በአገልግሎት አሰጣጥና ደንበኛ አያያዝ ፣ ስትራቴጂክ እቅድን እስከታች ካስኬድ ማድረግና ሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ስሌት አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ፡፡
(ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ እቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና የሪፎርምና አገልግሎት ክትትል ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬቶች በጋራ በመሆን በአገልግሎት አሰጣጥና ደንበኛ አያያዝ ምንነት እንዲሁም ስትራቴጂክ እቅድን እስከታች ካስኬድ ማድረግና ሳይንሳዊ የምዝገባና የንጽጽር ስሌት አሰራር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጠዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ቀደም ሲል በ11ዱ ክፍለ ከተሞች ክትትልና ድጋፍ መደረጉን አንስተው በድጋፍና ክትትሉ ውጤት መሰረት ፍረጃ በመስጠት የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ልምዳቸውን በመቀመር ለሌሎቹ እንዲያሳልፉ መደረጉን ተናግረው በድጋፍና ክትትሉ የታዩ እጥረቶችን ለመሙላት ቢሮው ስልጠናውን ማዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡
በሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች የተዘጋጀው ስልጠና በድጋፍና ክትትል ስራ ከአገልግሎት አሰጣጥና መደበኛ ስራዎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የታዩ እጥረቶችን ለመሙላት ያስችላል ያሉት አማካሪዋ ሰልጣኞች በስልጠናው ከሚነሱ ርእሰ ጉዳዮች በመነሳት ያላቸውን ግንዛቤ ማዳበርና አገልግሎት አሰጣጥና ሪፎርም ስራዎች የሚያጋጥሙ እጥረቶችን በመሙላት በሁሉም የትምህርት ተቋማት ተቀራራቢ ውጤት እንዲኖር መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡