በድሬዳዋ የመጀመሪያው የአእላፋት ዝማሬ ተካሔደ
| ጃንደረባው ሚዲያ | ታኅሣሥ 28 2017 ዓ.ም.|
ድሬዳዋ ኢትዮጵያ
ከጥቅምት 5-2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ይፋ የተደረገው የአእላፋት ዝማሬ ከሦስት ወራት የመዝሙር ጥናትና የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ በኋላ አእላፋት በተገኙበት በእግዚአብሔር ቸርነት በድሬዳዋ የመጀመሪያው ዙር የአእላፋት ዝማሬ በድሬዳዋ ምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ በድምቀት ተካሔደ::
ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ የሁሉም አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና ሰ/መ/ጉ/ጽ/ቤት አባላ ተገኝተዋል:: በኢጃት ጃን እስጢፋኖስ ሥር በሚያገለግሉ 12 ዲያቆናት ባካሔዱት በመሐረነ አብ እና በምሕላ ጸሎት ጉባኤው የተጀመረ ሲሆን በጸሎቱ ፍጻሜም በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ደርሶአል::
በዕለቱም ምእመናን 60 ካሬ ስክሪኖች በአራት አቅጣጫ እየተመለከቱ አብረው የዘመሩ ሲሆን ፍጹም በተረጋጋ መንፈሳዊ ድባብ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ልደት በአእላፋት ዝማሬ አክብረዋል:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ወጣቶች ለወራት በብዙ ጸሎትና ትጋት የደከሙበት ይህ የዝማሬ ማዕድ በእግዚአብሔር ጥበቃ ባማረ ሁኔታ ተከናውኖአል:: አእላፋት በዕንባና በተመሥጦ ሆነው እየዘመሩ የመድኃኒታቸውን ልደት በመንፈስ አክብረዋል: