Forward from: ከአንቂ መጻሕፍት ገፆች
" ማደግ የሚናፍቀኝ እንደነ ‘እገሊት‘ እንደነ ‘እገሌ‘ ለመሆን ሆነ ። እንደ‘ራሴ‘ መሆን መኖሩን የማውቅበት ስንዝር የሀሳብ ክፍተት አልነበረኝም ። እገሊትና እገሌን ለመሆን ስኳትን ብዙ ስብርባሪ እገሌዎችን ሆንኩ ። ሁሉንም የምሞክር ፣ ልክና ስህተትን ልክ ሆኜና ተሳስቼ የምፈትን ፣ ቀናና ወልጋዳውን ቀንቼና ተወላግጄ የማረጋግጥ ሆንኩ ። ምክንያቱም ትክክለኛ መንገድ የሚሉትን በዱላና በስድብ ሊያሳምኑኝ ሲሞክሩ እንጂ ሲኖሩት አይቼ የማላውቅ ነኛ ! .. "
ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም
ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም