ስልጤን እንደ ሞዴል
~
የስልጤ ወገኖቻችን ለቀሪው የኢትዮጵያ ሙስሊም ጌጥ ናቸው፣ ድምቀት። ከዚህም አልፎ መቀዛቀዝ አልፎም ማንቀላፋት ለሚታይበት የብዙ አካባቢ ሙስሊም ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው። ከዞኑ አልፎ በአዲስ አበባ የሚኖሩት፣ ከዚህም አልፎ በውጭ የሚኖሩት ጭምር ለዲናቸው ትጉ ናቸው። ይሄው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት ተግተው እየታገሉ ነው። ቀላል የማይባል ርቀትም ተጉዘዋል። በዞኑ ዐረብኛ ትምህርት እንዲሰጥም ዝግጅታቸውን እየጨረሱ ነው። ሀይረንዚ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በዚህ ት/ቤቶች ተማሪዎቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ባቃታቸው ጊዜ ሙሉ ተማሪዎቹን እያሳለፈ ያለ ድንቅ ተቋም ነው። ዞኑ ውስጥ ካለው ባሻገር አዲስ አበባ ያሉ ዱዓቶች ወደተለያዩ የስልጤ ዞን ወረዳዎች እየተጓዙ ደዕዋ የሚሰጡበት አሰራር አላቸው። ይሄ በዱዓት ብቻ የሚቻል አይደለም። ስለመጠኑ ባላውቅም የነጋዴው ሚና ወሳኝ ነው። ባጠቃላይ በዞኑም ከዞኑም ውጭ ከሌላው ማህበረሰብ በተሻለ መልኩ active ናቸው። አላህ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣቸው። ከሆነ ጊዜ ወዲህ ስልጤን የሚያጠለሹ ድምፆች ከፍ እያሉ የመጡት ያለ ምክንያት አይደለም።
መልእክቴ ምንድነው?
1ኛ፦ ለስልጤ ህዝብ ከዚህም በላይ አቅም አላችሁና ትጋታችሁን ይበልጥ አጠናክሩ እላለሁ። ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ጭምር እያሰባችሁ ተንቀሳቀሱ። እንቅስቃሴያችሁ በጥናት የታገዘ ይሁን። ዙሪያችሁ ያሉ ስጋቶችን የምትቋቋሙበት ሁለ ገብ አቅም መገንባት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ከዞኑም ውጭ አጎራባች አካባቢዎች ላይ ጭምር ስሩ። ዳር ካልተከበረ መሀል ዳር ይሆናል።
2ኛ፦ ለሌሎች አካባቢዎች ተወላጆች ደግሞ ከሰመመናችሁ ውጡ፣ ተንቀሳቀሱ፣ ተደራጁ እላለሁ። ቢቻል በዞን ደረጃ። ካልተመቸ ቢያንስ በወረዳ ደረጃ መንቀሳቀስ ይገባል። በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ የምትኖሩ መነሳሳቱን ብትወስዱ መልካም ነው።
* አንዳንዱ አካባቢ ብዙ ህዝብ እየከ -ፈ ^ ረ ያለበት ነው። ይሄ እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ ነው። ጉራጌ ዞን እና ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ይሄ አደጋ በተጨባጭ አለ።
* አንዳንዱ አካባቢ ህዝቡ እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ከዲን የራቀ በመሆኑ የተነሳ ብዙ አይነት ሺርክ፣ የካ - fiሮችን በዓል ማክበር፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት፣ ሶላት አለመስገድ፣ ጥንቆላና ድግምት፣ እርስ በርስ መገ ^ዳደ ል በሰፊው አለ። እነዚህ አደጋዎች ሁሉም ወይም ከሌሎቹ በየክልሉ ይታያሉ። ይሄው ሰሞኑን ትግራይ ውስጥ ጥምጣማቸውን የለበሱ ወገኖች የገና በዓል በጭፈራ ሲያከብሩ አይተናል። አማራ ክልልም ጥምቀትን የሚያከብረው ብዙ ነው። ኦሮሚያም አንዳንድ አካባቢዎች አለ። ሙስሊም በዝ በሆኑ ክልሎች ላይ ያለው ብሄር ወለድ ግጭትም ሰፊ ነው። ሺርኩ አይወራም። ከቤኒሻንጉል እስከ ሶማሌ፣ ከትግራይ እስከ ሞያሌ የተንሰራፋ ነው። ዐፋር ለራሱ ቀርቶ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ባጠቃላይ የክፉ ጊዜ መከታ ነው። ከዚህም በላይ ደጀን መሆን የሚያስችለው አቅም ነበረው። የንቃቱ የመደራጀቱ ጉዳይ ግን ገና ነው። የሶማሌም ሙስሊም ለኢትዮጵያ ሙስሊም አለኝታ የሚሆንበትን አቅም አላዳበረም። በተውሒድ ረገድ ሁሉም ብዙ ስራ ይፈልጋል። በአካደሚው ዘርፍ በጣም ወደኋላ የቀረን ነን።
ሌላው ሁሉ ቢቀር አዲስ አበባ የሚኖረው የነዚህ ክልሎች ተወላጅ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ቢሰራ የሚያቅተው አልነበረም። ነጋዴዎች ባለ ሃብቶች ጉዳዩን ለዱዓት አትተውት። ዛሬ ህዝብን ለማንቃት ቀርቶ ለደዕዋ እንኳ ያለ ገንዘብ ምንም ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ አደራጁ ተረባረቡ። የምትችሉ አካላት የማነሳሳቱን ጉዳይ ኃላፊነት ወስዳችሁ ስሩበት። አላህ ያግዘን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor