ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋውሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፯
...ሜርሲ ድምፇን ከፍ አርጋ ጮኸች ሁላችንም ተደናገጥን ማን ሊወስደው ይችላል ከዛ ሰውዬ ውጪ አንድም ሰው እንደዚ አይነት ስራ አይሰራም...ቅድስቴ ድንኳኑ ጫፍ ላይ ቁጭ ብላ ትንሰቀሰቃለች ባርሰናይትም በፊናዋ ፊቷን ባባ ደረት ላይ አድርጋ ታለቅሳለች እኔ በድንጋጤ የማወራውም የማስተውለውም ነገር የለም ፍዝዝ ድንዝዝ ብያለው ነይ "ቅድስቴ ተነሺ" ብሎ ባባ ሊያነሳት ሲሞክር "ልቀቀኝ ብቻዬን መሆን እፈልጋለው" አለች ከፍ ባለና ቁጣ በተሞላው ድምፅ በዚ ጊዜ ባባ ወደሗላ ተመለሰ ቅድስቴ ደሞ ወደ ድንኳኑ ገብታ ደሙን በእጆቿ መንካት ጀመረች በዚህ ገዚ ከተያዝኩበት የድንጋጤ እና የድንዛዜ ስሜት ነቃሁኝ ወደ ቅድስቴም ድንኳን ገብቼ እጇን ያዝኳት ባባ ላይ እንደሆነችው ጮኸች "ልቀቂኝ ልቀቂኝ" አለች እየደጋገመች እኔ ግን እንደ ባባ አልተውኳትም መመነጫጨቋንና ቁጣዋን ችዬ እቅፍ አድርጌ ወደራሴ አስጠጋሗት "ተረጋጊ ተረጋጊ የኔ ውድ አይዞሽ" እያልኩኝ ለማረጋጋት ሙከራ ጀመርኩ ግን አሁንም መወራጨቷንና እየጮኸች ማውራቷን አላቆመችም ለሩብ ደቂቃዎች ያህል ያለ ማቋረጥ ቀጠለች እኔም ድምፇ የቱንም ያህል ቢከብደኝም እንዳቀፍኳት አለሁ...ድካም ተሰማት መሰለኝ ድምፇ እየተስለመለመ መጣ ረጋ ባለ ድምፅ "እኔን ለማ ጥለኸኝ ነው ምትሄደው ምነው ብትነግረኝ ልሄድ ነው ብትለኝ እኔ አልሰማም ብዬሃለሁ ጨካኝ ነህ" እያለች ከራሷጋ ሰጣ ገባ ውስጥ ገባች...በዚ ሁኔታ ውስጥ ብዙም ሳትቆይ እንቅልፍ አሸለባት ወደ ድንኳኑ መውጫ ስመለከት ባባ እና ባርሳ በሚያቆረፍደው፡የለሊት ብርድ ውስጥ ቆመዋል...ባባ ወደኔ እንዲመጣ ምልክት ሰጠሁት ከዛም ጥንቃቄ በተሞላበት አያያዝ ለሁለት ተሸክመን ከድንኳኑ አወጣናትና እኔ ድንኳን ውስጥ አስተኛናት..."እሷ ትተኛ እኛ ደሞ ሮቤልን እንፈልገው" ሲል ባባ ባርሳ ሰምታ ኖሮ "ምንድነው ምታወራው ከእንግዲህ ተጣጥለን መንቀሳቀስ የለብንም የማይሆን ሀሳብ ነው" አለችው "ባርሳዬ እሱን ለመፈለግ ምንም አለማረጋችንን ስታውቅ ታዝንብናለች ብዬ እኮ ነው ስለሱ ምንም ግድ እንደሌለን ነው ምታስበው ከደረሰባት ነገር ጋ ተያይዞ የባሰ ትጎዳለች ከጓኗ እንዳለን እንድታውቅ ይህን ማድረግ አለብን" አለ ባባ ሊያሳምን የሚችል ምክንያት በማቅረብ "ምንም ሊሆን ይችላል እኔ አንተ በምትለው ነገር ፈፅሞ አልስማማም ራሳችንን አደጋ ውስጥ በመክተት ነው እንዴ ከሷጋ እንደሆንን ምናሳየው በዚ ሁኔታ ውስጥ ድጋሜ አንዳችን ብንጠፋስ?" በማለት ባርሰናይት የባባን ሀሳብ ተቃረነች "እንዴ ምንድነው ምትጨቃጨቁት ተረጋጉ እንጂ ለጊዜው ራሳችንን እናረጋጋ ግን ሮቤልን መፈለጋችን አይቀርም ለቤተሰቡስ ምን ብለን ነው ምንናገረው" እያልኩ እየተናገርኩ ሳለ ባርሳ ጣልቃ ገብታ "አንቺም ሜርሴ እንደዚ ትያለሽ ያለንበት ስፍራ እጅግ አስፈሪ ስፍራ ነው እኛም ማደራችንን እንጃ ጭራሽ ደግሞ ፍለጋ እንሂድ ትያለሽ" ብላ ጥያቄዋን አስከተለች "እንደሱ ማለቴ አይደለም ግን ቢያንስ ስለሱ የሆነ ነገር ማወቅ አለብን ተማለት ነው" ብዬ ሃሳቤን በእርጋታ አስረዳሗት ግን ባርሳ አሻፈረኝ "የማይደረገውን አጠይቁኝ" ብላ በእንቢተኝነቷ ቀጠለች "እሺ አሁን እንተኛ ማልዶ ሲነጋ ሁሉንም እናወራለን " አለ ባባ በሀሳቡ ተስማምታ ባርሳ ወዲያውኑ ወደ ድንኳናቸው ገባች "ደና እደሪ" ብሎ ባባም ተከተላት እኔ ደግሞ ቁጭ ብዬ የቅድስቴን አይን አይኗን ማየት ጀመርኩ...ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ መወረጫጨት ጀመረች በጣቶቿ አንሶላውን ወዲያ ወዲህ እየጎተተች...ሊሞት እንደሚያጣጥር ሰው አደረጋት በጣም ተደናግጬ ተጠጋሗትና መወራጨቷን እንድታቆም አጥብቄ ያዝኳት ወዲያውኑ ከፍ ባለና ቁጣ በተሞላበት ድምፅ "ልቀቀኝ" ብላ ተነስታ ወደ ድንኳኑ ግድግዳ ተጠግታ ቁጭ አለች አይኖቿ መገለጣቸውን ሳይ ላረጋጋት ስጠጋት "እንዳትጠጋኝ ልገለኝ ነው" አለች በጣም ደነገጥኩኝ ቅድስቴ ችግር ውስጥ እየገባች ነው የሷን ጩኸት ሰምተው ይመስለኛል ባባ እና ባርሰናይት ከውጪ ቆመው "ምንድነው" አሉ ድንጋጤ በተሞላበት ድምፅ ከዛም ቀጠል አርጎ "ክፈቺው ሜርሲ" አለኝ ባባ ውስጥ ያለውን ነገር ለመመልከት እኔም ከፈትኩላቸው አንገታቸውን ወደ ውስጥ እያሰገጉ ምን እንደተፈጠረ እንድነግራቸው ጠየቁኝ "ቅዠት ነው መሰለኝ አላውቅም ድንገት ነው የጮኸችው" ብዬ መለስኩላቸው...ቅድስቴ በጣም እያለቀለከች ነበር በዚ ቢሚጋራፍ ውርጭ ሰዓት እሷ ግን ላበላብ ሆናለች "ቅድስቴ" አላት ባባ በተንጨበረረው ፀጉሯ መሀል አይኗን ወደሱ አንስታ ተመለከተችው ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠችውም ጉልበቷን ወደ ደረቷ ስባ እጆቿን ጉልበቷ ላይ አስደግፋ አገጯን እጇ ላይ አድርጋ ወደፊት ወደሗላ እያለች ትወዛወዛለች ግን አንዲትም ቃል አተነፍስም ውስጧ በጣም መረበሹን እና ድንጋጤው እንዳልተዋት ተረዳሁ "ቅድስት አይዞሽ ተረጋጊ እኛ አለንልሽ" አለቻት ባርሰናይት እሷንም በአይኗ ከመመልከት ውጪ አንዳች መልስ አልሰጠቻትም ነበር...በጥቂቱም ቢሆን አሁን አተነፋፈሷ እየተስተካከለ ነው ከገባችበት ድንጋጤ እየተላቀቀች ነው "ድንጋጤው ነው እንደዚ ሚያረጋት በቃ ግቡና ተኙ እኔ አለሁ" አልኳቸው ለነ ባባ ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ እየነገርኳቸው "እሺ ችግር ካለ አሳውቂን" አለ ባባ "ጓደኛዬ አለንልሽ" አለች ባርሳ ወደ ቅድስቴ እየተመለከተች...የተፈጠረባት ነገር የሰላም እንቅልፍ እንደማይሰጣት የታወቀ ነው እናም ተረጋግታ እንድትተኛ የእንቅልፍ መድሃኒት ሰጠሗት ደረቴ ላይም አስጠግቼ "አይዞሽ አይዞሽ" እያልኩ ፀጉሯን እያሻሸው አስተኛሗት ከላዬ ላይ አውርጄ ወደ ፍራሹ ካደረኳት በሗላ ብርድ ልብስ አለበስኳት ከዛም ሻንጣዬን ከፍቼ ወፍራም ጃኬት አውጥቼ ለበስኩ ከድንኳኑ ወጣሁና ቅድስቴ ላይ ዘጋሁባት በያዝኩት ባትሪ ድንኳናችን አካባቢ ያለውን ነገር ቃኘሁት እነ ባርሳ ድንኳን አጠገብ አጠር ያለ ትንሽ ውፍረት ያለው እንጨት ተመለከትኩ ሄጄም አነሳሁት ከዛ ማንም ሳይሰማ ሮቤልን ፍለጋ ወደ ጨለማው ጫካ ውስጥ ገባሁ............
_Part #8 ___ይቀጥላል
ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱