🧷Tiktok https://www.tiktok.com/@weludebirhan1?_t=ZM-8t8Bq1Nt0vV&_r=1

◈ ገፆቹን #Like , #Follow , #Subscribe  እንዲሁም የሚለጠፉትን #Share , #Like ማድረግ እንዳይረሳ


★ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የስራ ማስታወቂያ

♦Closing Date: January 29, 2025

Ethiopian Airlines Group would like to invite qualified applicants for the positions.

✔ Position 1: Junior Administration Assistant

❇️ REQUIREMENTS: BA Degree in Management/Business Management/Business Administration/Management Information System/Accounting/Accounting Information System or any business-related field of study from recognized University/ college

✔ Position 2: Medical Doctor

❇️ REQUIREMENTS: Graduate In Medicine

✔ Position 3: Radiology Technologist

❇️ REQUIREMENTS: BSc Degree in Radiology Technology

🌀How to Apply??
   👇👇👇👇👇👇
https://dailyjobsethiopia.com/2025/01/23/ethiopian-airlines-vacancy-2025-2/


ለመቀላቀል

👉 @weludebirhane


#ቃና_ዘገሊላ

ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡

የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡

በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡

አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጇ ወደ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡

‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?››

ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡

ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡-
የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› ትወልጃለሽ ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡
በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ ጌታችን ቀርቦ ‹‹የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡፡ ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ (ሉቃ 8÷28-29) ስለሆነም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡ ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡፡

‹‹ጊዜዬ አልደረሰም›› ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡-
እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡
አንድም ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡
አንድም ይሁዳ ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡

አንድም እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል፡፡
የድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን የእናቱን የድንግል ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡፡ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡፡ ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትማ እንዴት አብልጣ አታማልድ?

👉 አነ ሳሚ ዘዉሉደ ብርሃን

ለመቀላቀል

👉 @weludebirhane





17 last posts shown.