'ገብቶኛል' እና 'እኔም ጋር እንደዛው ነው' ይለያያሉ አደል... ደስታዬ ተጋብቶብህ ተደስተህ ሳትደሰት ብቻ ገብቶህ... እከክ ሳያሳክክህ ያሳከከህ ያክል ስትረዳው ደሞ ይለያያል አደል
?
ይመስለኝ ነበር የገባኝ ያከኩኝ የተደሰትኩ የቆሰልኩ... ደርቆልኝ ልጬው ጠባሳው የሻረ ፤ ተደስቼ የጠገብኩ ጥጉን ያየሁ ይመስለኝ ነበረ... መች አወቅኩ ታዲያ ካለፈው የበረታ የጠለቀ ቁስል ካለፈው የበረታ ሆድን የሚያሳምም ፈገግታ እንደምፈግግ መች አወቅኩ... ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም ብዬ የተገበዝኩበት ኑሮ ፀሐይና በታችን እንኳን በግል ያልተረዳሁበት ሆነኣ ታዲያ።
አልገባኝም ገና... በዚህ አያያዜ መቼም ላይገባኝ ይችላል ፣ የገባኝ እንዳልገባኝ የገባኝ ብቻ መሆኑ ከ ሶቅራጥስ (ጲላጦስ ብዬ ልፅፍ ነበር... ለነገሩ ያው ናቸው ያም እጁን ታጠበ ይሄም እጁን ታጠበ) ከሶቅራጥስ ጋር ያዛምደኝ ይሆን እንዴ?... ርዕስ የሌለው መጽሐፍ ስም አልባው ደራሲ... ሃሳብ አልባ አሳቢ እግር አልባ ተጓዥ ምናምን እንደሚሉት እነዛ የጥበብ ሰዎች...... አልገባኝም...ገብቷቸዋል ግን እኔ አልገባኝም... ላስረዳህ ቢሉኝ እንኳ ይደብመኛል እና አልደክምም
"...ስለ ጲላጦስና ሶቅራጥስ( ፈላስፋ በጠቅላላው) ሌላ ጊዜ በደንብ እናወራለን
🖋ውሃ
https://t.me/wuhachilema